Connect with us

“ኢትዮጵያም አገባች፣ አፍሪካም ዳረች፤

"ኢትዮጵያም አገባች፣ አፍሪካም ዳረች፤
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

“ኢትዮጵያም አገባች፣ አፍሪካም ዳረች፤

“ኢትዮጵያም አገባች፣ አፍሪካም ዳረች፤

እንግዲህ ጁንታዋ ብቻዋን ቀረች!”

(ስናፍቅሽ አዲስ -ድሬቲዩብ)

መቼም ይሄንን እውነት ተንቤን ዋሻ ውስጥ ተደብቆ መካድ አይቻልም፡፡ የሆነው ነገር ሁሉ የሆነው ዓለም እያየና እየሰማ በአደባባይ ነው፡፡ ያልተጭበረበረ ምርጫ ተአማኒነት የለውም የሚለው እምነታችሁ ምን ያህል ጽኑ እንደሆነ ፍትሐዊ ምርጫችንን ስትጠራጠሩት አውቀናል፡፡

ያው እንደሰማችሁት ኢትዮጵያ አዲስ መንግሥት መስርታለች፡፡ የተመሰረተው መንግስት ኮሮጆ ገልብጦና አዲስ አበባ ላይ አጋዚ በትኖ ቤተ መንግስት የመጣ ስላልሆነ በድብቅ ስልጣኑን መያዝ አልፈለገም፤ እናንተም ሆነ የኢትዮጵያ ጠላቶች እያያችሁ አዲስ አበባ ሲመት ተደግሶባታል፡፡

ለዓለም የነገራችሁትና ከጉቦ ጋር ያቀበላችሁት መረጃ ዶክተር አብይ ስልጣኑን የያዘው አጭበርብሮ እንደሆነና አምባገነን የሚል ስም እንደለጠፋችሁበት ነበር ግን አደባባይ እውነት ይዞ ወጣ፡፡ ኢትዮጵያ ለአዲሱና በፍቃዷ ወንበር ለሰጠችው መሪ ስትዳር እንደ እናት አፍሪቃ ቆማ አየች፡፡ ነውር የሌለበት ሹመት ስለሆነ አደባባይ ታየ፡፡

ዛሬም እልሃችሁን በንጹህ ነፍስ፣ ኢትዮጵያን ስለማጥፋት በሚያስብ እኩይ ሀሳብና ጨለማ በዋጠው ስሜት ልታበርዱት ትሞክሩ ይሆናል ግን የትም አይደርስም፡፡ መንግስት ያለን ህዝቦች ሆነናል፡፡ ያፈረሳችሁትን መንግስት በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ዳግም አፍሪካ እያየች ገንብተነዋል፡፡

እናንተ እንደምትሏት ሳይሆን አፍሪካ የአፍሪካ መሪዎች እንዳሏት እናት ሀገር ናት፡፡ ነጻነትን የወለደች እናት ሀገር መሆኗን ከኢቢሲ ፕሮፖጋንዳ ሳይሆን ከአፍሪካውያኑ መሪዎች አፍ ሰምታችኋል፡፡ የምትጠሉትን ስም ሲያወድሱትና በአደባባይ እናት የምትባል ሀገር መሆኗን ሲመሰክሩ አድምጣችኋል፡፡

ብዙ ምክንያቶች ብዙ ወሬና ሀሜት ብዙ ዛሬም የሚቀጥል ድርቅናና ጥላቻ እናይ ይሆናል፤ አደባባይ እውን የሆነውን እውነት በአደባባይ መካድና ምስል መቀየር ባህሪያችሁ ሆኗል፤ ኢትዮጵያውያን በእናንተ እንዳልተስማማን፣ ሁሉ የተስማማንበትን መንግስት ያለ ግዳጅና ጭቆና በነጻነት መርጠን እንዴት እንኳን ደስ ያለህ እንደምንል አሳይተናችኋል፡፡

እኛ አደባባይ እውነትን ስናነግስ እናንተ በሳይበር የቴሌቨዥን ጣቢያ ፌስ ቡክ ገጽ ተቆጣጥራችሁ ሀሰት ስትለጥፉ ነበር፡፡ እንደ ሀሰታችሁ ብዛት እንኳን ኢትዮጵያ ዓለም ውቅያኖስ ውስጥ በገባ ግን ውሸት አሸንፋ አታውቅም፡፡ ድል ያደረገችውን እድል ዳግም በርሃ ትገባበታለች እንጂ ለህዝብ አትጠቅምበትምና፤

ኢትዮጵያ እንዲህ ተአምር አሳይታለች፤ ቀሪ ፈተናዋ ምናልባትም እናንተን ከወገናችን ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ እስከወዲያኛው ማራገፍ ነው፡፡ እዚህ መንደር አስር እና ሃያ ሲበዛም ሃምሳ ሺህ የፌስ ቡክ አርበኞች በትግራይ ህዝብ ስም ስለተንጫጫችሁ እውነት አትቀይሩም የትግራይ ህዝብ ዛሬም በአፈናና በስቃይ ነው፡፡

በመቀሌ ጎዳናዎች ላይ ጅግጅጋ ሙስጠፌን እንደመረጠችው፣ አልያም ኦሮሚያ ሽመልስን ወይም ሲዳማ ደስታ መርጣ እንደተደሰተችው አፈ ሙዝ ያልተደቀነበት አንድ ለአምስት ተደራጅቶ ስቃዩን የማይበላ ዜጋ መሆን የሚፈልግ ዜጋ እንዲህ ያለውን መልካም አጋጣሚ ይናፍቅባታል፡፡

ጥቂት ሌቦች ሚሊዮን ሀገር ወዳድ ዜጎችን አይወክሉም የሚለው ቃል ውሸት እንዳልሆነ የምታዩበት ቀን ቀርቧል፡፡ እውነት እያሸነፈ ነው፤ እንደ ፕሬዝዳንታችን ንግግር እጆቻችን ደምተው ኢትዮጵያ የምትባልን ጽጌረዳ የሆነች ሀገር ከእጃችን ሳትወጣ አሸብርቀንባት እንቀጥላለን፤ ጠላቶቿ ግን ይጠፋሉ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top