Connect with us

ጊዜው አልፏል!!

ወገን እንቁረጥ?!
Social media

ነፃ ሃሳብ

ጊዜው አልፏል!!

ጊዜው አልፏል!!
(ፋሲል የኔዓለም)

የተኩስ አቁም ጥሪ ጊዜ አልፏል። ህወሃት ተኩስ እንዲያቆም እድል ተሰጥቶት አልተጠቀመበትም። ተኩስ ማቆምን የሽንፈት ምልክት አድርጎ ውስዶታል። በኢትዮጵያ ሰራዊትና ህዝብ ወኔ ላይ ተሳልቋል። እነ ጌታቸው ረዳ “ስናባርራቸው አዲስ አበባ እንዳንገባ ነው የምንፈራው” እያሉ በሰራዊታችን ላይ አሹፈዋል።

ከእንግዲህ ማን አባራሪ፣ ማን ተባራሪ፤ ማን ወደ ሲኦል ገፊ፣ ማን ደግሞ ወደ ሲኦል ገቢ እንደሚሆን ይታያል። ሰለሰላም መዘመር ፈሪ ካስባለ፣ ስለጦርነት መዘመር ደግሞ ጀግና ያስብል እንደሆን፣ እነ ጌታቸው በቅርቡ የተግባር ትምህርት ይሰጣቸዋል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት በከፍተኛ የውጊያ ሞራል ላይ ነው። በቂ የሰው ሃይልና የጦር መሳሪያም እያገኘ ነው። በዚህ ሰዓት ከእያቅጣጫው የሚመጣ የተኩስ አቁም ጥሪ፣ ይህን የውጊያ ሞራል ለመስበርና ዝግጅቱን ለማደናቀፍ ያለመ ከመሆን አይዘልም።

ሰማንታ ፓወር ያቀረቡት የተኩስ አቁም ጥሪም ቢሆን አላማው፣ አንድም ህወሃት የእነ አሜሪካን የተኩስ አቁም ጥሪ ሰምቶ እንደወጣ በማስመሰል፣ በአማራና አፋር አካባቢዎች የደረሰበትን ውድቀትና የሞራል ኪሳራ ለመሸፈን ሌላም በተኩስ አቁም ስም ህወሃት የመዘጋጃ ጊዜ አግኝቶ እራሱን እንደገና እንዲያደራጅ እድል ለመስጠት ነው።

ህወሃት አፋርና አማራ ላይ በመደቆሱ የውጊያ ሞራሉ ወድቋል። አሁን የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች፣ “አልሞትኩም” ለማለት ካለሆነ በስተቀር፣ የሃይል ሚዛን ለውጥ የሚያመጡ አይደሉም።

ህወሃት ለኢትዮጵያ ህልውና ስጋት በማይፈጥርበት ደረጃ ላይ መድረሱ በትክክል ሲረጋገጥ፣ ያን ጊዜ ጦርነቱ እንዴት ይቋጭ በሚለው ጥያቄ ላይ መነጋገር ይቻላል።

መንግስት ከእነ ሳማንታ ፓወርም ይሁን ከሌሎች ወገኖች የሚመጣን የተኩስ አቁም ጥሪ በዲፕሎማሲ መንገድ እያስተናገደ፣ መሬት ላይ የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል አለበት። ህዝቡም ሁለንተናዊ ድጋፉን መስጠት አለበት። በተለይ ዲያስፖራው አገሩን በገንዘብ ለመርዳት ልዩ ታሪካዊ ሃላፊነት ወድቆበታል።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top