Connect with us

አፋር ትናንትም እንደዛሬው የኖረ ነገም በሀገሩ ጉዳይ ቀጥ ያለ አቋም ያለው ህዝብ ነው!!

Social media

ነፃ ሃሳብ

አፋር ትናንትም እንደዛሬው የኖረ ነገም በሀገሩ ጉዳይ ቀጥ ያለ አቋም ያለው ህዝብ ነው!!

አፋር ትናንትም እንደዛሬው የኖረ ነገም በሀገሩ ጉዳይ ቀጥ ያለ አቋም ያለው ህዝብ ነው!!

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)
አፋር አሁን ሆነ ብለን የምንገረምበት የረዥም ዘመን ግብሩ ነው፡፡ እንዲህ ነው የኖረው፡፡ እንዲህ ነው ለሀገር ዘብ ሆኖ እንደ ሸማ በበርሃ ያሳለፈው፡፡ አፋር በፖለቲካዋ ብልሽት አልቀርብ ያለችውን ሀገሩን ሩቅ ሆኖ ቀርቦ የኖረ በሳል ህዝብ ነው፡፡

እንዲህ ያለውን ምስክርነት የምጽፈው ዛሬ በተሰለፈበት ግንባር ድል ስላደረገ አይደለም፡፡ በድሉ ሀገር ታፍራ እንድትኖር ያልታፈረ ድንበር ጠባቂ ህዝብ ነው፡፡ ስለ አፋር ብዙ ጊዜ ደጋግሜ ጽፌያለሁ፡፡ ብዙ ብያለሁ፡፡ ስለማውቀው ዛሬም እመሰክራለሁ፡፡ አፋር ሀገሩን ይወዳል፡፡ በሀገሩ አፍሮ አያውቅም፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን ስለ አፋር ማፈር አለበት፤ ይሄ ህዝብ ነው ታሪኩም ዝናውም ጥቅሙም ችላ ተብሎ የኖረው፡፡

አፋር ድንቅ እሴት አለው፡፡ ቀድሞውኑም ወንድሙን አይገድልም፤ አፋር በአፋር ላይ አይነሳም፡፡ በዚህ ልብ ሀገሩንም ሰውንም ይወዳል፡፡ ከሰፈሬ ውጣ የሚል ህዝብ አይደለም፡፡ ሀገር ሰርቷል፡፡ ሰፈሩ ሀገሩ ናት፡፡ የአህጉራችን ድንቅ ህዝብ ነው፡፡

መሳሪያ ይዞ ይውላል፤ ግን የጥይት ድምጽ የማይሰማበት ጫካዎች አሉት፡፡ ጊሌ ታጥቆ ያጌጣል ደም ማየትን የሚጠየፍ ወገን ነው፡፡ ሀገርን ያለ መሃል ሀገር ፖለቲካ አለኝታነት አስከብሮ ኖሯል፡፡ ጠረፉ ተሰጥቶት አደራውን በልቶ አያውቅም፡፡

አፋር በጀግንኑት ድንበሯ ያለ ኮሽታ የታፈረ ሀገር አኑሯል፡፡ በተቃራኒው ግን የኢትዮጵያ ቤተ መንግስት የሸለመው ከወንድሙ የሱማሌ ህዝብ ጋር በጦርነት ሲታመስ እንዲኖር ሴራ መጎንጎንን ሆነ፡፡

አፋርና ኢሳ ወንድማማቾች ናቸው፡፡ ከጠብና ከሰላማቸው መራቅ ጀርባ ስውር የፖለቲካ ሴራ አለ፡፡ አፋር የሀገሬ ፖለቲከኛ አሴረብኝ ብሎ ሀገሩን አይጠላም፡፡ እየቻለ ያሳለፈውን መአት ለመመልከት አሁን እንኳን ሀገሩን እንደምን እንደታደገ መመልከት በቂ ነው፡፡

ከዩኒቨርሲቲዎቻችን በላይ የራሳችን እሴት ብንማማርበት ዓለምን የምንሰራበት ድንቅ ጉልበት ነበረው፡፡ ከአፋር ብዙ እምንማረው ነገር አለ፡፡ አፋር በመረጃ ያምናል፡፡ አፋር እውነተኛ መረጃ ይሰጣል፡፡ አፋር ለጥቅም ወንድሙንም ወገኑንም ሀገሩን አሳልፎ አይሰጥም፡፡ የጎሳ መሪዎችን ያደምጣል፡፡ ልብ ለልብ ለመግባባት በየወንዙ መማማል አያስፈልገውም፡፡ ይሄ እሴት እንደ ሀገር ብንማርበት እንደ ሀገር የምንድንበት መድሃኒት ነው፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top