Connect with us

የአዲስ አበባ ካቢኔ የመሬት አገልግሎቶችን አገደ

Social media

ዜና

የአዲስ አበባ ካቢኔ የመሬት አገልግሎቶችን አገደ

የአዲስ አበባ ካቢኔ የመሬት አገልግሎቶችን አገደ
(ውድነህ ዘነበ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርብ ነሐሴ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ለመሬት ተቋማት፣ ለመሠረተ ልማት ቅንጅት እና ግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን እንዲሁም ለ 11ዱም ከፍላተ ከተማ ባስተላለፈው ትዕዛዝ ፣ የመሬት እና መሬት ነክ አገልግሎቶች በሙሉ እንዳይሰጡ አገደ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት እና ካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ካሳሁን ወርቁ ፊርማ፣ አርብ ነሐሴ 7 ቀን 2013 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለከተው፣በከተማ ፣ በክፍለ ከተማ እንዲሁም በወረዳ ደረጃ የመሬት እና መሬት ነክ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ታግዷል።

የአቶ ካሳሁን ደብዳቤ የዕግዱን ምክንያት ሲያብራራ፣ አገሪቱን በገጠማት ወቅታዊ ችግር ምክንያት በየደረጃው ያለው አመረር ትኩረት አገር ማዳን ላይ ሆኗል። ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ የቆጠሩ ስግብግብ ግለሰቦች በአቋራጭ ለመክበር በመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ላይ ሲዘምቱ ተስተውሏል።

በዚህ ምክንያት ማንኛውም መሬትና መሬት ነክ አገልግሎት የታገደ ሲሆን ፣ በካቢኔ ካልተወሰነ በስተቀር ስድስቱም የመሬት ተቋማት ፣ ለሚ ኩራን ጨምሮ 11ዱም ከፍላተ ከተማ እና ግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን የመሬት አገልግሎቶችን እንዳይሰጡ ትዕዛዝ ተላልፏል።

የመሬት እና መሬት ነክ አገልግሎቶች የሚባሉት መሸጥ መለወጥ ፣ ካርታ ማውጣት፣ ሰነድ አልባ አገልግሎት ፣የጀርባ ማህተም፣ ስም ዝውውር፣ ግንባታ ፈቃድ እና የይካተትልኝ ጥያቄዎችን ያጠቃልላል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top