Connect with us

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማርያ ዛካሪቫስ ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል

በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ

ዜና

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማርያ ዛካሪቫስ ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማርያ ዛካሪቫስ እየተካሄደ ያለውን የህልውና ዘመቻና በወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል

በትግራይ ካለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ሁኔታውን የሚያዩበት መንገድ መለያየትን የሚያባብስና ሃላፊነት የጎደለው ሆኖ መታየቱን ሩሲያ አስታወቀች።

ቃል አቀባይዋ በመግለጫቸው አሸባሪው ህወሃት አሁንም ድረስ ወደ ውጊያ በመግባት ወደ አፋር እና አማራ አጎራባች ክልሎች ጥቃት በመሰንዘር የሰብአዊ ድጋፍ እንዲስተጓጎል ማድረጉንና የኢትዮ-ጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ጥቃት መፈጸሙን ገልጸዋል።

“ቡድኑ ከክልሉ በማለፍ ያደረሰው ጭፍጨፋና ጥቃት ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈለጋቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ድጋፍ እንዳያገኙ አድርጓል” ብለዋል።

“ለእነዚህ ችግሮች መከሰት የአንዳንድ የምዕራባውያን የሚዲያ አካላት ሚናም ከፍተኛ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል” በማለት ያብራሩ ሲሆን፤ የእነዚህ አካላት እንቅስቃሴ ሰላምን ከማምጣት ይልቅ ሀላፊነት በጎደለው ተግባር ጥፋትን ማባባስና ልዩነቶችን የማቀጣጠል ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

“ደም መፋሰሱን ለማስቆም፣ የሰብአዊ ሁኔታን ለማሻሻል፣ ማህበረ-ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለመፍጠርና ተፈናቃዮችን ወደ ቋሚ መኖሪያቸው ለመመለስ በሁለቱም በኩል የተኩስ አቁም ማወጅ ብቸኛው አስተዋይ መንገድ ነው ብለን እናምናለን” ነው ያሉት።

“በትግራይ ክልል ሰላምን ለማምጣትና ወደ መደበኛ የህይወት እንቅስቃሴ ለመመለስ በኢትዮጵያ መንግስት እየተከናወነ ያለውን ተግባር አለም አቀፉ ማህበረሰብንና ቀጠናቂ ተቋማትን እንዲደግፉ ጠሪ እናቀርባለን ሲሉም አስታውቀዋል።

“ሩሲያ ኢትዮጵያውያን የውስጥ ጉዳያቸውን ከአፍሪካውያን ጋር በራሳቸው ለመፍታት ወሳኝ ሚና መጫወት አለባቸው ብለን እናምናለን” ሲሉ መግለጻቸውን በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አስታውቋል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top