የወያኔ ዘራፊዎች “ ሁሉን ተምኝተው ፣ ሁሉን ያጡ ” ከንቱዎች ሆነዋል !!
Ø “ ባድሜ ሰፈርን“ እንደማሳያ
( ገለታ ገ/ወልድ – ድሬቲዩብ )
በአዲስ አባባ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 13 “ ባድመ ሰፈር“ የሚባል አንድ ዘናጭ የመኖሪያ አካባቢ አለ ፡፡ ከኢትዮ -ኤርትራ ጦርነት በኋላ በአብዛኛው የህውሀት ጀኔራሎችና ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች ብሎም ደህንነቶችና ቱባ የትግራይ ባለስልጣኖች ከ500 እስከ 1000 ካሬ ሜትር ቦታ ተቀራምተውት ዘመናዊ ቪላና ፎቅ የሰሩበት የቅንጦት መኖሪያ አካባቢ ነው ፡፡
ይህ አካባቢ በማስተር ፕላኑ ላይ የሚያሳየው የአርንጓዴ ቦታ መሆኑ እየታወቀ ፣ በማን አለብኝነትና ስልጣንን ተገን አድርጎ በተፈፀመ አሻጥር አውሮፓን የመሰለ ስፍራ ሆኗል ፡፡ የሚያሳዝነው ግን በአሁኑ ወቅት ሰው የማይኖርበት ብቻ ሳይሆን ማታ መብራት እንኳን የማይበራበት ፣ “ የወያኔን አዲስ አበባ መግባት“ የሚጠብቅ ተስፈኛ ከባቢ መሆኑ ነው ፡፡ ብዙዎቹ ቤቶች እየጠበቁ ያሉ ቆምጨዎች የማን ቤት መሆኑን እንኳን እንደማያውቁ የአካባቢው የፖሊስ ሃላፊ ገልፆልኛል፡፡
በዚህ አካባቢ አይደለም ለግዥ ፣ ለኪራይ እንኳን በወር ከ100ሺ ብር በታች ቤት ለማግኘት ማሰብ የህወሓት ነው፡፡ ገራሚው ነገር “ ስልጣንና ጊዜ ደግ ስለሆነ እንጂ” 10 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታ ለማከናወን ህጋዊ ፈቃድ ማግኘት በማይቻልበት አካባቢ፤ እንዴት አድርጎ ፣ አንድ ሰው አራት አምስት ቦታ ይዞ ባለመቶ ሚሊየነር መሆን ተቻለ የሚለው ተጠየቅ ነው !? ዘመኑ እንደቀኝ ገዥዎች ጥቂቶች ያሻቸውን የሚያደርጉበት ነበርና ግን ሆነ ፡፡ የሚጠቀሙበት ባይሆንም !!
እነዚህ ዘራፊዎች ፣ የያዙት አልበቃ ብሏቸው ተጨማሪ በደል በህዝብ ላይ ለማድረስ አልቦዘኑም ነበር ፡፡ ዛሬ ትግራይ ያለውን የመከላከያ ሃይል አጥቅተው፣ ዳግም ተንቤን በረሃ ገብተው፣ አማራና አፋር ክልልን ለመውረር ብሎም አገርን ለመበተን የሚፍጨረጨሩትና በግብረ ሽበራ ላይ የተጠመዱትም አንድ ጊዜ የለከፋቸው ሳይጣን ስላለቀቃቸው ነው ፡፡ ከቀድሞዎቹ ጀኔራሎች ትናንት የተማረከው ማሾን ጨምሮ ፣ እነወዲ ወረደ፣ ወዲ መድን ፣ጀ/ራ ዮሀንስ፣ ጄኔራል ፃድቃን ( ቢባረረም ) ፣ ጄኔራል አበበ( ጀቤ) ፣ ኳርተር፣ ኒቆዲሞስ ዜናዊ… ሁሉ በዚያችው ወረዳ ከሶስት በላይ ዘመናዊ ቪላ ባለቤቶች መሆናችውን በመረጃ ማረጋጋጥ ይቻላል ፡፡ በርካታ የህውሀት ኮሎኔሎችና ሻለቃዎችም ቢያንስ አንድ አንድ ቪላ ገንብተዋል ፡፡በህዝብ መሬት ፣በህዝብ ገንዘብ !!
