Connect with us

ሽብርተኛው ህወሃትና በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች የጥፋት ቁርኝት……

ሽብርተኛው ህወሃትና በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች የጥፋት ቁርኝት……
Photo: Social media

ዜና

ሽብርተኛው ህወሃትና በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች የጥፋት ቁርኝት……

ሽብርተኛው ህወሃትና በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች የጥፋት ቁርኝት……

የትግራይ ህዝብ የጥሞና ግዜ እንዲያገኝና አርሶ አደሩም የክረምቱን ዝናብ በአግባቡ ተጠቅሞ ማሳውን እንዲያለማ መንግስት በሆደ ሰፊነት የወሰደውን የተናጥል የተኩስ አቁም እርምጃ ሽብርተኛው ህወሃት ይህን እድል እንደመልካም አጋጣሚ በመውሰድና እድሉ እንዳያመልጠኝ በማለት በአፋር ክልል ያደረገውን አይነት ተመሳሳይ ትንኮሳና ወረራ ከአማራ ክልል ህዝብ ጋርም የማወራርደው ሂሳብ አለኝ በሚል ስሌት ፈፅሞታል፡፡ 

የሽብር ቡድኑ በአማራ ክልል እንዲህ አይነት መጠነ ሰፊ የሆነ ወረራ ሲፈፅም በሱዳን በኩል የመውጫ ኮሪደር በማመቻቸት ለሽብር እንቅስቃሴው ይረዳው ዘንድ ሱዳንን የወታደራዊና የፖለቲካዊ ማዕከል ማድረግ፤ እንደለመደው ሀብት መዝረፍ የማሸሽ፤ሰብዓዊ ክብርን በማርከስና በማዋረድ ሴቶችንና ህፃናትን የመድፈር አሁን ላይ እያደረገ ያለውን የጅምላ ግድያ በማካሄድ የብቀላ በትሩን ማሳረፍ ነው ዓላማው፡፡ 

ቡድኑ ታዲያ ይህንን እኩይ የጥፋት ሴራውን እውን ለማድረግ በራያ ቆቦና በወልዲያ በኩል  እያደረገ ካለው ትንኮሳና ወረራ በተጨማሪ በሁመራና በማይፀብሪ ባሉ ግንባሮችም በተከታታይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ቢሰነዝርም፤በድንበሩና በመሬቱ ድርድር የማያውቀው ጀግናው የአማራ ህዝብ፣ልዩ ሀይሉና ታጣቂው እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወረራና ትንኮሳውን በጣምራ በመመከትና የአፀፋ እርምጃ በመውሰድ የሽብር ቡድኑን ፍላጎት አምከነውታል፡፡ 

ይህ አልሳካለት ያለው አሸባሪው ህወሃት የጥፋት ተልዕኮውን እውን ለማድረግ ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን በማማተር በጦርነቱ ወቅት በስደተኛ ስም ሀሻባና ግንዳማ በተባሉና በሌሎችም በሱዳን በሚገኙ ስደተኞች ካምፕ ውስጥ አስርጎ ያስገባቸውን እንደ የሳምሪ ወጣቶች ያሉ ገዳይ እስኳድና ልዩ ሀይልም ጭምር የሚገኙበትን ሰብስቦ በማደራጀት፣ በማስልጠንና በማስታጠቅ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በሁመራ በኩል ዘልቀው እንዲገቡና ወረራና ጥቃት እንዲፈፅሙ በተደጋጋሚ ከፍተኛ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም፤ በድንበር ላይ በሚገኘው በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እየተደመሰሱና የሃፍረት ካባቸውን እየተከናነቡ ተመልሰዋል፡፡

ካልሆኑት እንደ ግብፅ ካሉ ሀገራት ጋር በህቡእ ግንኙነት በመፍጠር አሁንም ተመሳሳይ ወረራና ትንኮሳ ለመፈፀም በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ የመረጃ ምንጮቻችን ያሰረዳሉ፡፡ ለዚህ ሴራቸው ስኬትም በስደተኞች ካምፖች ላይ የተለያዩ የመቀስቀሻና የማነሳሻ የተሃድሶ ዝግጅቶችን እያተጠቀሙ መሆኑን ምንጮቻችን በቪዲዮ አስደግፍው አረጋግጠዋል፡፡

በተያያዘም የቀድሞ የህዋሃት አመራር የነበሩትና አሁን ላይ የሽብር ቡድኑ የውጭ ጉዳይ ተወካዮች የሆኑት አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ እና ፍስሃ አስገዶም የተባሉት በቅርቡ ወደ ሱዳን ካርቱም በመምጣት የገዳይ እስኳድ ቡድን የሆነውን የሳምሪ ወጣቶች ቡድን አባላትንና በሱዳን ለልዩ ተልዕኮ ቡድኑ እያዘጋጃቸው ያሉ ታጣቂዎችን በአካል በማግኘት የሞራል ግንባታና

የቀጣይ ስምሪት አቅጣጫዎች ላይ ዉይይት ማድረጋቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ አስፈላጊውን የገንዘብና የሎጀስቲክስ ድጋፎችን ከሽብርተኛው ህወሃት እንደሚያገኙ ቃል የገቡላቸው ሲሆን፤ በተጨማሪም በቆይታቸው እነዚህ የጁንታው አመራሮች በሱዳን የሚገኙ እንደ ራሻይዳ ያሉ የህገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን በማግኘት ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ሚስጥራዊ ድርድር ማድረጋቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው አረጋግጠዋል፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top