Connect with us

ብሄራዊ ምክክር እና መንግስት

ዶ/ር ደረጄ ገረፉ

ነፃ ሃሳብ

ብሄራዊ ምክክር እና መንግስት

ብሄራዊ ምክክር እና መንግስት 

(ዶ/ር ደረጄ ገረፉ)

ሰሞኑን የተለያዩ አካላት ስለብሄራዊ ምክክር የተለያዩ አስተያዮቶችን ሲሰጡ እየተመለከትኩ ነው።

ጥቂቶች ብቻ ስለብሄራዊ ምክክር አስፈላጊነት ሲናነሳ ቆይተን አሁን ብሄራዊ ምክክር በዚህን ደረጃ አጀንዳ መሆን መቻሉ ደስ የሚል ነገር ነው። ነገር ግን ብሄራዊ ምክክር እና መንግስትን በተመለከተ በመንግስት ባለስልጣናትም ሆነ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ ትንሽ የተዛባ ነገር ያለ ይመስለኛል ።

መንግስት ለብሄራዊ ምክክር በ እውቅና መስጠት እና በውጤቱ ለመገዛት ( Buy-in) እንዲሁም  ብሄራዊ ውይይትን ለራሱ ፍላጎት ለመቆጣጠር ( Co-option ) መካከል በጣም ጥንቃቄ እና ሚዛኑን  በጠበቀ መልኩ  መጓዝ  አለበት።

ለአንድ ብሄራዊ ምክክር ስልጣን ላይ ያለው የመንግስት አካል በበቂ መልኩ እውቅና ካልሰጠው እና ከብሄራዊ ምክክሩ የሚመነጩ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመተግበር እና በነሱ ለመገዛት ከምሩ  ካልቆረጠ  ያ ብሄራዊ ምክክር ሳይጀምር ወድቋል ማለት ይቻላል። 

በተመሳሳይ መልኩ መንግስት ብሄራዊ ምክክርን ለጠባብ  የስልጣን ዓላማው ማስፍፈፀሚያ መሳሪያ ለማድረግ በሚያስቸለው መልኩ ለመቆጣጠር ( Co-option)  ፍላጎት ካለው እና ማን በብሄራዊ ውይይቱ እንደሚሳተፊ መሥፈርት ማውጣት ከጀመረ በተመሳሳይ ማልኩ ብሄራዊ ውይይቱ ሳይጀመር ወድቋል ማለት ይቻላል።

ስለዚህ መንግስት ብሄራዊ ውይይቱ ውጤት እንዲያመጣ ከፈለገ ለብሄራዊ ውይይት  በቂ እውቅና መስጠት እና ለውጤቱም ተገዥ ለመሆን መዘጋጀት በአንድ በኩል ሲያስፈልገው በሌላ መልኩ እጁ ረዝሞ እንዳይቆጣጠሩው እና ያንን የሚመስል ምልክት እንዳይፈጠር በጣም መጠንቀቅ አለበት። በእርግጥ በዚህ ረገድ መንግስት ብቻም ሳይሆኑ ከመንግስት ተቃራኒ የቆሙትም መንግስት በአከባቢው ስላለ ብቻ መበርገግ ሳይሆን የመንግስት ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ በአከባቢው መኖር አስፈላጊ መሆኑን ከግንዛቤ ማስገባት አለባቸው።

በአጭሩ መንግስት ከላይ ባነሳሁት እና ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ  እውቅና ሰጥቶ በሌላ መልኩ  አላስፈላጊ ጫና  ሳይፈጥር ብሄራዊ ምክክር ለማድረግ የሚያስችል ምህዳር መፍጠር ካልቻለ ብሄራዊ ምክክር ባይደረግ ይመረጣል።

ምክንያቱም  እሄ ለሀገር ፍቱን የሆነ ብሄራዊ ምክክር አንዴ ከወደቀ ለሁለተኛ ጊዜ መሞከር ስለማይቻል ነው።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top