Connect with us

ኢትዮጵያን ሊበትን- አገሩን ሊጎዳ…

ኢትዮጵያን ሊበትን- አገሩን ሊጎዳ እልፍ ወጣት አዝምቶ ፥ ጌታቸው ረዳ ትግራይን ገደላት፥ ቦሩ አላንሻ ሜዳ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ኢትዮጵያን ሊበትን- አገሩን ሊጎዳ…

ኢትዮጵያን ሊበትን- አገሩን ሊጎዳ

እልፍ ወጣት አዝምቶ ፥ ጌታቸው ረዳ

ትግራይን ገደላት፥ ቦሩ አላንሻ ሜዳ

(አሳዬ ደርቤ ለድሬ ቲዩብ)

በራቢስ እንደተለከፈ ውሻ የማሰብ አቅሙን የተነጠቀው ‹‹ሽብርተኛ›› አማራ እና አፋር ክልል ላይ ወረራ ፈጽሞ የጦርነት ሜዳውን ከክልሉ ማውጣቱ የተወሰኑ ዞኖችን የሚዘርፍበትን፣ ክልሎችን የሚያወድምበትን እና በውሸት የድል ዜና እያማለለ የክልሉን ወጣቶች የሚያዘምትበትን እድል አስገኝቶለታል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ እንደ አሸዋ በሲኖ ትራክ እየጫነ ከሞት ቀጠና ውስጥ የሚደፋቸው ወጣቶች እረግፈው መቅረታቸውን የትግራይ እናቶች እንዳያውቁ እረድቶታል፡፡

የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት ሐጂ አወል አርባ ‹‹ምክንያት የለሽ ወረራ ፈጽሞ ከአፋር አሸዋ ውስጥ እረግፎ የቀረውን እልፍ አእላፍ ወጣት የትግራይ እናቶች ቢመለከቱ ኖሮ ልጅ አልባ ያደረጋቸውን አሸባሪ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጎን ተሰልፈው ይደመስሱት ነበር›› እንዳሉት ጦርነቱ በሌላ ክልል መካሄዱ ለጌታቸው ረዳ ፕሮፖጋንዳ ምቹ ሁኔታ ፈጥሮለታል፡፡ በጥይት ያለቀውን ወጣት ከመቃብር አስነስቶ ‹‹ወደ አራት ኪሎ እየገሰገስን ነው›› በሚል ብሽከታ ተጨማሪ ሟች የሚያዘምትበትንና የህውሓትን እድሜ የሚቀጥልበትን እድል ፈጥሮለታል፡፡

በነገራችን ላይ ከሌሎች የህወሓት አመራሮች ነጥዬ ጌታቸው ረዳ ላይ ያተኮርኩት ባሁኑ ሰዓት በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ስለ ጦርነቱ ሁኔታ የሚረዱት ከጌታቸው ረዳ አንደበት በመሆኑ ነው፡፡ የሽብር ድርጅቱ ሕልውና ያለው ውጊያውን በሚመሩት አመራሮች እጅ ሳይሆን ጌቾ ምላስ ላይ በመሆኑ ነው፡፡

በዚህም መሠረት የእርዳታ ዱቄት ጭኖ በሄደ ተሳቢ አጭቀው በጎንደር ግንባር ያሠማሩት ወጣት በመከላከያ ሠራዊቱ፣ በአማራ ልዩሃይልና ፋኖ ጥይት ተለቅሞ ማለቁን የሚገልጽ ዜና ጌቾ ሲሰማ ዘና ባለ ስሜት ውስጥ ሆኖ ባንዱ ሚዲያ ይቀርብና ‹‹እጅ እንስጥ›› ብሎ በመናዘዝ ፈንታ ‹‹እጅህን ስጥ›› የሚል ማስጠንቀቂያ ለመንግሥት ያስተላልፋል፡፡

