Connect with us

“እነዚህን መጨረስ ነው ያለብን። ካልጨረስናቸው እንቅልፍ አይወስደንም።

"እነዚህን መጨረስ ነው ያለብን። ካልጨረስናቸው እንቅልፍ አይወስደንም። አሁንም መስዋዕትነት እየከፈልን ነው። ካልጨረስናቸው ግን ዋጋ የለውም።"
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

“እነዚህን መጨረስ ነው ያለብን። ካልጨረስናቸው እንቅልፍ አይወስደንም።

“እነዚህን መጨረስ ነው ያለብን። ካልጨረስናቸው እንቅልፍ አይወስደንም። አሁንም መስዋዕትነት እየከፈልን ነው። ካልጨረስናቸው ግን ዋጋ የለውም።” 

የህወሀቱ ሊቀመንበር ደብረጺዮን ሰሞኑን ከተናገረው ንግግር የተወሰደ ነው። 86 ገጽ ባለው ሰነድ ላይ በዝርዝር የተቀመጠው እቅድ የኢትዮጵያን ሰራዊትና ማንኛውንም ሃይል ማጥፋት ለትግራይ ህዝብ(እኛ ለህወሀት ብለን ተረድተነዋል) ህልውና ወሳኝ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል። ደብረጺዮን ሰነዱ ላይ የሰፈረውን የናዚ አዋጅ ሰሞኑን በአደባባይ ደግሞታል። 

ልዩነቱ ሰነዱ የተጻፈ ጊዜ የነበረው ህወሀትና አሁን ያለው የሰማይና የምድርን ያህል መራራቃቸው ነው። ያን ጊዜ ቢያንስ ህወሓት በተዋጊ ሀይል የተደራጀ ነበር። መሳሪያ እስከ ሚሳየል ድረስ የታጠቀ ነበር። ዋና የሚባሉት የፖለቲካና የወታደራዊ መሪዎቹ አንዳቸውም አልጎደሉም። “በምስራቅ አፍሪካ መቺ የሆነ፣ ሰማይ ምድሩን የተቆጣጠረ ሃይል ገንብተናል” ብለው በእብሪት የደነፉበት ወቅት ላይ ነበር ሰነዱን ያዘጋጁት።

አሁን ያ ህወሓት የለም። ተንፍሷል። በወታደራዊ አቅሙ ተንኮታክቷል። ዋናዎቹ የፖለቲካና የወታደራዊ አመራሮቹ ተገድለዋል። ዘብጥያ ወርደዋል። የታጠቀው ሮኬትና ሚሳየል ተደምስሰዋል። ህዝብን ለጦርነት በማሰለፍ የወሰዳቸው እርምጃዎች ጥንካሬውን የሚያሳዩ ፈጽሞ አይደሉም። ህወሓት ተሸንፏል። አሁን የገባበት የእብደት ጦርነት በፖለቲካም ሆነ በወታደራዊ ቁመና የላሸቀና ወደዘላለማዊ ሞቱ በፍጥነት እየገሰገሰ መሆኑን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። 

ታዲያ ደብረጺዮን አሁን ላይ እንዲህ የሚያስደነፋው ምን አቅም ይዞ ነው? ቢይዝስ የአንድን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ጨርሳና አጥፍታ የምትቆም የትግራይ መንግስት እንዴት ልትመጣ ትችላለች? ሰዎቹ እዚያ ከዋሻ በተደበቁ ጊዜ ከውስጣቸው ብዙ እቃዎች ሳይወድቅባቸው አይቀርም። ምናልባት ወደሰውነት የመመለስ ፍላጎት ካላቸው ከተንቤን ዋሻ ስር የወደቁባቸውን ልብና ህሊናቸውን ፈልገው ያግኙት።

የደብረጺዮን ድንፋታ የሽሮን ግንፍልና የሚያስታውስ ነው። ሽሮ ቢገነፍል ከእንጀራ አያልፍም አይደል የሚባለው? አእምሮአቸውን የደፈነው የዘረኝነት መንፈስ መድሃኒት ወደሌለው ክፉ ደዌ ተቀይሮባቸዋል። 110 ሚሊዮን ህዝብ ደጀን የሆነለትን መከላከያ ሰራዊት እንጨርሰዋለን የሚለው ዛቻ፣ ዘረኝነት ወደካንሰር ሲቀየር ከሚታዩ ምልክቶች አንዱ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። ይህ ካንሰር የሚደን አይደለም። 

ሳይገድል አይመለስም። ህወሓት በዚህ ካንሰር በጽኑ ታሟል። እየተሰቃየ ነው። ብቻዬን አልሞትም በሚል የትግራይን ህዝብ ለእልቂት ጋብዟል።

እንግዲህ ምርጫ የለም። የደብረጺዮን የሰሞኑ ድንፋታ በመከላከያ ሰራዊት ልክ ማግኘቱ የማይቀር ነው። ይህን እነደብረጺዮን ያውቁታል። ምላስ አልሞት ብላ እንጂ የመጣባቸውን የህዝብ በትር በሚገባ ተረድተውታል። በእርግጥ ድንፋታውን እንደኑዛዜም መውሰድም ይቻላል። ህወሓት እንኳን መከላከያ ሰራዊቱን ለመጨረስ ይቅርና የራሱንም አመራሮች ከማይቀረው የሞት ቅጣት ለማስጣል የሚያስችል አቅም የለውም። 

አሜሪካን እግር ስር ተደፍቶ የሚነፋረቀው ምናልባት ለአጭር ጊዜም የእድሜ ማራዘሚያ ከተገኘ በሚል እንደሆነ ተረድተናል። ለማንኛውም ህወሀትን ለማዳን እየተደረገ ያለው ርብርብ በቅርቡ መልሱን ያገኛል። ስለ ድርድር የሚያስቡ ወገኖችም ያን ጊዜ አርፈው ይቀመጣሉ።

#መሳይ_መኮንን

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top