Connect with us

የአንካራና አዲስ አበባ የውሀ ስምምነት የካይሮ እራስ ምታት…..

የአንካራና አዲስ አበባ የውሀ ስምምነት የካይሮ እራስ ምታት…..
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የአንካራና አዲስ አበባ የውሀ ስምምነት የካይሮ እራስ ምታት…..

የአንካራና አዲስ አበባ የውሀ ስምምነት የካይሮ እራስ ምታት…..

(እስክንድር ከበደ – ድሬቲዩብ)

በአለማችን አራት ዋና ዋና ጥንታዊ የወንዝ ሸለቆ ሥልጣኔዎች ይጠቀሳሉ:: በአለማችን የመጀመሪያው ሥልጣኔ በ3500 B.C በመካከለኛው ምስራቅ የሚፈሱት የጢግሮስና የኤፍራጠስ ወንዞች ዳርቻ አካባቢ መፈጠሩ ይነገራል:: 

ይህ የ”ሜሶፖታሚያ” ሥልጣኔ ይሰኛል :: ሜሶፖታሚያ የተባለው በወንዞች መካከል የሚገኝ ምድር መሆኑን ለማመልከት ነበር ::የጢግሮስ ወንዝ በምስራቃዊ ቱርክ ከሚገኘው ታውረስ ታራራ ተነስቶ 1 ሺህ 750 ኪሎሜትር ድረስ ይፈሳል::

የአባይ ሸለቆ (Nile Valley) በ3100 ከክርስቶስ ልደት በፊት አካባቢ ግብጽን በግብርና ላይ የተመሰረተ ሰፈራ ፈጥሮ የአለማችን አንዱ የጥንታዊ ሥልጣኔ ማእከል አድርጓታል:: ሦስተኛው ሥልጣኔ በ2600 BC አካባቢ የኢንዱስ ወንዝ በዛሬዎቹ ከፊል ህንድና ፓኪስታንየጀመረው ሥልጣኔ ነበር :: አራተኛው በቻይና የተፈጠረው የየሎው ወንዝ ወይም ሀንግ ሂ ወንዝ ሥልጣኔ ይጠቀሳል::

ሥልጣኔ በወንዞች ሸለቆዎች አካባቢ ለማቆጥቆጡ እንደምክንያት የሚጠቀሰው ባብዛኛው ለግብርናና ለሰዎች ፍላጎት ለማሟላት ሚሆን አስተማማኝ የውሃ ሀብት ስለሚፈጥር ነው:: የተትረፈረፈ የውሃ ሀብት ባለበት እና በአመታዊ የጎርፍ ፍሰት

የሚፈጠር ለም አፈር ከግብርና መንደሩ ፍጆታ በላይ የተትረፈረፈ የእህል ምርት ይፈጥራል :: ይህም ለተወሰኑ የማህበረሰቡ አባላት ከግብርና ውጭ በሆኑ የግንባታና ከተሞች መቆርቆር፣የብረታብረት ሥራዎች ፣ንግድ እና ማህበራዊ ድርጅት ተግባራት ዙሪያ ይሳተፋሉ::ጀልባዎችና የውሃ ላይ መጓጓዣዎች ሰዎችና እቃዎችን በቀላልና አመቺ በሆነ መልኩ ከማጓጓዝ የንግድ ግንኙነት እንዲሰፋ እና የማእከላዊ መንግስት በግዛቱ ስር ያሉትን አካባቢዎች መቆጣጠር ያስችለዋል::

ጢግሮስ ወንዝ በደቡብምእራብ እስያ ከቱርክ ተነስቶ ከኤፍራጠስ ወንዝ ጋር ከመቀላቀሉ በፊት በኢራቅ ምድር ይፈሣል::ወንዙ 1 ሺህ 900 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ ከምስራቃዊ ቱርክ ተነስቶ ወደ ደቡባዊ ምስራቅ ኢራቅ ይፈሳል::

ኤፍራጠስ ወንዝ 2 ሺህ 700 ኪሎሜትር የሚረዝም ሲሆን፤444 ሺህ ስኩዬር ኪሎሜትር መሬት የሚሸፍን ነው ::94 በመቶ የሚሆነው የውሃ ተፋሰስ የሚመነጨው ከቱርክ ደጋማ ስፋራዎች ነው ::ኤፍራጠስ ወንዝ ከ120 ኪሎሜትር ያህል በቱርክና ሰሜናዊ ምስራቅ ሶሪያ አሌፖ ግዛትን የሁለቱ ሀገራት ድንበር በመሆን ይከፍላቸዋል::የኤፍራጠስና የጢግሮስ ወንዞች ትይዩ ሆነው የሚፈሱ ሲሆኑ፤ሁለቱ ወንዞች ኢራቅ ከገቡ በኋላ በመካከላቸው የሚኖረው ርቀት ከ160 ኪሎሜትሮች አይበልጥም::ዝነኛው ጥንታዊው የባቢሎን ሥልጣኔ በሁለቱ ወንዞች መካከል ይገኝ ነበር::

