Connect with us

የጆ ባይደን ግልፅ ውሸት!!!

የጆ ባይደን ግልፅ ውሸት!!!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የጆ ባይደን ግልፅ ውሸት!!!

የጆ ባይደን ግልፅ ውሸት!!!

(ጌታሁን ሄራሞ)

ጆ ባይደን የታሊባንን ድል አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ አፍጋኒስታን የነበርነው ለሀገሪቱ ግንባታ(Nation Building) ሳይሆን አልቃይዳ ከአፍጋኒስታን ተንደርድሮ ዳግም የሴምቴምበር 11 ዓይነት ጥቃት እንዳይፈፅምብን ማኮብኮቢያውን ለማፍረስ ነው ብሏል። በአጭር ቃል አሜሪካ የራሷን ዓላማ ለማሳካት በምትወስደው እርምጃ አፍጋኒስታን የተባለች ሀገር ብትፈራርስም ግድ አይሰጣትም ማለት ነው።

  ጆ ባይደንና ደጋፊዎቹ ግን ለመላው ዓለም የውሸት መረጃን እያስተላለፉ ነው፣ ለምሣሌ ከዚህ በኋላ አልቃይዳም ባይሆን ሌሎች አሜሪካ-ጠል አክራሪዎች ወደ ፊት አፍጋኒስታንን እንደ መስፈንጠሪያ ተጠቅመው አሜሪካን ለማጥቃት ስለአለመቻላቸው ባይደን እርግጠኛ ሊሆን የቻለው በምን መስፈርት ነው?  ለዚህ ጥያቄ ጆ ባይደን ምላሽ ይኖረዋል ብዬ አልገምትም። 

ምክንያቱም በአፕሪል 2009 የአሜሪካ መከላከያ “United States Plan for Sustaining the Afghan National Security Forces” በሚል ርዕስ ያወጣው ሪፖርት የሚያመለክተው የአሜሪካኖቹ የአፍጋኒስታን ቆይታ ስትራቴጂአቸው ታሊባኖች ወደ ፊት አፍጋኒስታንን በመነሻነት ተጠቅመው አሜሪካ ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ ጠንካራ የአፍጋኒስታንን የፀጥታ ኃይልን መገንባት ነበር።  

አሜሪካኖቹ ይህን ግባቸውን አላሳኩም፣ በአፍጋኒስታን ለማቋቋም ያሰቡት አሻንጉሊት መንግስትና የመከላከያ ኃይል ሕልም ብቻ ሆኖ ቀርቷል። በአጭር ቃል አሜሪካ ነገ ከነገ ወዲያ ከአፍጋኒስታን ምድር ወደ አሜሪካ የሚሰነዘር ጥቃት ይኑር አይኑር መተማማኛ የላትም። ጆ ባይደን ግን ይህን ውድቀቱን ባለየ አልፎት በመግለጫው “We went to Afghanistan almost 20 years ago with clear goals: get those who attacked us on September 11, 2001 — and make sure al Qaeda could not use Afghanistan as a base from which to attack us again.

We did that — a decade ago.

Our mission was never supposed to be nation building.” በማለት አስቀምጧል። በዚህ መግለጫው ውስጥ “…make sure al Qaeda could not use Afghanistan as a base from which to attack us again. We did that — a decade ago.” ያለውን አስምሩልኝ። ይህ ውሸት አፕሪል 2009 ይፋ ከሆነው ከአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ሪፖርት ጋር ፊት ለፊት የሚላተም ነው። 

 አሜሪካ አልቃይዳም ይሁን ሌላ ቡድን አሜሪካን ወደ ፊት ዳግም እንዳያጠቃት ጠንካራ የአፍጋኒስታንን መከላከያ ምንጩ ላይ ማስቀመጥ አልቻለችም። Hence, USA is not sure that al Qaeda or any other terrorist groups could use Afghanistan as a base from which to USA again.

 እንግዲህ አሜሪካ አፍጋኒስታን የነበረችው የአልቃይዳን ማኮብኮቢያ ለመናድ እንደሆነ በግልፅ አስቀምጣለች። በዚህ እርምጃዋ አፍጋኒስታን የሚባል ሀገር ይፍረስ አይፍረስ ግድ እንደማይሰጣትም በመሪዋ በኩል ይፋ አድርጋለች። ይህ የሚያሳየው አሜሪካ ጣልቃ በምትገባባቸው በሌሎቹም ሀገራት ዓላማዋ የራሷን ጥቅም ከማስጠበቅ የዘለለ እንደማይሆን ሲዘገብ የነበረውን የሚያረጋግጥ ነው። ዓላማዋ ወታደራዊም ወይም ጂኦ-ፖለቲካዊም ሊሆን ይችላል።

 ለምሣሌ በአሁኑ ወቅት አሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ ገብቼ ካልፈተፈትኩ ሞቼ እገኛለሁ በማለት የምትታትረው በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ወደ ፊት የምኖራትን ጂኦ-ፖለቲካዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እንደሆነ ብዙዎች ተንታኞች የሚስማሙበት ነው፣ በዚህ ሂደት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከፈራረሳች ወደ ፊት ከአሜሪካኖቹ የሚሰጠው መግለጫ ልክ እንደ አፍጋኒስታኑ “Our mission was never supposed to be nation building.” የሚል ስለመሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።

የአሜሪካኖቹ የአፍጋኒስታን ጣልቃ ገብነት ከኢትዮጵያው ፈፅሞ የተለየ ስለመሆኑ ግን እዚህ ጋ ማስመር ግድ ይላል። አፍጋኒስታን ውስጥ አሜሪካ የተቃወመችው የታሊባን አማፂያንን ነው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የወገነችው ከሕወሓት አሸባሪዎች ጎን ነው፣ በሌላ አነጋገር በሚሊየኖች የተወከለውን መንግስትንና የሕዝቡን ምርጫ ወደ ጎን በመተው በ27 ዓመታት አገዛዙ ሀገሪቱን ላራቆተው የሕወሓት ቡድን ወዳጅነቷን ገልፃለች። 

ይህ ብዙኃኑን ወደ ዳር የገፈተረው የአሜሪካ እርምጃ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከአፍጋኒስታንም የከፋ ያደርግባታል። አሜሪካ እንደ አፍጋኒስታን በኢትዮጵያ ጉዳይ ገብቼ ልፈትፍት ካለች ተቃውሞ የሚጥማት እንደ አፍጋኒስታን ከጥቂት ቡድን ሳይሆን በሕወሓት የበፊት አመራር ከተማራረው ከመቶ ሚሊየን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top