Connect with us

በሁለታችን ጉዳይ በዝግ መክረናል የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሬም ሳዲቅ

Social media

ዜና

በሁለታችን ጉዳይ በዝግ መክረናል የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሬም ሳዲቅ

በሁለታችን ጉዳይ በዝግ መክረናል የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሬም ሳዲቅ
.
የአረብ ሊግ ምክርቤት 156ኛው ስብሰባ ነገ ይጀመራል። የሊግ አባል አገሮች ተወካዮች ለስብሰባ ካይር እየገቡ ነው። መሬም ግን ትናንት ነው ካይሮ የገባችው። መሬም በፌስቡክ ገጿ ላይ እኔና ሳሚ ሽኩሪ የግብፅና የሱዳን ጉዳይ በተመለከተ በዝግ መክረናል ብላ ፅፋለች።
.
የሁለቱን ዜና ካዳመጠ ቡሀላ ዘ_ጆርዳን ታየምስ እንዲህ ሲል ፅፏል። የሁለቱ አገሮች ውጭ ጉዳይ በዝግ መክረዋል። መምከርም አለባቸው። ጀነራል ቡረሀን ከአራት ቀን በፊት ግብፅን ያስቆጣ ንግግር አድርጓል። የሀላይቭና የሻላቲን ወንድሞቻችን መቼም አንረሳችሁም ብሎ ተናግሯል። በዚህ ንግግሩ የግብፅ ጋዜጠኞች የስድብ ናዳ እያወረዱበት ነው። በርግጥ ቡሀራን ማይክራፎን ከያዘ
የተመቸውን ለመዘርጠጥ አይቸገርም። መፎግላት ልምዱ ነው ይሉታል የሀገሩ ልጆች።
.
የመሬምና የሳሚ ዝግ ውይይት፣ ሁለት ነገሮችን የያዘ ነው። አንዱ የአረብ ሊግ በኢትዮጵያ ላይ ከነሱ ጎን ቆመ የሆነ ንግግር እንዲናገርላቸው ከወዲሁ አቋማቸውን አንድ ለማድረግ ነው። ሁለተኛው የቡራሀን ንግግር በተመለከተ ነው። በነገራችን ላይ ግብፅና ሱዳን ሰሞውኑን የናይል ዘበኞች የሚል ወታደራዊ ልምምድ በገዳሪፍ ግዛት እና በከሰላ ግዛት ያደርጋሉ።

በነዚህ ጉዳዮችም ዙሪያ መምከራቸውን ነው ዘጆርዳን ታየምስ የፃፈው። ሰሞውኑ የግብፅን ታንክ የጫኑ መኪኖች በካርቱም አቋርጠው ወደ ገዳሪፍ ግዛት ሲገቡ የታዩትም ለዚሁ ነው።
.
7 ሚሊየን ተከታይ ያለው አል አለሚ ጋዜጣ በበኩሉ በዚህ ዙሪያ ረዘም ያለ ትንታኔን አቅርቦ የመሬምንና የአለም የጤና ድርጅት ሊቀመንበሩ ቴዎድሮስ አድሀኖምን ድብቅ ሴራ እንደሚከተለው ከትቦታል።

የመሬምና የሳሚ ዝግ ውይይት የታወቀ ነው ። መሬም ሰው እለለበት ቦታ ብቻችንን ተወያየን ብላ መፃፏ ቢያስገርምም ማን ፎቶ እንዳነሳሳቸው ግን አል አለሚ ያውቃል፤ የአል አለሚው ጦማሪ ካሊድ እብራሂም፤ መሬም የቴዎድሮስ አጀንዳ አስፈፃሚ ሱዳናዊት ናት። ከሱጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ አብረው የሚሰሩት ድብቅ ስራ አለ። ሰውየው የህወሓት የውጭ ግንኙነት ቁልፍ ተጨዋች ነው። ለዛም ነው መሬም ከሱጋር ሰው የማያቀው ግንኙነት የኖራት።

