ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ሞላ መልካሙ መልዕክት
ለዘመናት የአማራ ህዝብን እና ኢትዮጵያዊነትን በከፋ ጥላቻ ውስጥ ፈረጆ ሊያጠፋን ሲታገል የኖረው አሸባሪው የትግራይ የትህነግ ቡድን እና ተላላኪዎቹ እንደሆኑ በግሃድ ይታወቃል።
በቅርቡ በተለየ “ከአማራ ህዝብ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን” በሚል ከድብቅና የሴራ ትግበራው ወጥቶ በአደባባይ እንደ ዛተው ሁሉ ወደ ክልላችን ተንቀሳቅሶ ህዝባዊ ጥላቻውን ከውጊያ ጀምሮ ሊጥና እንጀራ ሳይቀር የአማራ ህዝብ የሆንን ማንኛውንም ቁስ እና የፋብሪካ ምርት ለመዝረፋ ችሏል።
ያም ሆኖ ሊያከስመውና ሊዘርፈው ያልቻለው የአማራ ህዝብን አይበገሬነትና የኢትዮጵያዊ አንድነታችንን ነው።ለዚህም ምስክሩ በሁሉም ግንባር እየደረሰበት ያለው ሽንፈትና ኪስራ ከጥቅም ውጭ እያደረገው መገኘቱ ነው።
በዚህ የወራዳነትና የከፋ ጭካኔ ተግባራቸው የተነሳ የህዝብና የሰው ፍጡር ለሆነው ሁሉ ክፉ ጠላት መሆናቸውን አሳይተው በሁሉም የሀገራችን አቅጣጫ የማይፈለጉ እንደሆኑ በኢትዮጵያዊያን የአንድነት ድምፅ!ተረጋግጧል።
ይህን ትንግርታዊ ተግባር በፀረ ትህንግ ወረራ
ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን፤ማገር በመሆን የአማራ ልዮ ሀይላችን ለወራሪው የመረዝ ብልቂያጥ በመሆን አረበኞቻችን እና ፤ፋኖዎቻችን የወራሪውን ቋንጃ በመቁረጥ ድል ተቀናጅተዋል።የፖሊስና አድማ በተና ሰራዊታችን ወራሪውንና ሰርጎ ገቡን በመመንጠር አይተኬ ሚና ተጫውተዋል።
ወጣቶቻችን ከሰራዊቱ ጋር ከመቀላቀል ባሻገር ከተማቸውን እና ቀጠናቸውን በመጠበቅ የብረት ካስማ ሆነው24 ስዓት እየተጉ ይገኛሉ።አጠቃላይ ህዝባችን ደግሞ በገንዘቡ በጉልበቱና እና በወኔ ቀስቃሽ ብርቱ ስሜቱ ደጅንነቱን በማሳየት ቀጥሏል።
ለዚህም የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከታላቅ ክብር ጋር ለሁላችሁም ምስጋናውን ያቀርባል።
የቀጣዩና የመጨረሻው የጋራ ሥራችን የሚሆነው በተለይም ወጣቱ ከሱስ የተጠበቀ፤ ስነ-ምግባር የተለባስ ፤እና የሀገር ፍቅርን በሁሉም ዘርፈ በተግባር ያረጋገጠ መሆን ይገባዋል።
ቀጥሎም እስካሁን በአሳየነው የልተከፋፈለ የአንድነት መንፈስ ፤በጦር ግንባርና በደጀንንት በአረጋገጥነው የጋለ ስሜትና ወኔ ቀሪው ሰላማችንን በአስተማማኝ መሰረት ላይ
በማድረስ የተጀመሩ የልማትና ዕድገት፤ ዕቅዳችንን ወደ ተግባር በመለወጥ ፤ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት ፤ለመልካም አስተዳደር እና ለዲሞክራሲ ስርዓት ማበብ እጅ ለእጅ መያያዝ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይሆንም።
በመሆኑም ዛሬ ነገ ሳንል ጎንደርን፣ ክልላችንን እና ኢትዮጵያችን በማሻገር የሴረኛውን የአሸባሬውን የትህነግ ዓላማ ቅዥት በማድረግ
“በመቃብሬ ላይ ነው !”የሚለውን መፈክሩን ለማሳየት ከነሴራው በመቅበር በትህነግ መቃብር ላይ ኢትዮጵያዊነትን እና ብልፅግናዋን አንድናስቀጥል በታልቅ አክብሮት አደራ እላለሁ!
የህልውና ዘመቻችን ድል ቅርብ ነው!
የከፈልነውና አየከፈልነው ያለው
መስዕዋትነት ዋጋ አለው!
ብሎም ሁላችንም በወስድነው የሀገርና የህዝብ ሃላፊነት፣ በተሰማራንበት ሞያ በታማኝነት እና ትጋት ህዝባችንን በማገልገል የህልውና ዘመቻው ደጅን በመሆን የሀገራችንን ፍቅር በተግባር መግለፅ ይገባናል።
አዲሱ ዓመት
የድል፣ የሰለም፣ የፍቅር ፣የልማትና ብልፅግና አዲስ እመት እንዲሆንልን ለመላው የክልላችን ህዝብ እንዲሁም ለ ኢትዮጵያችን እንመኛል !
መልካም አዲስ ዓመት!
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት
ጎንደር!
ሞት !ለ አማራ ህዝብና ለኢትዮጵያዊነት ጠላት ለሆነው አሽባሪው ትህነግና ተላላኪዎቹ!
ድል !ለአማራ ህዝብና ለታላቋ ኢትዮጵያችን!