Connect with us

የአማፂያንን የጦር አውርድ ለመግታት ዜጎች በጋራ መቆም ይኖርብናል!

የአማፂያንን የጦር አውርድ ለመግታት ዜጎች በጋራ መቆም ይኖርብናል!
ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ

ዜና

የአማፂያንን የጦር አውርድ ለመግታት ዜጎች በጋራ መቆም ይኖርብናል!

የአማፂያንን የጦር አውርድ ለመግታት ዜጎች በጋራ መቆም ይኖርብናል!

ከ #ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ

ነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም

አንኳር

  • የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በቁጥጥሩ ስር ከነበሩ ቦታዎች ለቆ መውጠቱን ተከትሎ ኢዜማ ሰኔ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋ ባደረገው የቢሆንስ (Scenario) ትንተና፥ ሕወሃት ሀገራችንን ለማተራመስ ከሌሎች አክራሪ ብሔርተኞች ጋር ጥምረት መመስረት የሚችልበት ሁኔታ የሚፈጠር ከሆነ ለሀገራችን አንድነት እና ሰላም በራሱ ከሚፈጥረው አደጋ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ የውጪ ጠላቶች መሣሪያ በመሆን በሀገራችን እና በምንገኝበት ቀጠና ከፍተኛ አደጋ ሊደቅን እንደሚችል ገልፀን የኢትዮጵያ አንድነት እና ሰላም እንዲረጋገጥ የምንፈልግ ኃይሎች በሙሉ አቅማችን ተረባርበን አደጋውን እንድንቀለብስ ጥሪ አስተላልፈን ነበር።
  • የፌደራል መንግሥት ግዴታውን ከምንግዜውም በላይ በከፍተኛ ውጤታማነት መወጣት እንዲችል የወታደራዊ፣ የዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ የፕሮፖጋንዳ፣ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ማገዝ እንዲሁም የሀብት ማሰባሰብ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መሠራት ያለባቸው ሥራዎችን ስትራቴጂ እየነደፈ እንዲፈፀሙ ውሳኔ የሚያስተላልፍ «ብሔራዊ የሀገር ሉዓላዊነት እና የሕዝብ ደህንነት ማሰከበር ዘመቻ ግብረ ኃይል» ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ጭምር በማሳተፍ በአስቸኳይ እንዲያቋቁም እና ወደ ሥራ እንዲገባ እንጠይቃለን።
  • ከዚህ ቀደም እንደገለፅነው፥ የሀገር ሰላምን እና አንድነትን የማስከበር ኃላፊነቱ በዋነኛነት የፌደራል መንግሥቱ በመሆኑ አሁን የተደቀነብንን አደጋ ለመቀልበስ የሚወሰደው እርምጃ የዛሬውንም ሆነ የወደፊቱን ወቀሳም ሆነ የድል ሽሚያ ማስቀረት በሚያስችል መልኩ አንድ ወጥ የዕዝ ሰንሰለት ኖሮት በፌደራል መንግሥት እና በኢፌደሪ መከላከያ ሠራዊት አመራር ሰጪነት ብቻ መወሰድ እንደሚገባው አበክረን እናሳስባለን።
  • ሐምሌ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣነው መግለጫ፥ ሕወሃትን ደግፋቹኻል በሚል በጅምላ የሚወሰዱ እርምጃዎች ባስቸኳይ እንዲቆሙ እና በዚህ መልኩ የተወሰዱ እርምጃዎች አፋጣኝ ማጣራት ተደርጎባቸው የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ እንዲሁም አሁን ያለውን ሁኔታ እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የግል ጥቅም ለማግኘት ዜጎች ላይ እንግልት የሚፈፅሙ የመንግሥት እና የፀጥታ ሠራተኞች ላይ አስፈላጊው ማጣራት በአስቸኳይ ተደርጎ የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ መጠየቃችን ይታወሳል።

 አሁንም ቢሆን በሀገር አንድነት እና ሰላም ላይ የተጋረጠው አደጋ ለመቀልበስ የሚደረገው እርምጃ ዘላቂ አብሮነታችንን በማይጎዳ መልኩ ሕግ እና ሥርዓትን ተከትሎ መወሰድ እንዳለበት እያስታወስን የዜጎች ሁሉ ሰብዓዊ መብት ያለምንም ልዩነት በእኩል እንዲከበር የአደራ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

  • የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸውን ልዩነቶች ወደጎን በማለት የሀገር ህልውና ፈተና ላይ መውደቁን በቅጡ በመረዳት፤ አባሎቻቸውም የአማፂያኑን እብሪት ለማስተንፈስ በሚደረገው እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ጥሪ እንዲያደርጉ ከአደራ ጭምር እንጠይቃለን፡፡

ኢዜማ እንደ ሀገራዊ ፓርቲ የሀገር ህልውናን ለማስከበር እና የዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ በዚህ አጋጣሚ እያረጋገጠ በቀጣይ ከአባላት ጋር በመመካከር የሚያደርጋቸውን ተጨማሪ ነገሮች እንደተጠበቁ ሆኖ አሁን ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ከግጭቱ ጋር በተያያዘ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ እንዲውል ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ያስረክባል።

 

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top