እድሉን ተጠቀም‼️
እድሉን ተጠቀም፣ ራስክን፣ ሕዝብህንና ሀገርህን አድን!
በምንም ተአምር ትህነግና ኦነግ ከፊት ሆነው በሚመሩት ኃይል ስር በሰላም ልትኖር አትችልም። ሰላሙን ተወው በሕይወት መኖር አትችልም።
በሕይወት ብትኖር እንኳ ከሰው በታች ሆነህ፣ ባርነትንም እንደ ፀጋ ቆጥረኸው መሆን አለበት! ንፁሃንን በየቀኑ ሲቀጥፉ የሚውሉ አሸባሪዎች ላይህ ላይ ወጥተው ምን እንደሚያደርጉ አይጠፋህም! መኖር አትበለውና፣ በሕይወት ከኖርክ ምድር ሲኦል ትሆንብሃለች!
~በእነዚህ ክፉዎች ስር ሆነህ አቅመ ቢስ ትሆናለህ። መሳርያ ብትል የትም አታገኝም። ባዶ እጅህን ይገርፉሃል። ከፊትህ ቤተሰብህን እደፈለጉ ያደርጋሉ፣ ከቤተሰብህ ፊት አንተን እንደፈለጉ ያደርጉሃል። ከእስር ቤትም መርጠህ “ይሄ ይሻለኝ ነበር” ብለህ እስር ቤት አማርጠህ “ከዚህ ባሰሩኝ” እንድትል ያደርጉሃል።
በአደባባይ ለአላማ መሰዋትማ ክብር ነው። ገድለው የትም ይጥሉሃል። ቤተሰብህ ህምጥ ትገባ ስምጥ እንዳያውቅ ያደርጉሃል። ድሮ አድርገውታል። የሚመጣው የከፋ ነው። በይፋ ገጥመሃቸው፣ አባረሃቸው ቂም ይዘውብሃል።
~ያኔ መደራጀት የሰማይ ያህል ይርቅሃል። መሳርያ ይዞ መታገል ዝም ብለህ የምትናፍቀው ይሆናል። ባርነትን ራሱ እንደ መልካም ነገር ትናፍቃለህ። “በሰላም መገዛት” ብለህ ታንቆለጳጵሰዋለህ። አታገኘውም። እድልህን ካልተጠቀምክ “በሰላም” ባርያ ሆነህ መኖርን እንደ ስጦታ የምታይበት ጊዜ ይመጣል። አንተን ማሰቃየት፣ ሕዝብህን ሰላም መንሳት፣ ሀገርህን ማናወጥ የሚዝናኑበት የቂም በቀል ጨዋታቸው ይሆናል።
~ ዛሬ “ሰልጥን፣ መሳርያ ያዝ” እየተባልክ ነው። የከፋው ከመጣ ይህን እድል መቸም አታገኘውም። አሁን ሰልጥነህ ታጥቀህ ትህነግንና ጀሌዎቹን ከመለስክ መከራህን ትቀንሳለህ። የሕዝብና የሀገርን መከራ ታቀልላለህ። የባሰ ቢመጣ መደራጀትንም፣ ወታደርነትንም ተምረሃል። የታጠከውን መሳርያ ይዘህ ፋኖ ትሆናለህ። ቢያንስ ራስክን፣ ቤተሰቦችህን ትከላከላለህ። በደንብ ከተደራጀህ ደግሞ የሕዝብህን ክብር ትመልሳለህ። እንዲያው ቢያንስ ቢያንስ ውትድርና ስልጠናው፣ መደራጀቱ በክፉ ዘመንህም ይጠቅምሃል።
በባርነት መሃል የነፃነት አማራጭ ለመፈለግ አይከብድህም። ሰማይና ምድር ተገናኝቶ፣ ሁሉም የጨለመ ያህል አይሰማህም። እድሉን ተጠቀምበት!
~በእነዚህ ክፉዎች እጅ ብትገባ ዝም ልትላቸው አትችልም። “በሰላም መገዛት” ራሱ ይናፍቅሃልና ትዘገያለህ እንጅ በእነሱ ላይ ማመፅህ አይቀርም። አሁን ካልተዘጋጀህበት ግን ነገ ላይህ ላይ ሲወጡ አደባባይ ወጥቸ ልቃወማቸው ብትል ደስታቸው ነው። በባዶ እጅህ በስናይፐር የተበረቀሰ ወገንህን አስከሬን ትሰበስባለህ። ያውም ከሰጡህ። አደባባይ ላይ በፈሰሰ ደም ስትቆዝም ትኖራለህ። ባዶ እጅህን ወጥተህ አይምሩህም።
በየአካባቢው ያለህን ሀብት ብታወድም፣ ሰልፍ ብትወጣ ለእነሱ ጉዳያቸው አይደለም። መግደያ ሰበብ ነው የሚያገኙልህ። ዛሬ በአደባባይ ታጠቅ፣ሰልጥን ተብለህ ነገ በስራቸው ሲያደርጉህ አደባባይ ወጥቸ እቃወማለሁ ብትል ኪሰራ ነው። በመሳርያ መፋለም እየቻልክ፣ ባዶ እጅህን ልትቃወማቸው የምትወጣበትን ሁኔታ አታመቻች።
ዛሬ በመሳርያ ተፋልመህ መልሳቸው እየተባልክ፣ ነገ መሳርያ ደግነውብህ፣ አንተ ባዶ እጅህን ለመፋለም ሁኔታ አትፍጠር። ሳትዘገይ፣ ሳትወላውል እድልክን ወስን። በአደባባይ ታጠቅ፣ ስልጥን ተብለሃል! ይህን ጊዜ አታገኘውም። ከተጠቀምክበት ሀገርና ሕዝብህን ታድናለህ። እንደዋዛ ካሳለፍከው የውርደት፣ የንቀት፣ የባርነት፣የጨለማ ዘመን ወዘተ ኑሮም “አሜን” ብለህ ጉልበት ስመህ የምትቀበለው የቂም በቀለኞች፣ የአጥፊዎችህ “ስጦታ” ይሆናል!
አስበው እስኪ! ትህነግ፣ ኦነግ፣ ከሱዳን እየሰለጠነ የሚጨፈጭፈው የቤንሻንጉሉ ቡድን፣ በቅማንት ሕዝብ ስም እየነገደ ሰው አግቶ ሚሊዮን ብር አምጡ የሚለው አሸባሪ፣ መቀሌ ሄዶ ኢትዮጵያን ሲረግም የከረመ ምድረ ተገንጣይ ስር ሆነህ? አስበው? ምድር ሲኦል ትሆንብሃለች!
እድሉን ተጠቀም!
“አሜን” ብለህ ለመኖር ከምትገደድበት ባርነት በእንዝላልነት አትግባ!
ምድርን ሲኦል ለሚያደርጉብህ ክፉዎች እጅህን አጣጥፈህ እድል አትስጥ!
ዛሬ ያገኘኸው እድል ነገ አይኖርም! ይናፍቅሃል!
እድሉን ተጠቅመህ ራስህን፣ ወገንህን፣ ሀገርህን አድን!
ከተደራጀህ ታሸንፋለህ! አማራጩ ማሸነፍ ብቻ ነው። መሸነፉን እንዳታስበው!(አማራ ፖሊስ ኮሚሽን)