አሸዋ በሚጭን ሲኖትራክ አሳፍሮ ከአፋር አሸዋ ላይ የደፋው ሠራዊት ግመሎቻቸው በተገደሉባቸውና የጭራሮ ጎጇቸው በተቃጠሉባቸው የአፋር ጀግኖች እርሳስ ተመትቶ ከወረረው ምድር ላይ ሲቀር አይተ ጌታቸው ረዳ እንደ ኮሦ የሚመረውን እውነት ተቀብሎ በሕይወት ያለውን ወጣት የሚታደግ ሐሳብ በማስተላለፍ ፈንታ ህውሓትን የሚታደግ ውሸት ቀምሮ ከተፍ ይላል፡፡ በዚህም ቀደዳው በሽብር ሠራዊቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱትን የአፋር ጀግኖች ከTDF ጋር እንደተሰለፉና መከላከያ ሠራዊቱን ሲረፈርፉ እንደዋሉ በመግለጽ ተጨማሪ ዘማች (ሟች) የሚያገኝበትን ፕሮፖጋንዳ ይነዛል፡፡

የአፋሩና የጎንደሩ ወረራ የከሸፈበት አሸባሪ በቅርቡ ደግሞ ‹‹ደሴና ኮምቦልቻን እቆጣጠራለሁ›› ብሎ ያለ የሌለ ሃይሉን ወደ ደቡብ ወሎ ምድር ሲያስጠጋ የነበረ ቢሆንም ጁንታው በኩታበር፣ በአላንሻ፣ በቦሩ ሜዳ፣ በወረባቦ፣ በደላንታ ከሚያጓጉዘው የሽብር ሠራዊት መሃከል አብዛኛው በአየር ሃይላችን ዱላ ተመትቶ አየር ላይ ቀርቷል፡፡ ከተጫነበት ወኪና ወደ ምድር ሳይወርድ ወደ አመድነት ተቀይሯል፡፡ ቀሪው ደግሞ ደሴና ኮምቦልቻን ማየት እንደናፈቀ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩሃይል እና በፋኖ ክንድ ተደቁሶ የአላንሻ ሜዳ ላይ እንደ ቀጤማ ተጎዝጉዟል፡፡

ይሄንንም ሁኔታ ከስፍራው ተገኝቶ የተመለከተ አንድ ሰው የተሰማውን ስሜት የገለጸው እንዲህ በማለት ነበር፡፡

‹‹በዮሐንስ ዘመን- ወድቆ በታየበት- ወሎ እንደ ፍሪዳ

ሒሳብ ሊያወራርድ- ልጅየው ተገኝቶ- ቦሩ፣ አላንሻ ሜዳ

ሕይወት ሲከፈል ዐየሁ- አያቱ ያን ጊዜ- ያለበትን እዳ፡፡

ጠቅለል ስናደርገው ነፍስና ሥጋ ከተነጣጠሉ ሕይወት እንደማይኖር ሁሉ የጌታቸው ረዳ አንደበትና ውሸት ከተለያዩም ህውሓት የሚባል ድርጅት አይኖርም፡፡ ሆኖም ግን የጌቾ ምላስ መቅጠፉን የሚያቆመው እባብ መናደፉን ሲተው በመሆኑ አሁንም መተርተሩን ቀጥሎበታል፡፡ የቱርክ ሸሚዝ ከቱርክ ድሮን የሚታደግ ይመስል በነጫጭ ሸሚዝ በየሚዲያው እየቀረበ ትግራይን የሚያወድም ብሽከታውን አጠናክሯል፡፡ ‹‹የትግራይ ወጣት ካላላቀ በቀር የኔ ውሸት ለሊያልቅ አይችልም›› በሚል ቀደዳ እና በተበላበት ፕሮፖጋንዳ ሕይወት ማስገበሩን ቀጥሏል፡፡

ምንም እንኳን የአፋር አሸዋማ ምድሮች እና የደሴ ዙሪያ ሜዳዎች ላይ የተከሰተው እልቂት ከጌታቸው ረዳ ጭንቅላት ውስጥ ዘግናኝ ምሥል ጥሎ ማለፉ እርግጥ ቢሆንም፣ በቀጣፊ ምላሱ ግን ሠራዊታችንን እንዳይደመስስና ወደ አራት ኪሎ እንዳይገሰግስ ማድረግ አልተቻለም፡፡

‹‹ኢትዮጵያን ሊበትን፥ አገሩን ሊጎዳ

እልፍ ወጣት አዝምቶ ፥ ጌታቸው ረዳ

ትግራይን ገደላት፥ ቦሩ አላንሻ ሜዳ›› ተብሎ እስኪገጠም ድረስ ትግራይ ላይ ያለውን ፍጥረት ሁሉ አማራና አፋር ምድር ላይ እያመጣ የአሞራ ሲሳይ ያደርገው ይዟል፡፡

ድል ለኢትዮጵያ!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top