Connect with us

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተላለፈ ጥሪ

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተላለፈ ጥሪ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 

ነፃ ሃሳብ

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተላለፈ ጥሪ

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተላለፈ ጥሪ

የአሸባሪውና ተስፋፊው የትሕነግ ቡድን  ጦርነት  ከከፈተብን  ዕለት ጀምሮ  ገንዘባችሁን፣ ጊዜያችሁንና  ጉልበታችሁን ሳትሰስቱ ለኅልውና ዘመቻው ላዋላችሁ ሁሉ የክልሉ መንግሥት ላቅ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።

የተከፈተብን  ጦርነት የኅልውና ነው፡፡ የኅልውና ጦርነት ነው ካስባሉት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከልም  አሸባሪ ትሕነግ ለኅሊና የሚከብድ፤ ለሰሚ የሚዘገንን በቀልና ጭካኔ የተጫነው አረመኔነትና የክፋት ሁሉ ጥግ  በሕዝባችን ላይ እያደረሰ መሆኑ ነው።  ስለሆነም ይህ ጊዜ የተቃጣብንን የኅልውና አደጋ በመመከት ጠላታችንን ለመቅበርና ኅልውናችንን ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ በጋራ የምንቆምበት ወሳኝ ወቅት ነው፡፡  

ስለሆነም  ዕድሜያችሁና ጤንነታችሁ  ለደጀንነትም ሆነ ለወታደርነት ብቁ የሆነ የመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የመሰናዶና ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ተማሪዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት/የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ምሩቃን፣ መምህራንና መላው ወጣቶች በያላችሁበት የክልሉ አካባቢዎች ባለው አደረጃጀት መሰረት ጠላትን ለመቅበር እንድትከቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን። 

በመሆኑም፡- 

1ኛ. የሀገር መከላከያ ሰራዊታችንንና ልዩ ኃይላችንን በመቀላቀልና በማጠናከር እንዲሁም ደጋፊ ሚና በመጫወት የየድርሻችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን። 

2ኛ. በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጀመርነው የኅልውና ትግል ሳይደናቀፍ በአሸናፊነት እንዲቋጭ የሚጠበቅባችሁን ሁሉ እስከ ሕይወት መስእዋትነት ድረስ ሳትሰስቱ እንድታበረክቱ ከአደራ ጋር ጥሪያችንን እናቀርባለን። 

3ኛ. የትሕነግ ወራሪ፣ ጨፍጫፊና ዘራፊ ኃይል በወረራ በያዛቸው የአማራና የአፋር ግዛቶች ሁሉ በሰፊው ሕዝብና በአርሶ አደሩ የወልና የግል ኃብት ላይ እየፈፀመ ያለው ዘረፋና ውድመት ፣ የአርሶ አደሩን ሕፃናት ልጆችና የአባዎራዎችን ሕጋዊ ሚስቶች አስገድደው እየደፈሩ መሆኑ፣ የኃይማኖት አባቶችን፣ የአገር ሽማግሌዎችን፣ ወጣቶችን እንደ አውሬ እያደኑ በመጨፍጨፍ እና የኃይማኖት ተቋማትን በመዝረፍና በማውደም ላይ መሆናቸውን በመገንዘብ ለውድ ወገኖቻችንም ሆነ በአካባቢያችን የሚገኙ ተቋማትን ከውድመት ለመታደግ ሁላችንም ወታደሮች ሁነን አካባቢያችንን ልንጠብቅና ከዘራፊ ልንከላከል ይገባል፡፡ 

ስለሆነም የተከበራችሁ ወጣቶች ሁሉንም የተግባቦት አማራጮች በመጠቀም ለመላው የአማራ አርሶ አደርና የከተማ ነዋሪ፥ በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ሞት እና እንግልት እንድታሳውቁ እያሳሰብን ይህን ሁሉ ግፍ እየፈፀመ ያለ ወራሪ፣ ጨፍጫፊና ዘራፊ ኃይል የአርሶ አደሩን ቀዬ ረግጦ በሰላም እንዳያልፍ ልታደርጉ ይገባል፡፡ ሕዝባችን ከአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ጋር በመተባበር ጠላትን በየደረሰበት እንዲደመስስ ወጣቶች እንደመደበኛ ሥራ ቆጥራችሁ ሰፊውን ሕዝብ  እንድትቀሰቅሱና እንድታነቁ  የክልሉ መንግሥት በድጋሚ ጥሪ ያቀርብላችኋል። 

በሕይወታችን ላይ የተቃጣውን የኅልውና አደጋ በሕዝባዊ ትግል እንቀለብሰዋለን!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 

ባሕር ዳር

ነሐሴ 24፣2013 ዓ.ም.

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top