Connect with us

በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

ከአማራ ህዝብ እና ከሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ጎን በመሠለፍ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፡- የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል
የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት

ዜና

በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

ከአማራ ህዝብ እና ከሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ጎን በመሠለፍ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፡- የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከለውጡ ማግሥት አንስቶ የህዝቦችን ፍትሃዊ የልማት፣ የሠላምና የዴሞክራሲ ሥርዓት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሪፎርሞችን በማካሄድ ትርጉም ያላቸው ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡

በሀገራችን አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ከተጀመረበት ማግስት አንስቶ ባለፉት ሦስት አመታት ውስጥ የተጀመረው ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ እጅግ የሚበረታታ ውጤት የተመዘገበበትና አካታች እንደነበር በተለይ ለክልላችን ማህበረሰቦች ግልጽ ነው፡፡

በአንፃሩ በሸፍጥ እና በሴራ ፖለቲካ የረዥም ዓመታት ልምድ ያካበተው የህወሃት ሽብርተኛ ቡድን  ላለፉት ዓመታት ክልላችንን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶችንና በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶችን ከማቀናበር ፣ ከመደገፍ እና በቀጥታ ከመሳተፍ ባለፈ የሀገራችን መከታና የህዝባችን አለኝታ በሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን ላይ የክህደት ጥቃት በመፈፀም ሉዐላዊነታችንንም ጭምር አደጋ ውስጥ የጣለ የሽብር ተግባር ፈፅሟል፡፡

ህልውናውን ማቆየት የሚችለው  በግጭት ብቻ እንደሆነ አጥብቆ የሚያምነው ይህ ጠብመንጃ አምላኪ ቡድን በቅርቡ ለሠላም ሲባል የተከፈተለትን በር ጥሶ በመግባት የሽብር ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የሽብር ቡድኑ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተለያዩ አካባቢዎችን በመውረር በንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ ሳያንስ ህፃናትን ጠብመንጃ በማስታጠቅ እና በጦርነት እንዲማገዱ በማድረግ እጅግ አስነዋሪ ተግባር በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡

ይህ የሽብር ቡድን ክልላችንን እንደሁለተኛ የሽብር ማስፈፀሚያ ግንባር በመቁጠር ተላላኪዎችን በማሰልጠንና በመደገፍ የበርካታ ንጹሃንን ህይወት እንዲቀጠፍና አለመረጋጋት እንዲሰፍን በማድረግ ሀገር የማፍረስ እና ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ዓላማውን በተጨባጭ ከማረጋገጥ ባለፈ ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚወስደውን መንገድ ለማስዘጋት እና የግንባታ ሂደቱን ለማስተጓጎል አበክሮ በመሥራት የተለመደ የተላላኪነት ተግባሩን ለመፈፀም ሲውተረተር ቆይቷል፡፡

በመሆኑን ይህ ሽብርተኛ ቡድን ራሱ በለኮሰው ዕሳት ተቃጥሎ ማለቁ የማይቀር የመሆኑ ዕውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየተወሰደ ያለውን ሀገራዊ እርምጃ የክልላችን መንግሥትና ህዝብ አጥብቀው ከመደገፍ ባሻገር ከአማራ ህዝብ እና ከሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ጎን በመሠለፍ የሚጠበቅባቸውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡

መላ የክልላችን ህዝቦች በህወሃትና በተላላኪዎቹ የተዛባ የፈጠራ ትርክት እና የሀሰት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሳትበገሩ ወንድማማቻዊ አንድነታችሁን ሀገራዊ ህብረታችሁን ይበልጥ በማጥበቅ የአካባቢያችሁን ሠላም ከማስጠበቅ ባሻገር  ሀገራዊ ኃላፊነታችሁን በላቀ ሀገራዊ ሥሜት እንድትወጡ የክልሉ መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የባንዳዎችን ሴራና ተንኮል በማክሸፍ ሀገራዊ አንድነታችን እና ሉዐላዊነታችንን የበለጠ ይጠናከራል!!

የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት

ሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓ.ም

አሶሳ

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top