ይህ የሆነው እንግዲህ በባድሜ ጦርነት በአስርሺዎች የሚቆጠሩ የብሄር ብሄረሰቦችና የድሀ ልጆች ህይወት ከተገበረ በኋላ ለፈሰሰው ደምና ለተከሰከሰው አጥንት እዚህ ግባ የሚባል መታሰቢያ እንኳን ሳይቆምለት ነው ፡፡ ዘራፊዎች ግን በሸገር በባድመ ስም የሚጠራ ድንቅ ፣ የተጭበረበረ ከተማ ፈጥረው ላይኖሩበት ገንብተው ነበር ፡፡ በእርግጥ አሁን ወደ ጁነታነት የተቀየሩና አገር የከዱ ዜጎች ይዞታዎች ፣አንዳንዶቹም ባለቤት አልባ የሆኑ ቪላዎች ወደ መንግስት ይዞታነት ተመልሰዋል ሲባል ሰምቻለሁ ፡፡ ምን ያህል ተጨባጭ እርምጃ እንደተከናወን ባይታወቅም ፡፡
በዚህ ላይ ሁሉን ተመኝቶ፣ ሁሉን ያጣው ጁንታ፣ አስቦትም ይሁን ሳያስበው ከአገር ጋር ተላትሞ እንዳይሆኑ ሆኗል ፡፡ የዘረፈውንም ሆነ ሰርቶ ያገኘውን ሀብት አጥቷል ፡፡ ከኢትዮጵያ ህዝብ ላብና ደም እየነጠቀ ኢፈርት… ምናጥርሴ እያለ ያካበተው ገንዘብ ማነቆ ተበጅቶለታል ፡፡ በጋራም ሆነ በተናጠል ምዝበራ የተከማቹ ድርጅቶች ፣ ፎቆችና ሪልስቴቶች እንዲሁም ባድሜ ሰፈርን የመሰሉ ቪላ መንደሮች አደባባይ ላይ የተጋለጡ የህዝብ ሀብት መሆናቸው ተረጋግጧል ፡፡በእርግጠኝነት ህወህትና መሪዎቹ ለፍርድ ሲቀርቡ ተገቢውን ውሳኔ ማግኘቱ አይቀርም !!
እናም ጁንታዉና የአሸባሪው ህውሀት አንዳንድ ቁንጮዎች የተዘረፈ ሀብታቸውንም ሆነ የቋመጡለት ስልጣን ከተገኘ እስከ መጨረሻው መፋለምን ሽተዋል ፡፡ ካልሆነ ግን ሁሉንም አጥተው በኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን፣ ራሳቸው ከወጡበት የትግራይ ህዝብ የሚገጥማቸውን ውግዘት ላለመሸከም በጦር ሜዳ ለመደምሰስ የወሰኑ መስለዋል ፡፡ ይሄውና እየተደመሰሱም ይገኛሉ!!
ለዚህ እኩይ ተግባራቸው ከትግራይ እናቶች ጓዳ እያስገደዱና አደንዛዥ እፅ እያስጠቀሙ በየአውደ ውጊያው ከፊት ያሳጨዷቸው ወጣቶች አንድ ማሳያ ናቸው ፡፡ በአፋርም ሆነ በአማራ ክልል በንፁሃኖች ላይ እየወሰዱት ያለው እርምጃም ሆነ ኮልኮሌ የቤት እቃ ሳይቀር ለመዝረፍ የነበረው መራኮትም ሌላ መገለጫ ነው ፡፡ ሁሉም ግን ላይመለስ እየሄደ ወደፍፃሜው ተቃርቧል !!