አንቱ የተባሉ የትግራይ አርቲስቶችና ጀነራሎች ደህንነቶች ካርቱም ባለው የመሬም ፅፈት ቤት እንደፈለጉ ገብተው ይወጣሉ። ባለ ጉዳይ ሱዳኒዎች ራሱ እንደዛ ፍልስስ ብለው ዘንጠው አይገቡም።

ለነሱ ግን በሯ ክፍት ነው። ይህ የመሬም የተደበቀ ስራ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች ላይ መሬም ከሌሎች አገሮች ጋር እጇን አስገብታ ማቡካት ከጀመረች ቆይታለች። እራሷ ፍቃድ የሰጠችው የኢትዮጵያ አየር መንግስት በ2019 ሱዳን ከሩሲያ የገዛችውን ለአደን የሚሆን መሳሪያ ካርቱም ይዞ ሲመጣ አየር መንገዱ ፍቃድ የለውም ወንጀለኛ ነው እያለች ስሙ እንዲጠፋ ህብቡ የተሳሳተ መረጃ የሰችውም እሷ ናት።

በዳርፉር የተሰማራው የኢትዩጵያ ሰላም አስከባሪ ሀይል ይውጣ ብሎ የጠየቀ የሱዳን ባለስልጣናት ሳይኖር መሬም ናት ከግብፅ ጋር መክራ እንደወጣ ያደረግችው።
.
በአል አለሚ ዜና የተበሳጨችው መሬም ለሱዳን 24 የዜና አገልግሎት፣ በሰጠችው ቃል፤ አል አለሚዎች የተባሉ የቡና አጣሪ ስብስቦች ስሜን እንደፈለጉ እንዲያጠፉት የፈቀደላቸው የሱዳን የፀጥታ መዋቅር ነው ያለች ሲሆን፤ አያይዛም ወንጀለኛ ጋዜጠኛ ስለሚፅፈው ነገር ብዙም ትኩረት ማድረግ አያስፈልግም ብላለች። ወንጀለኛ የምትለው የአል አለሚውን ጋዜጠኛ ካሊድ ሙሳን ነው። ካሊድ ሙሳ በሌለበት የ12 አመት የእስር ፍርድ ተፈርዶበት ዛሬም እየተፈለገ ያለ ጋዜጠኛ ነው።

ከዚህ በፊት መሬም ዱባይ ሄዳ ለአንድ ጫማ 2000 ዶላር ክፍላ መግዛቷን ያጋለጣት ይሄው የምትፈራው ካሊድ ነበር፤ መሬም በጋዜጠኛው ተባሳጭታ አንድ አይኑን በካሮቶን አስሮ የሚፅፍ ጋዜጠኛ፤ ስለኔ ምንም ነገር ቢፅፍ ሁሉንም እንደ እውነት አትውሰዳት እኔ አይደለም የ2000
ዶላር ጫማ የ5ሺ ዶላር ጫማ ገዝቼ የመልበስ መብት አለኝ ብላ ነበር። በርግጥ ልጁ መሬምን ከነ ነውሯ ጭምቅ አድርጎ ነው ለአለም ገበያ የሚያቀባት።

በበሳል ብዕሩና ቅኔ በተሞላበት ጉንተላው የሚታወቀው ጋዜጠኛ ካሊድ፤
የመሀመድ ጋዳፊን የግድያ ሴራ መርምሮ ለአለም ያደረሰው እሱ የሚመራው አል አለሚ ጋዜጣ ነበር። በዛን ግዜ ነበር አል አለሚ በነ አልጀዚራና ሲኤንኤን ቢቢሲ አንደበት ገብቶ ተፅዕኖ ፈጣሪ የአፍሪካ ጋዜጣ ሆኖ የቀረበው።

ትርጉምና ትንታኔ
ሱሌማን አብደላ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top