Connect with us

በዳንሱ ያደነቃችሁትን በሀሳቡ ለምን ትገረማላችሁ?

በዳንሱ ያደነቃችሁትን በሀሳቡ ለምን ትገረማላችሁ?
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

በዳንሱ ያደነቃችሁትን በሀሳቡ ለምን ትገረማላችሁ?

በዳንሱ ያደነቃችሁትን በሀሳቡ ለምን ትገረማላችሁ?

ለሁሉም ከመቸኮል ሀገር ለማዳን መቸኮል ይበጃል!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

ዲሽታ ጊና አዳም ወንድሜ ስላለ ወደዳችሁት አይደል? እውነቱን ልንገራችሁ አዳም ወንድሜ ያለው ታሪኩ አይደለም፤ ፕሮፌሰር ገብሬ ኢንቲሶ ይባላል፤ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ነበር። ለነገሩ ዘፈኑን አድምጣችሁ ንግግሩን ሳትሰሙ ብትቀሩ ነው እንጂ ታሪኩም የግጥሙ ደራሲ ፕሮፌሰር ገብሬ ኢንቲሶ መሆኑን ደጋግሞ በየሚዲያው ነግሯችኋል፡፡

ከዚያስ? አሌክስ ይለፍ የሚባል ድንቅ የሙዚቃ አቀናባሪ ሀገር የተወዛወዘበትን ዜማ ሙዚቃ አድርጎ ሰራው፡፡ መልእክተኛው ይዞት በድምጹ አደባባይ ወጣ፡፡ ያለ አግባብ ሆ ብለን ስናደንቅ መሰናክል መሆናችንን ጭምር አላጤንም ነበር፡፡

የድምጻዊው ሀሳብ መጥፎ አይደለም፤ እርቅ እያለ ነው፡፡ ድምጻዊው በኢትዮጵያ ጉዳይ ራሱን እንደ ኦባሳንጆ ቆጥሯል፡፡ የትህነግ ሚዲያዎች በደስታ ተቀባብለውታል፡፡ አድናቂዎቹ በሀገራችን መጣ በሚል መንፈስ ቅር ብሏቸዋል፡፡

እንደውም እግዜር አትርፎናል፤ በየመድረኩ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ሳይቀር ሲተቃቀፍ የከረመ ዘፋኝ ጦርነቱ የወንድማማች ነው ይቅር ሲል አድምጠውት ቢሆን ሀሰተኞቹ የምዕራብ ሚዲያዎች “አንድ ለእናቱ የሆነው ኢትዮጵያዊ ከያኒ ጦርነቱን አወገዘ” ብለው ዜና በሰሩ ነበር።

ሰው የሚመዘንበት እንደ እድሜው፣ እንደ እውቀቱ፣ እንደ ትምህርቱና እንደ ኑሮው ነው፡፡ አሁን በዳንሱ የወደድነውን ድምጻዊ በሀሳቡ ማውገዝ ደስ አይልም፡፡ ቀድሞስ ቢሆን በሀሳቡ መች ቦታ ሰጠነው፡፡

በአንድ ነጠላ ዜማ ሀገርና የሀገር ክብር እጃቸው ላይ እያኖርን እጣ ፈንታችን ምላሳቸው ላይ እንዲያርፍ የሚያደርግ ቂልነት ትልቅ ሀገር ለመፍጠር ሳንካ መሆኑን ብንማርበት ግን ደግ ነው፡፡

ከየት መጣ? ሳንል፤ የት መሄድ ይፈልጋል? የሚለው ሳያሳስበን ብዙ ሰዎች የዕለቱ ልብ ገዢዎቻችን ስለሆኑ ሆ ብለን ተከትለናቸዋል፡፡ ገደሉ አፋፍ ሲያደርሱን ሆ ብለን አውግዘናቸዋል፤ ቀድሞውኑ ለክቶ እና መዝኖ ቦታ የመስጠት ባህላችን ቢያድግ ኖሮ ከጥፋታቸው እንኳን መልካሙን መምዘዝ በቻልን ነበር፡፡

እናት ሀገሩን ለማፍረስ ሲዖል መውረድ የሚፈልግ ሰው ወንድሜ የሚል ወንድም ሊኖረን ይችላል፤ ሲዖል ወርዶ ከሀገር አፍራሽ ጋር ፍቅር ልሁን ማለት ግን የፍቅርን ክብርም ስምም ማጉደፍ መሆኑን ከተስማማን ሌላው ቀላል ነው፡፡

በአድናቆት ለማጨብጨብ ከተረጋጋን በነቀፋ ለመቆጨት አንቸኩልም፡፡ ሀገር ጠባቂ ወንድሞቻችን የታረዱብን፣ እናት እህቶቻችን የተደፈሩብን፣ ሀገራችን እንድትፈርስ የተሴረብን ህዝቦች ነን፤ እናም ለእኛ ፍቅር እና ወንድምነት ሀገር ማዳን ነው፡፡

ለማድነቅም ለመውቀስም እንቸኩላለን፤ አሁን የሚያስፈልገን ችኮላ ግን መሆን ያለበት ሀገር ለማዳን ነው፡፡ ያኔ ነገሮች መልካቸው ሌላ ነው፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top