የኤፍራጠስ ወንዝ በመካከለኛው ምስራቅ የሥልጣኔ መነሻ ቢሆንም ፤በተለይ በቱርክ ፣ በሶሪያና በአራቅ መካከል ዋነኛ የፖለቲካ ውጥረት የፈጠረ መሆኑ ይነገራል::ሁሉም የወንዙን ውሃ ለመስኖና የኤሌክትሪክ ሀይል ምንጭነት መጠቀም ዙሪያ ይወዛገባሉ:: ቱርክ ከኤፍራጠስ ወንዝ ከፍተኛ የውሃ ድርሻ በመቀልበስ ለረዥም ጊዜ እቅድ የአናቶሊያ ገጠር ልማት እየሰራችበት ነው ::ይህ እቅድ የደቡባዊ ምስራቅ አናቶሊያ ፕሮጀክት   በመባል የሚታወቅ ሲሆን ፤ በእቅዱ ቱርክ 22 ግድቦችንና 19 የኃይል ማመንጫዎችን :: ቱርክ ከዚሁ ፕሮጅክቷ ግዙፉን የአታቱርክ ግድብ እ.ኤ.አ በ1990 አጠናቃለች :: 

የግድቡ የሚይዘው የውጃ ሽፋን 816 ስኩዬር ኪሎሜትሮችን ነው:: በተወሰነ ጊዜ ለአንድ ወር ያህል የወንዙን የውሃ ፍሰት በመግታት ግድቡ እንዲሞላ ይደረጋል:: የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ሶሪያና ኢራቅ በዚሁ የኤፍራጠሥ ወንዝ የእርሻና የሀይል ምንጫቸውን ሲገነቡ ቆይተዋል::

ሶሪያ በዚሁ ወንዝ ላይ ግዙፉን አል ታውራ ወይም ሪቮሉሽን ዳም የተሰኘ የሀይል ማመንጫና የመስኖ ግድብ እ.ኤ.አ በ1973 ግንባታ አጠናቃለች:: ግድቡ 640 ስኩዬር ኪሎሜትር ውሃ የሚይዝ “አሳድ ሀይቅ” ፈጥራለች :: ሶሪያ በኤፍራጠሥ ወንዝ ላይ የገነባቸው ግድብ በፈጠረው የወሃ መቀነስ በኢራቅና በሶሪያ እ.ኤ.አ 1975 ወደ ጦርነት ሊገቡ ጥቂት ነበር የቀራቸው :: ኢራቅ የግብርና ኢንዱስትሪዋን ለማዘመን እ.ኤ.አ በ1986 የገነባችው “ሀዲዝ ግድብ” መጠነኛ እፎይታ ሰጥቷል::

በአለም ስልጣኔ ግንባታ ውስጥ እያንዳንዱ ሥልጣኔ የተለየ ነገር ቢኖረውም ፤ በእነዚህ የመጀመሪያ ሥልጣኔዎች የሚያመሳስላቸው በወንዞች ዳርቻ መመስረታቸው ነው:: አብዛኛዎቹ A hydraulic empire የተሰኘ የውሃን ሞኖፖሊ ግዛት መፍጠራቸው ይጠቀሳል::ይህም የውሃ ሀብትን በመቆጣጠር ማህበራዊ ወይም የመንግስታዊ አወቃቀር ሃይል መፍጠር ነበር:: በዚህ የመንግስት ስርአት መነሻው ጎርፍን መቆጣጠር እና የመስኖ እርሻ በማስተባበር እና የተለየ ቢሮክራሲ በመፍጠር የማስተዳደር ዘዬ ነበረው::

ሰሞኑን  ኢትዮጵያና የቱርክ መሪዎች  አራት ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡ ከእነዚህ ሰምምነቶች የውሃና የወታደራዊ ስምምነቶች ይጠቀሳሉ፡፡ ግብጽና ሱዳን ይህንን የቱርክና  የኢትዮጵያ  አዲስ ስምምነቶች  ኢትዮጵያ ከቱርክ ስለምታገኘው የጦር መሳሪያዎች ይልቅ የሚያሳስባቸው፤ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ  አጠቃቀም እንደ ቱርክ   በጢግሮስና  በኤፍራጠስ  ወንዞች  ላይ የገነባችው  የአታቱርክ ግድብ  አይነት አቅጣጫ እንዳትከተል ይሰጋሉ፡፡ 

በአንድ ወቅት  አንካራ ላማደራደር በጠየቀች ጊዜ የግብጽ ባለስልጣን ”ኢትዮጵያ ቱርክ አይደለችም፡፡ ግብጽና ሱዳን ደግሞ ኢራቅና ሶሪያ አይደሉም፡፡ ” በሚል ጠንከር ያለ መግለጫ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡  

ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር በውሃ ዘርፍ ለመስራት ያደረገችው ስምምነት  ሁለቱ ሀገራት  የወታራዊ  ስምምነት በላይ  በኢፍራጠስና የጠየግሮስ ወንዞችን የመገደብ ልምድ በአባይ ወንዝ እንዳይደገም ይሆናል፡፡ 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top