ጠባችን “ከዶክተር አብይ ነው” አሉን፤ ዶክተር አብይ የሚኖሩት ታዲያ ገበሬው ቡሃቃና ሞሰብ ውስጥ ሆኖ ነው ዝርፊያው?
(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)
ደሃው ገበሬ ትህነግን በተመለከተ የነበረው ጥላቻ በሀገሩ ስለመጣችበትና ስለነጠቀችውና ስለዘረፈችው ነበር፡፡ አሁን ብርቱዎቹ እነ ጌታቸው ረዳ በየጓዳው ገብተው ህዝባቸውን ከደሃ ገበሬ ደም አቃቡ፡፡
የትህነግ አማጺዎች በለየለት ውሸት ስማቸውን በወርቅ መዝገብ የጻፉ አጭበርባሪዎች ቢሆኑም በየቀኑ የሚፈጥሩት ምክንያት ደግሞ እንኳን የእነሱን የደጋፊዎቻቸውን ጤንነት እንድንጠራጠር ያደርገናል፡፡
አፋር ላይ ንጹህ ገድለው መጋዘን አቃጥለው በጀግናው ሀገር ወዳድ የአፋር ህዝብ ተገርፈው ሲወጡ ከወንድም ህዝብ ጋር ላለመዋጋት ለቀን ወጣን ብለው ነገሩን፤ የሚገርመው ሲያፈቅሩ ህጻን ሴትና አረጋዊ መግደል ከሆነ ሲጠሉስ ምን ይሆን የሚያደርጉት?
ሰሞኑን አማራ ክልል ወሎና ደቡብ ጎንደር የገባው ሃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል፡፡ መግቢያ አጥቶ እጅ እስኪሰጥ ድረስ ሞት ምሱ ነበር፡፡ አሁን ዓለም እንኳን የማይወጣውን እንደገባበት ገብቶት በገዛ ደጋፊዎቹ ተው እየተባለ ነው፡፡
ጌታቸው ረዳ ግን ዛሬም የቅጥፈት ጌታ ሆነዋል፡፡ አብይ አህመድ ከሚለው ተደጋጋሚ የጥላቻ ንግግራቸው ቀጥሎ አገኘሁ ተሻገር በምትለው ያሟሹና አዲስ ውሸት ይነግሩናል፡፡ የአማራ ገበሬ እውነትም አውቋል ሲሉ ትናንት የምናውቀውን ደፋር ንግግራቸውን አካፍለዋል፡፡
መጀመሪያ ፍላጎታችን የትግራይ እናት ላይ የመሳሪያ አፈሙዝ እንዳይደቀን ነው ብለው የአማራን እናቶች ለማስለቀስ ሆ ብለው መጡ፡፡ ቀጠሉና የለም ከብልጽግና እና ከአብይ አህመድ ነው ጠቡ አሉ፡፡ እውነቱ ግን ሌላ ሆነ፤
ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እህቶቻችን ጭን ውስጥ አይደሉ፤ ይሄ ሁሉ ጥቃትና ደፈራ ምን ማለት ነው? ዶክተር አብይ እና አቶ አገኘሁ አማራ ሞሰብ ውስጥ ምን ይሰራሉ? አማራ ቡሃቃ ውስጥስ ይኖራሉ?
ሊጥ ሳይቀር የዘረፈ ቡድን፣ ሞሰብ ተሸክሞ የሄደ፣ ትምህርት ቤቶች ያወደመ፤ የንጹሃንን መኖሪያ ቤት በሞርታር የመታ፡፡ መቼም እያንዳንዱ የግፍ ስራ መልሶ ይከፍላል፡፡ ነገ የሚሆነው ሲሆን ምን አፍ ምን እንደሚናገር አብረን እናያለን፡፡
በወሎ እና በደቡብ ጎንደር ያልተዘረፈ ምንድን ነው? ዶክተር አብይን ደሃው ገበሬ ቁሳቁስ ውስጥ ሊፈልጉ ነው ጭነው የፈረጠጡት? ደጋፊዎቻቸው ሳይቀር ያደረጉትን ቢመለከቱ ከነውሩ ብዛት የተነሳ አንገታቸው በተሰበረ ነበር፡፡
በየቀኑ የፈጸሙት በደል ግፍና ስቆቃ የጠላቶቻቸውን ቁጥር አብዝቶ የደጋፊዎቻቸውንና የሠራዊታቸውን ሕይወት ቀጠፈ፡፡ ሀገር ለማፍረስ ቋምጠው የወንበዴ ቡድናቸውን ህይወት በአጭር አስቀሩት፡፡ ከትዕቢታቸው ብዛት ቀድሞ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ገቡ፡፡ ትዕቢት ቀጥሎ ከመቀሌ ወደ ተንቤን ዋሻ ወሰዳቸው ምናልባት የአሁኑ ከትግራይም ሊያስወጣቸው ይሆናል፡፡
የተፈጸመው ግን አይረሳም፡፡ ከትህነግ ታጋዮች ሞት ይልቅ ክረምቱን በሰላም ማረስ የሚፈልግ ገበሬን ሰፈሩ ድረስ መጥተው መከራ ሆነውበታል፡፡ በመጡበት መንገድ አልተመለሱም፡፡ የሚበልጡት በሀገር መከላከያና በአማራ ህዝባዊ ሰራዊት በወረሩት መሬት ቀርተዋል፡፡
እንወድሃለን ለሚሉትም ሂሳብ እናወራርድብሃለን ለሚሉትም እኩል ስቃይና መከራ መሆናቸው ይገርማል፡፡ ኢትዮጵያ ግን ሲዖል ድረስ ወርደው ማፍረስ ሳይጠበቅባቸው በጉና ተራሮች ላይ ህልማቸውን ያከሸፈች ሀገር ሆናለች፡፡