Connect with us

የኢዜማ አስቸኳይ ጉባዔ

Ethiopiansider.com

ነፃ ሃሳብ

የኢዜማ አስቸኳይ ጉባዔ

የኢዜማ አስቸኳይ ጉባዔ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በቅድመ ምርጫም ወቅት ሆነ ከምርጫው በኋላ ባሉት ጊዜያት በሀገር አንድነት፣ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና የዜጎች በሰላም የመኖር መብት ላይ በሀገራችን ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር በአብሮነት ለመሥራት ፅኑ ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ ባወጣቸው መግለጫዎች እና በተለያዩ መድረኮች ላይ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል።

ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ከየትኛውም ፓርቲዎች በተለየ መልኩ በአብሮነት ለመሥራት ተግባራዊ እንቅስቃሴም ሲያደርግ ቆይቷል።

ገዢው ፓርቲ ምርጫ 2013 መካሄዱን ተከትሎ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን በየደረጃው ባሉ የመንግሥት ሥራ አስፈፃሚ ኃላፊነቶች ለማሳተፍ ውጥን እንዳለው በተለያዩ መድረኮች በአመራሮቹ በኩል መግለፁ ይታወሣል።

ይሕንንም ተከትሎ ለተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በፌደራሉ እና ክልል መንግስት ምስረታ ላይ እንዲሳተፉ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ከነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ኢዜማ አንዱ ነው።

ፓርቲያችንም በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው በሀገር አንድነትና፣ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እና የዜጎች በሰላም መኖር ላይ በጋራ ለመስራት ያለውን መርህ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በቀረበው ጥያቄ ላይ በብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ደረጃ ሲወያይበት ቆይቷል።

በፓርቲው የውስጥ አሰራር መሠረት ይህንን የ‹‹አብረን እንሥራ›› ጥያቄ ለመቀበልም ሆነ ላለመቀበል ኢዜማ በሚታወቅበት ሥልጡን የውስጠ ዴሞክራሲ ሥርዓት መሠረት በአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ጥያቄውን ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ላለችበት ሁኔታም ሆነ ለዘላቂው ዴሞክራያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚኖረውን አስተዋፅዖ እና ሊኖሩት የሚችሉ ተያያዥ ተግዳሮቶች ከግምት በማስገባት የሥራ አስፈፃሚው የሚያቀርበው ምክረ ሀሳብ ላይ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ (መስከረም 22 እና 23 ቀን 2014 ዓ·ም) ከሁሉም የምርጫ ወረዳዎች የተወጣጡ አባላት በሚሳተፉበት የኢዜማ ጠቅላላ ጉባዔ አስቸኳይ ስብሰባ የሚወያይ ይሆናል።(ኢዜማ)

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top