Connect with us

ልክ ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑንም ወይዘሮ ገነት ዘውዴንም እኩል ማድነቅ አይቻልም፡፡

ልክ ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑንም ወይዘሮ ገነት ዘውዴንም እኩል ማድነቅ አይቻልም፡፡ ፕሮፌሰሩ በብሔር ኮታ አንቱ የማይባልበት ሀገር ሹም መሆናቸውን አንርሳ፡፡
Photo: Social media

ማህበራዊ

ልክ ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑንም ወይዘሮ ገነት ዘውዴንም እኩል ማድነቅ አይቻልም፡፡

ልክ ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑንም ወይዘሮ ገነት ዘውዴንም እኩል ማድነቅ አይቻልም፡፡ ፕሮፌሰሩ በብሔር ኮታ አንቱ የማይባልበት ሀገር ሹም መሆናቸውን አንርሳ፡፡

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ካቤኒያቸውን ይፋ አድርገው በህዝብ እንደራሴው ምክር ቤት አጸድቀዋል፡፡ አዲሱ ካቢኔ የተቃዋሚዎች ወገን የተካተተበት መሆኑ አዲስ ባህል አድርጎታል፡፡ በአዲሱ ካቢኔ የተካተቱት ሰዎች መካተታቸው ለምን የሚልም መካተታቸው በጄ ብሎ የተቀበለም አለ፡፡
አነጋጋሪ ሆኖ የዋለው የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ነው፡፡
ሰውዬው የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ከተገለጸ በኋላ ቅር ብሎኛል ባዮም ደስታውን ገላጩም የየራሱን ሀሳብ አስፍሯል፡፡
አንድ የፓርላማ አባልና የአዲስ አበባ ተወካይ ተናገሩት የተባለው ነገር ወቃሽም ነቃሽም በዝቶበት በአናቱ ጥቂት ደጋፊዎችን ደስ አሰኝቶ የማህበራዊ ሚዲያው መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል፡፡
አንድ የምንግባባበት እውነት ቢኖር ወይዘሮ ገነት የመሩትን እንዴት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ብሎ መጠየቅ ነውር የለውም፡፡ የእውነተኛ ተቃርኖዎች ማሳያ የአዲስ አበቤ ፖለቲካ ጉዲት ብሎ በቅጽል ስም የሚጠራቸው ወይዘሮ ገነት እና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ናቸው፡፡
አንድ ሰው ቢፈልግም ባይፈልግም የአንዳቸው ወዳጅ ከሆነ የሌላቸው ፍጹም ተቃራኒ አብጠልጣይ ይሆን ዘንድ ሃቅ ያስገድደዋል፡፡ ሁለቱንም እኩል ማድነቅ አይቻልም፡፡ ፕሮፌሰር ብርሃኑ መለስን ከመስደብ ባለፈ በምርጫ ታግለው ሲያቅታቸው ደግሞ በርሃ ወርጄ እንደመጣበት ልምጣ ያሉ ትህነግ ጠል ናቸው፡፡
ወይዘሮ ገነት ዶክተር ነጋሶ መለስ ዜናዊን መንግስቱን መሰልከኝ አለ ብለው ስቅስቅ ብለው ያለቀሱ ከለውጥ በኋላ ጭምር የመቀሌ ፖለቲካና መንፈስ አልለቅ ብሏቸው የነበረ አፍቃሪ ትህነግ ናቸው፡፡
ጉዳዩ እሱ አይደለም፡፡
እንደ ሰለጠነ እና የመንግስት ፖሊሲ ሥርዓት ዓላማና ግብ ጠንቅቆ እንደሚረዳ ወገን ትውልድ በገደለ የትምህርት ፖሊሲ ውስጥ የወይዘሮ ገነት ሚና የግል ድርሻ ብቻ ይመስል ከፍ ብሎ የብቻ ተወቃሽ የሆኑበትን አግባብ መኮነን ይቻል ይሆናል፤ ሴትየዋን ግን ከፕሮፌሰሩ ማወዳደር የዓለም ትልቁ ቀልድ ነው፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑን በትግል ህይወቱ፣ በፖለቲካ አቋሙ፣ በመሰረተው ፓርቲ መርህና ዓላማ፣ ተናግሮት አልያም አድርጎት ነበር በሚባል ጉዳይ መደገፍም መቃወምም የግል መብት ነው፡፡ በትምህርት ህልውና የሚያምን ፊደል የቆጠረ ግን በፕሮፌሰሩ ተምሮ እዚህ መድረስ ጥያቄ ያነሳል የሚል እምነት የለኝም፡፡
ፕሮፌሰሩ ቢያንስ የእከሌ ብሔር ቁጥሩ አነሰ ተብሎ ፕሮፍ በሚል ማዕረግ እንዲጠራ ሰፈር ውስጥ የጻፈው የጥናት ወረቀት ተቆጥሮለት ፕሮፌሰር የተባለ አይደለም፡፡
የእኛ መንግስት ለሀገራችን ስም ከሚጨነቀው በላይ ለዩኒቨርሲቲያቸው ስም ከሚጨነቁ ሀገራት ያገኘው ማዕረግ ነው፡፡
ፖለቲካችንም ሆነ ነቆራችን አንዳንዴ ፊደል ያልቆጠረ ይሆንና ፊደል ለቆጠረም ግራ ሆኖ ያልፋል፡፡ ሰውዬው ረዥም ነው ስንል ግን ያነክሳል እየተባባልን መቼ ድረስ ዘልቀን መግባባት እንደምንችል ግራ አጋቢ ነው፡፡
አንድም ቀን የፕሮፌሰሩ የፖለቲካ ተቃራኒዎች እውቀቱና ተምሮ እዚህ መድረሱ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ የሚል ስጋት አልነበረኝም፡፡ ምክንያቱም ዓለም አቀፋዊ እውነት በሰፈር አሉባልታ ይፈተናል ብዬ አላስብምና፤ ለማንኛውም ፕሮፌሰሩ ለወደዷቸውም ለጠሏቸው ሀገር የትምህርት ዘርፍ ትንሳኤ እንዲሆኑ እመኛለሁ፤ ስኬታቸው ከእሳቸው በላይ ለሁለቱም ጠቃሚ ነውና፤

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top