Connect with us

ከትግል ዘመን እስከ መንግሥትነት፤ ከመንግሥትነት እስከ አማጺነት-ከባንክ ዘረፋ ያልተላቀቀ ታሪክ! 

ከትግል ዘመን እስከ መንግሥትነት፤ ከመንግሥትነት እስከ አማጺነት-ከባንክ ዘረፋ ያልተላቀቀ ታሪክ!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ከትግል ዘመን እስከ መንግሥትነት፤ ከመንግሥትነት እስከ አማጺነት-ከባንክ ዘረፋ ያልተላቀቀ ታሪክ! 

ከትግል ዘመን እስከ መንግሥትነት፤ ከመንግሥትነት እስከ አማጺነት-ከባንክ ዘረፋ ያልተላቀቀ ታሪክ! 

(ስናፍቅሽ አዲስ -ድሬቲዩብ)

የንፋስ መውጫ ከተማን ውድመት ተመለከትን፤ ከእያንዳንዱ ገበሬ ጓዳ እስከ ከተሞች መሰረተ ልማት ስርቆትና ውድመት የተፈጸመው ታሪክ ጭቆናን አመልጣለሁ ብሎ ፕሮፖጋንዳ ከሚነዛ ሳይሆን በተቃራኒው ካልጨቆንኩ ሀገር ይውደም ብሎ ከማለ የሚጠበቅ ነው፡፡

ትህነግ ከትግል ዘመን የአክሱም ባንክ ዝርፊያዋ ጀምሮ ባንክን የማራቆት ፖለቲካ መገለጫዋ ሆኖ የኖረ ነው፡፡ አሁን የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ ከየባንኩ በአስገዳጅ የፖለቲካ ያለ በቂ ማስያዣ ተወስደው የነበሩ ብድሮች ቀልጠው ቀርተዋል፡፡

ንግድ ባንክ የብዙ የትህነግ ነጋዴዎችን ሀብት ለጨረታ ማቅረቡንም እየሰማን ነው፡፡ አስገራሚው ነገር ባለሀብቶቹ የገቡበት አልታወቀም፤ ፓርቲያቸው ቤተ መንግስቱን ሲለቅ እነሱ ንግዳቸውን ትተው ፈረጠጡ፤ አስቀድሞ በባንክ ፖለቲካ የካበተ ገንዘብ መያዣ የተባለውም ንብረት የባንክ እዳና ደመወዝ ያልተከፈለው ሰራተኛ ጥሪት ሆነ፡፡

የትህነግን የባንክ ፖለቲካ ለመረዳት በትግል ዘመን ምዕራፏ አክሱም ከተማ ከሚገኘው የመንግስት ባንክ የዘረፈችው ገንዘብ ታሪክ መነሻዋ ብቻ ሆኖ አልቀረም፤ የልማት ባንክ ብዙ ቢሊዮን ብሮች መንግስት ሆና ሀገር እጇ ሲገባ የመዘበረችው ጥሪት ነው፡፡

እርግጥ ነው፤ እታገልለታለሁ ከሚለው ወገን የእርዳታ እህል ሽያጭ መሳሪያ የሚገዛ ፓርቲ ከሚጠላትና ሊያጠፋት ሲዖል ድረስ መውረድ አለብኝ ከሚላት ሀገር ባንክ ቢመዘብር ጽድቁ እንጂ ነውሩ አይሆንም፡፡

የትህነግ የሥልጣን ዘመን የባንክ ፖለቲካ ስለመሆኑ ዓለም ከነገረን የገባበት ያልታወቀ በቢሊዮን የሚቆጠር የኮበለለ ዶላር ባሻገር የኮንትሮባንድ ንግዱ አንድ ማሳያ ነው፡፡ ይሄንን ጽሁፍ የሚያነቡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአካባቢያቸው ስላለው ኮንትሮባንድ ነጋዴ ጥቂት ቢያስቡ እውነቱን ያለ ድካም ያገኙታል፡፡

ዋናው የባንክ ፖለቲካ ዛሬም መሳሪያ እስከማስነሳት ያደረሰ፤ ከቤተ መንግስት መልሶ ተንቤን ዋሻ የከተተ ጥቅም በስልጣን የተገኘበት ዘርፍ ነው፡፡ እንደ ልብ መበደር፣ ኮንትሮባንድ መነገድ ሀገር መመዝበር፤ የዚህ ድምር ውጤት ከፍቶ ከፍቶ ሰላማዊ ዜጎች ለጥቂቶች ምቾት ተላልፈው የተሰጡበት ምዕራፍ ላይ አድርሶናል፡፡

ግን ትህነግ አሁንም ከባንክ ፖለቲካ አልወጣችም፡፡ ኢትዮጵያን የምትመራ ገዢው ፓርቲ የሚለውን ስሟን ወደ አማጺነት ቀይራም አሁንም የምትታማው፣ ስሟ የሚነሳውና ትውልድ ስለ እሷ እንዲሰማ የሚደረገው ከባንክ ጋር ተቆራኝቶ ነው፡፡

አማጺዋ ትህነግ ከተደበቀችበት ዋሻ ከወጣች በኋላ ትግራይን ጨምሮ በወረረቻቸው መሬቶች የመጀመሪያ ስራዋ ባንክ ፈልጋ መዝረፍ ነው፡፡ ንፋስ መውጫ ኤትኤም ማሽን ሳይቀር ፈንቅላ ብር ፍለጋ የማሳነችበት ነውርም ይሄንን ያሳያል፡፡

አማጺዋ ትህነግ ነጻ አውጪ ነኝ ብላ እንደምትታገልበት ዘመኗ የራሷን ታሪክ አሁን ደግማዋለች፡፡ ዛሬም ባንክ ቤት ፎቶ ተነስታ ከባንክ የተቆራኘ ፍቅሯን ገልጻ፣ ባንክ ዘርፋ ትሄዳለች፡፡ በሌላ በኩል ዛሬም እንደ መንግስትነት ዘመኗ የትግሏ ስልት ዘረፋ ነው፡፡ ዛሬም ለመብትና ለጭቆና አደርገዋለሁ የምትለውን ትግል ባንክ ቤት ጎራ ሳትል፣ ሳትዘርፍና ሳትመዘብር እንደማታሳካው በተጨባጭ አሳምናናለች፡፡

የትህነግ ፖለቲካ ከትግል ዘመን እስከ መንግስትነት ከዚያም እስከ ዳግም የአማጺነት ህይወት በባንክ ፖለቲካ የተቃኘ ነው፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top