Connect with us

ትውልድን አጥፍቶ፣ ቀሪውን ሕዝብ የባርነት ቀንበር ለመጫን የመጣ አሸባሪና ወራሪ ጠላት እንደሕዝብ ሊመከት ይገባል!

ትውልድን አጥፍቶ፣ ቀሪውን ሕዝብ የባርነት ቀንበር ለመጫን የመጣ አሸባሪና ወራሪ ጠላት እንደሕዝብ ሊመከት ይገባል!
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

ዜና

ትውልድን አጥፍቶ፣ ቀሪውን ሕዝብ የባርነት ቀንበር ለመጫን የመጣ አሸባሪና ወራሪ ጠላት እንደሕዝብ ሊመከት ይገባል!

ትውልድን አጥፍቶ፣ ቀሪውን ሕዝብ የባርነት ቀንበር ለመጫን የመጣ አሸባሪና ወራሪ ጠላት እንደሕዝብ ሊመከት ይገባል!

አሸባሪው ትህነግ የአማራ ሕዝብ ላይ ያለሀጥያቱ “ሒሳብ አወራርዳለሁ” እያለ በሚዲያ ተናግሯል። በአደባባይ ዓለም እየሰማው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖል መግባት ካለበት እንደሚገባ ገልፆል። ትርክቱም ሆነ ድርጊቱ በእውን የማይታሰብ የእብደት ገጸ ባህሪ ቢመስልም ከመቼውም ጊዜ በላይ በግብር ትርክቱን ሊኖረው የጥፋት ሰይፉን በአማራና በኢትዮጵያ ላይ መዝዟል።

“የአማራ ሕዝብ ላይ ሒሳብ አወራርዳለሁ” ያለው ትህነግ፣ ሽብርና ወረራ ለሚፈፅሙለት የሽብር አባላቱ ምን አይነት ተልዕኮ እንደሰጣቸው ከምርኮኞች በምርመራ የሰበሰብናቸው መረጃዎች ያመላክታሉ።

በርግጥም ትህነግ በእብሪት በወረራቸው አካባቢዎች እየፈፀማቸው ያሉ ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በወንድም የአፋር ሕዝብ ላይ ተመሳሳይ የጥፋት ሰይፉን መዝዟል። በዚህም የአፋር ሴቶችን ደፍሯል፣ ሕጻናትንና ወጣቶችን ገድሏሎ፣ የአርብቶ አደሩን የቁም እንስሳት በገፍ ዘርፏል። የጠኔ ማወራረጃው አድርጎታል። አቅዶ የመጣውን ቂም በቀል በግልፅ በተግባር እያሳየን ነው።

በሌላ በኩል በየቀኑ ሲረግመው የሚውለውን የአማራ ልሂቅ ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳው ትህነግ፣  ነገ አድገው  አማራን ይጠቅማሉ ያላቸውን የአማራ ልጆች የማጥፋት ውጥን ይዟል። በዚህም ትውልዱን ለማምከን ባቀደው ክፉ እቅድ መሰረት በየከተማው ያገኛቸውን ታዳጊ ወጣቶች በራቸው ላይ ገድሎ ጥሏቸዋል። ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ ባለሀብቶች፣ ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች ላይ ትኩረት አድርጎ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከወሰነ ቆይቷል። 

የአእምሮ ህሙማንን በስለላ ሲያሰማራ የለመደው ትህነግ፣ ሁሉም እንደ እሱ መስሎትና  በህመም የሚሰቃዩትንም  በየደረሰበት አካባቢ ገድሏቸዋል። ከሚገድላቸው በተጨማሪ ሕዝብን በገፍ በማፈናቀል ከቀየው ተፈናቅሎ ተቅበዥባዥ ማድረግን፣ እረፍት መንሳትን የደስታው ምንጭ አድርጎታል። ሕዝብ ሲፈናቀልለት ከተማውን በሙሉ ዘርፎ ለማሸሸትም እድል እየፈጠረ ይገኛል።

 ትህነግ ትግራይ ክልል ውስጥ የሚኖሩትን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ለሚኖሩት የሽብር አባላቱና ተባባሪዎቹ አማራን ወርረው እንዴት ንብረቱን ዘርፈው ወደ ትግራይ እንደሚወስዱት  የዘረፋ ዕቅድ አውጥቷል። አንዳንድ የትግራይ ተወላጆችም ለአማራ ወዳጆቻቸው እስከ መስከረምና ጥቅም ባለው ጊዜ ያለቀው ኃይላቸውን አልቆ ወረራውን እንደሚያሳኩና የአማራን ሀብትና ንብረት ዘርፈው፣ የተረፈውንና መውሰድ የማይችሉትን አውደመው የአማራን ሕዝብ አደኸይቶ የመበቀል አላማ እንዳላቸው ገልፀውላቸዋል። ይህን መረጃ ከምርኮኞችና ከመረጃ ክትትላችን ማረጋገጥ ችለናል። 

የትህነግ አሸባሪ ኃይል አባል አልቆ አማራም ሆነ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል የሚልሰው የሚቀምሰው ማሳጣት የሽብር ቡድኑ ግብ ነው። ወትሮም በአማራ ቁልቁለት፣ በተዳከመች ኢትዮጵያ ታላቋን ትግራይ የመፍጠር ፖለቲካዊ ግብ ይዞ የተነሳው የጥፋት ኃይል፣ ዛሬ በመላ ኢትዮጵያውያን የደም ጎርፍ  ራሱን ነጻ ለማውጣት ጋኔሉን ከጠርሙሱ አስወጥቶታል። ዛሬ በአማራም ሆነ በአፋር ወረራና የሽብር ተልዕኮ ላይ የተሰማሩ የሽብር ቡድኑ አባላት ከጠርሙሱ የወጣው ጋኔል ተምሳሌት ናቸው። 

