Connect with us

በእኩይ ፖሊሶች ጥፋት ጉዳይ መንግስትን እናመሰግናለን፤

Social media

ህግና ስርዓት

በእኩይ ፖሊሶች ጥፋት ጉዳይ መንግስትን እናመሰግናለን፤

በእኩይ ፖሊሶች ጥፋት ጉዳይ መንግስትን እናመሰግናለን፤ እነሱ እግራቸውን ያነሱት በጨዋዎቹ የፖሊስ አባላት ላይ ጭምር ነበር፡፡
(ስናፍቅሽ አዲስ~ ድሬቲዩብ)

ሁሉም ሰው ተቆጥቶ ብዙ ነገር ያለበት ስለሆነ ነውሩን ደግሞ መግለጹ ደግሞ ከመታመም ያለፈ ትርጉም አልሰጥህ ብሎኛል፡፡ እንዲህ ያሉ ነውረኞች ዛሬም በህብረተሰቡ ውስጥ ብዙ ተሰግስገዋል፡፡ ፖሊሶቹ ምናልባትም የችግሩ ምልክቶች ሆነው እንጂ ሴት በመሆኗ ሳቢያ በውጤት ጠረባ ህይወቷን ያመሰ መምህር ገና አልተጋለጠም፣ የቢሮም አለቃ እንዲሁ፤ የታክሲ ረዳትም ወንድ ቀና ብሎ የማይመለከተው ሴት ስትሆን መልሱም ግልምጫውም ይበዛል፡፡ ይህ ማኅበረሰባዊ ንቅናቄ ይፈልጋል፡፡

ከሁሉ አስቀድሞ አንዳንድ የፖሊስ አባላት እንኳን እነሱን ራስን ፎቶ ማንሳት አይቻልም የሚሉ ጠብ ያለሽ በዳቦዎች ናቸው፡፡ እንዲህ ለማጋለጥ የሚቻልበት እድል በጣም ጠባብ ነው፡፡ ይህንንም ወደፊት አጢኖ ፖሊስ ካሜራ ቀረጽክ እያለ ካልገደልኩ ባይነቱ በዓለም ፖሊስ ሙያ ትልቁ ስህተት እንደሆነ መገለጽ አለበት፡፡

የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች የሰጡትን ምላሽ አለማድነቅ አይቻልም፡፡ ምስሉን ከተመለከቱ በኋላ ቁጣቸውን የገለጹት ኘረዝደንቷ፣ የሰላም ሚኒስትሯና ከንቲባዋ ሰው ሰው የሚሸተው ነገራችው ማሳያ ሆኖብኛል፡፡ እርግጥ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካላወገዘ የአበሻ ቀሚሳቸውን ለብሰው ወጥተው ለምን የማይሉት ብዙ ሴት ሚኒስትሮችና ሹማምንቶችን አፍሬባቸዋለሁ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስም ወዲያው ጉዳዩ በህግ አግባብ እንዲያዝ ለማድረግ የሄደበት ፍጥነት ህዝባዊነት ስለሆነ ክብር ይገባዋል፡፡ ጠቅላይ አቃቤ ህግም ሰኞ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ገልጾልናል፡፡

አንዳንዴ እንዲህ ያሉ ጉዳዮች የአንዲት ሴት ጉዳይ ብቻ አይደለችም፤ በየቤቱ ያለች ሴት እንደተጠረበች፣ እንደተደበደበች መቁጠር አለብን፤ በከተማችን ብዙ የወንጀል ድርጊቶች ይፈጸማሉ፡፡

ጉልበተኛ ነጥቆ ሲበላ እያየን ነው በዚህ መንፈስ አንዲት ሴት መንገድ ላይ ለመንሽ ተብላ እንዲህ መቀጥቀጧ የነውሩ ይፋ መውጫ ቀን ቀርቦ እንጂ እንዲህ ያለ ተግባር ብዙ ቦታ ብዙ ቀን ይፈጸማል፡፡ ከዚህ ቀደም እነ ያሬድ ሹመቴ ያጋለጧቸውና አዛውንት የደበደቡት ፖሊሶችን ማንም አይረሳቸውም፡፡

እንዲህ ያሉ እንኳን ከፖሊስ ከደረሰ ወንድ የማይጠበቅ ተግባር ፈጻሚ የፀጥታ ሃይሎች እንዲህ ያለውን ተግባር ሲፈጽሙ አብረው የሚደበድቡት የህዝባዊውን ሠራዊት ክብርና ስም ነው፡፡ ከዚህች ሴት ጠረባ ጋር አብሮ የተሰነዘረበት ጨዋው ፖሊስና የፀጥታ ሃይል ነው፡፡

ጥፋታቸው ትልቁንና ክቡሩን ሙያ ማዋረድ ነው፤ ምናልባትም የዓለምን ፖሊስነት ሙያና ክብር ሁሉ ያዋረዱ ዓለም አቀፋዊ ጸያፍ ተግባር ፈጻሚዎች ልንላቸው እንችላለን፡፡

አሁን በመንግስት በኩል የታየው እርምጃ በዜጎችና በመንግስት መካከል መተማመንና መግባባት የሚፈጥር ጉዳይ ነው፡፡ ከንቲባዋ ከዚያም አልፎ ሴትየዋን ለመርዳት ቤትና ስራም ለመስጠት ቆርጠዋል፡፡ በእውነቱ አዳነች አበቤን አለማመስገን አይቻልም፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስም እነሱ ሊያጠፉት የሞከሩትን ስምህን በፈጣን እርምጃህ ምኞት ብቻ ስላደረከው ምስጋና ይገባሃል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የዜጎችን ልብ ጸጥታ ያደፈረሱት የጸጥታ ሃይሎች ክስ ውጤቱ ጭምር ትልቅ ዜና ሆኖ የደማውን ህዝብ በማሳወቅ የደረሰበትን መግለጽ አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ እንዳይደገም የሚያደርግ እርምጃ ያስፈልጋል፡፡
***

ፎቶ:- ቪድዮውን የቀረችው ወጣትና ተደብዳቢዋ፣ እንዲሁም በቁጥጥር ስር የዋሉት የፖሊስ አባላት

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top