Connect with us

ለአሸባሪው ህወሓት ሲሰሩ በነበሩ 27 የሰራዊት አባላት ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ችሎት ተሰየመ

ለአሸባሪው ህወሓት ሲሰሩ በነበሩ 27 የሰራዊት አባላት ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ችሎት ተሰየመ
Ethiopian News Agency

ዜና

ለአሸባሪው ህወሓት ሲሰሩ በነበሩ 27 የሰራዊት አባላት ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ችሎት ተሰየመ

ለአሸባሪው ህወሓት ሲሰሩ በነበሩ 27 የሰራዊት አባላት ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ችሎት ተሰየመ

 ለአሸባሪው ህወሓት ሲሰሩ በነበሩና ክስ በተመሰረተባቸው 27 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት በደቡብ ዕዝ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ችሎት ተሰየመ።

የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 293 ንኡስ አንቀጽ አንድን  በመተላለፍ የሀገር መከላከያ ተቋምን የአገልግሎት ደንብ በመጣስ እንዲሁም አንቀጽ 32 ንኡስ አንቀጽ አንድ (ሀ) እና አንቀጽ 247(ሐ) ሰራዊቱ ወደ ጠላት እንዲኮበልል በማደፋፈርና በማነሳሳት ኮሎኔል ካሳ ሀብቱ፣ ኮሎኔል ሀጎስ አሰፋና ሌተናር ኮሎኔል ሀይላይ ገብሩ በዋና ወንጀል አድራጊነት  ክስ የተመሰረተባቸው ይገኙበታል።

 ተከሳሾቹ የገቡትን ቃል ኪዳን ወደጎን በመተው የሰራዊቱን እንቅስቃሴ አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ሲያከናውኑ መቆየታቸው በችሎቱ ተነስቷል።

 የሰራዊቱን ልዩ ልዩ ምስጢራዊ ሰነዶች ለትግራይ ልዩ ሃይል አሳልፈው በመስጠት፣ የሰራዊቱን ልዩ ልዩ ትጥቆች የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዳይሰጡ ምስጢራዊ ቡድን በማደራጀትና መሳሪያዎቹን በማበላሸት ስራ ላይ ተጠምደው እንደነበር በችሎቱ ተገልጿል።

 ተከሳሾቹ ለግዳጅ የተዘጋጁ መሳሪያዎች የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዳይሰጡ በማድረግ፣ ሰራዊቱ ሽብርተኛውን የሸኔ አባላትን ለመደምሰስ በሚንቀሳቀስበት ዕለት ቀድሞ መረጃ በመስጠትና ተልዕኮው ተፈላጊውን ውጤት እንዳያገኝ በማድረግ፣ የሰራዊቱን ምስጢራዊ ክንዋኔዎች ለሽብርተኛው አካል ማድረስም የፈፀሙት የወንጀል ተግባር መሆኑ ችሎቱ ተመልክቷል።

 የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ወደጎን በመተው ከሽብርተኛው አካል የሚሰጣቸውን ድብቅ አጀንዳ መፈፀም በሚያስችላቸው አካሄድ ላይ ብቻ ማተኮር፣ የትግራይ ልዩ ሃይሎች “የብልፅግና ወታደሮችን” ድል እያደረጉ ነው የሚል ሽብር መንዛትም ጥፋተኛ ያስባላቸው መሆኑ ተመልክቷል።

በዚህም ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በ24 መዝገብ በተከሰሱ  27 የሰራዊቱ አባላት ላይ በደቡብ ዕዝ መምሪያ የተሰየመው ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡( ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top