Connect with us

ወገን እንቁረጥ?!

ወገን እንቁረጥ?!
ፋሲል የኔዓለም

ነፃ ሃሳብ

ወገን እንቁረጥ?!

ወገን እንቁረጥ?!

(ፋሲል የኔዓለም)

ጌታቸው ረዳ ደሴንና ኮምቦልቻን በከባድ መሳሪያ ኢላማ ውስጥ አስገብተናል በሚል የለቀቀው ፕሮፓጋንዳ፣ መልዕክቱ ግልጽ ነው። መቀሌን በአየር የምትደበድቡ ከሆነ፣ ደሴንና ኮምቦልቻን በመድፍ እንደበድባለን ማለቱ ነው። አላማቸው አጥፍቶ መጥፋት እስከሆነ ድረስ፣ ምንም ነገር ቢያደርጉ አይገርመንም።

የሚገርመው ግን ወያኔዎች እዚህ ደረጃ መድረሳቸው ነው። እንዴት የሚለውን ጥያቄ ማንም በትክክል መመለስ የሚችል አይመስለኝም። ያው ብዙ ” ተከዳን፣ ተሸጥን” ከሚሉ፣ በአብዛኛው ድል በታጣ ጊዜ ከሚሰጡ አስተያየቶች በስተቀር፣ ማንም በትክክል እየሆነ ያለውን ነገር የሚያውቅ አይመስለኝም። ምናልባት ተዋጊዎችና አዋጊዎች የሚያውቁት ነገር ሊኖር ይችላል።

ያም ሆኖ ግን አሁን ያለንበት ሁኔታም የዓለም ፍጻሜ አይደለም። በኢትዮጵያ ያለው አቅም በወያኔ ዘንድ ካለው አቅም ይበልጣል። ይህን አቅም አሟጦ መጠቀም ግድ ይላል።  በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያ ሁለት ነገሮች ያስፈልጓታል።

አንደኛ፣ መነቃቃትን የሚፈጥር ጥሩ ተናጋሪ። ህዝቡ በእጁ ያለውን እምቅ ሃይል እንዲጠቀምበት፤ ድንዛዜ ውስጥ የገባውን ፣ ከድንዛዜው እንዲወጣ እንዲሁም የወያኔ መስፋፋት በኢትዮጵያና በህዝብ ህልውና ላይ የሚያመጣውን አደጋ አሳማኝ በሆነ መልኩ የሚያስረዳ  ተናጋሪ ያስፈልጋል። የሆነ አነቃቂ መንፈስ (spirit) የሚፈጥር፣ በምክንያት፣ በስሜትና በወኔ የሚናገር ሰው።    

ሁለተኛ፣ የህዝብ አደረጃጀት ግብረሃይል ያስፈልጋል። ወያኔ ከሌሎች አካባቢዎች ተዋጊዎችን ካላገኘ በስተቀር፣ በራሱ ሃይል ብቻ መስፋፋት አይችልም። ወያኔ በተስፋፋ ቁጥር ሃይሉ እየተበታተነ ይሄዳል። ይህን የተበታተነ ሃይል እያደነ የሚመታና የሚያዳክም፣ በህዕቡ የሚደራጅ ሃይል በሁሉም አካባቢዎች ማዘጋጀት ያስፈልጋል። አባይን ብዙ ገባሮች በየመንገዱ ባይቀላቀሉት፣ የሰከላው አባይ ብቻውን ግብጽ ባልደረሰ ነበር። ወንዙን ለማቆምም ባልከበደ ነበር። ህወሃትም ሌሎች ሃይሎችን እያሰባሰበ ካልተጓዘ በስተቀር፣ የትግራዩ ህወሃት ብቻውን የትም አይደርስም። ዋናው ይህን አውቆ መዘጋጀት ነው። 

ወገን እንቁረጥ! ሁሉም ነገር በእጃችን ነው። እናሸንፋለን ካልን እናሸንፋለን። ይህ የአሸናፊነት መንፈስ ከውስጣችን እንዳይወጣ እናድርግ። በምንችለው መንገዱ ሁሉ አገራችንን ለመታደግ በአጭር ታጥቀን እንነሳ።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top