አሸባሪ ቡድኑ በወረራቸው የአማራና የአፋር አካባቢዎች የተደራጀ ኃይል አሰማርቶ የመንግስት ተቋማትን፣ የግል ንግድ ቤቶችን፣ የግለሰብ ንብረቶችን በከባድ የጭነት መኪናዎች እየጫነ ይገኛል። አጠቃላይ ግቡ የኢትዮጵያን ሕዝብ 100 ዓመት ወደኋላ መጎተት ነው። ይህን ደግሞ በአማራና በአፋር ክልሎች እንደሕዝብ ወረራ ፈጽሞ ጀምሮታል።

አሸባሪውና ወራሪው ትህነግ በእብሪት በወረራቸው የአማራና አፋር  አካባቢዎች የጀመራቸው የዘረፋና የጭፍጨፋ ወንጀሎች የወረራ አላማው ቢሳካለት በመላ ኢትዮጵያ ምን ሊያደርግ እንደሚችል እያስመሰከረ ነው። አነስተኛ የመንገድ ዳር ኪዮስኮች ሱቅ  ውስጥ ገብቶ ቁሳቁሶችን ዘርፎ ከመጫን በተጨማሪ በወረራቸው አካባቢዎች ያገኛቸውን ተሽከርካሪዎች በሎቬድ ጭኖ አይን ያወጣ ዘረፋ ውስጥ ይገኛል።

በሕግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት ሌሎችን በሐሰት ሲከስስ የነበረው አሸባሪው ትህነግ በወረራቸው የክልላችን አካባቢዎች ግን በግልፅ ዘረፋን የወረራው አላማ አድርጎ እየሰራበት ነው። ከአሸባሪው ተዋጊ አባላት ባልተናነሰ በኋላው ለዘረፋ በአደረጃጀትና በዕዝ የትግራይ ሴቶችንና አዛውንቶችን አሰልፏል። ታሪክ ይቅር ሊለው በማይችልበት ሁኔታ ከ70 ዓመት በታች ያለ የትግሬ ተወላጅ የወረራውና የዘረፋው ተሳታፊ እንዲሆን አደረጃጀት ተፈጥሯል፤ ስምሪትም ተሰጥቷል። 

“… ሂዱ አማራንና አፋርን እንዲሁም ቀሪዉን የኢትዮጵየሠ ህዝብ  ውረሩ፣ ሀብት ንብረቱንም ዝረፉ ኢትዮጵያንም አፍርሱ…” የሚል መመሪያ ከአሸባሪውና ወራሪው ትህነግ የወረደለት ኃይል፣ በተለይም በአሁኑ ወቅት የአማራንና አፋርን ክልሎች እንደአንበጣ በመውረር ላይ ነው። ይህ አደገኛ ተስፋፊ ኃይል እንደሕዝብ ካልተመከተ የጥፋት አድማሱን በማስፋት ኢትዮጵያን ወደታሪክ ሊቀይራት እንደሚችል ሕዝባችን ግንዛቤ መያዝ ይኖርበታል።

አሸባሪው አባላቱን ሲመለምል የተጣባውን ክፉ የአማራ ጥላቻ ትርክት ከመስበክ በተጨማሪ የአማራንና የሌላዉነሰ ኢትዮጵያዊ  ሀብት ዘርፈው ጥሪት ይዘው እንደሚመለሱ በማሳመን ጭምር ስለመሆኑ ምርኮኞች ላይ ባደረግነው ምርመራ ደርሰንበታል። ይህ ኃይል የወረራ አላማው  ሕዝብን እንደ ሕዝብ ማጥፋትን ዒላማ ያደረገ ነው። ከጭፍጨፋ የተረፈው ሕዝብ በድህነት ቀንበር እንዲኖር  የጥላቻ ጥግ የሆነ እቅዱን አስቀምጦ የመጣ በመሆኑ እንደሕዝብ ተነስተን ካልመከትነው በቀጣይ በአማራውና ሌላዉ ኢትዮጵያዊ ላይ ሊያደርሰው የሚችለውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ለመገመት ይከብዳል።

ስለሆነም አለም በቃኝ ያሉ አባቶች የሚኖሩባቸውን ገዳማት ጨምሮ ቤተ እምነቶችን ዘርፎ፣ ቀሪውን የሚያወድም ይህ አሸባሪ ኃይል ትውልድን ገድሎ፣ የአማራ ክልልና የኢትዮጵያ ሕዝብ በጥረቱ ያፈራውን ሀብት ዘርፎ ለመበቀል የያዘውን የዘረፋና የጭፍጨፋ አላማ በአጭሩ መቅጨት ያስፈልጋል።  ትውልድን አጥፍቶ፣ ቀሪውን ሕዝብ በባርነትና በድህነት እንዲኖር አቅዶ የመጣን ክፉ ጠላት እንደሕዝብ ተረባርቦ ማስቆም ታሪካዊ ግዴታችን ነው።

ትውልድን አጥፍቶ፣ ቀሪውን ሕዝብ የባርነት ቀንበር ለመጫን የመጣ አሸባሪና ወራሪ ጠላት እንደሕዝብ ሊመከት ይገባል!

ክተት መክት ለፍትሕ ለነጻነት!

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

ነሐሴ 09/2013

ባህርዳር-ኢትዮጵያ

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top