Connect with us

“በአዲስ አበባ 73 በመቶ የምግብና መጠጥ ተቋማት በቀን፣ 95 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በማታ ትምባሆ ይጤስባቸዋል” ጥናት

Social media

ማህበራዊ

“በአዲስ አበባ 73 በመቶ የምግብና መጠጥ ተቋማት በቀን፣ 95 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በማታ ትምባሆ ይጤስባቸዋል” ጥናት

“በአዲስ አበባ 73 በመቶ የምግብና መጠጥ ተቋማት በቀን፣ 95 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በማታ ትምባሆ ይጤስባቸዋል” ጥናት

የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አዲስ አበባን ከትምባሆ ጭስ ነፃ የማድረግ ኢንሼቲቨ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01፣ 04 እና 10 የተሰሩ ስራዎችንና የተደረሰበትን አሁናዊ ሁኔታ አስመልክቶ ነሀሴ 3 ቀን 2013ዓ.ም ግምገማ አካሄደ፡፡

በግምገማው መድረክም የመቋሚያ ማህበረሰብ ልማት ድርጅት ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤልያስ ካላዩ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት አዲስ አበባን ከትምባሆ ጭስ ነፃ ለማድረግ ተግባራትን ለማከናወን ምቹ መኖሩን ጠቁመው አዲስ አበባን ከትምባሆ ጭስ ነፃ የሆነች ሞዶል ከተማን ለመፍጠር አዋጅ 1112/2012 በማስተግበርና ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ታመነ አጫሞ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣንና የመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ላሳዩት ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበው ከተማችንን ከትምባሆ ጭስ ነፃ ለማድረግ ከፍተኛ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ በመሆኑ በትጋት በመስራት የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ጠቁመው ህጉን ለማስተግበር የሚያስቸግር ሁኔታ እንደሌለ አብራርተው በተሰጣቸው ጊዜ ማስተካከያ በማያደርጉ ተቋማት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ በበኩላቸው በስራው ተነሳሽነት ላሳዩና በፋይናንስ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበው ኢትዮጵያ በትምባሆ ቁጥጥር ለውጥ እያስመዘገበች መሆኑንና በኢንሼቲቩ የተሰሩ ስራዎች ጥሩ መሆኑን ገልፀው በተቀናጀ ሁኔታ መስራት ከተቻለ ውጤት የማይመጣበት ምንም ምክንያት እንደማይኖር አብራርተው ለአንድ ዓላማ በመቆም ስነ ምግባር መኖር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የባለስልጣን መ/ቤቱ የጤና ተቆጣጣሪ ባለሙያ አቶ አሸናፊ ደመቀ እንደገለፁት በአራዳ ክፍለ ከተማ በተመረጡ ወረዳዎች አዲስ አበባን ከትምባሆ ጭስ ነፃ የማድረግ ኢንሼቲቨ 221 ተቋማት ላይ የዳሰሳ ጥናት መደረጉን ፣ 73% የሚሆኑት ምግብና መጠጥ ተቋማት በቀን 95% የሚሆኑት ምግብና መጠጥ ተቋማት ደግሞ በማታ ትምባሆ እንደሚያስጨሱ፣ በኢንሼቲቩ ያጋጠሙ ችግሮችን፣ የተገኙ ግንቶችንና የቀጣይ ስራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በጋራ ተባብሮ ለመስራት ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልፀው አጫሾች ወደ ተቋማት መጥተው ሲያጨሱ የተቋማት ባለቤቶች አታጭሱ በሚሉበት ጊዜ ፀብ እንደሚፈጠር ጠቁመው አጫሾች ላይ ከፍተኛ የሆነ የግንዛቤ ስራ መሰራት እንዲያስፈልግ ተናግረው አዋጁን ወደ ተግባር ለመቀየር ግለሰቦች ማጨስ ከማይፈቀዱ ቦታ ላይ ለሚያጨሱ ሰዎች አዋጁን ከማስተግበር አንፃር ክፍተት ስላለ በአዋጁ ላይ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታመነ አጫሞ እንዳሉት አዲስ አበባን ከትምባሆ ጭስ ነፃ የማድረግ ኢንሼቲቭ የተሰራው ስራ አበረታች ስለሆነ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመው ለአንድ ዓላማ በመቆም በተደረሰው ልክ ቁጥጥር በማካሄድ እርምጃ እየተወሰደ መሄድ እንዳለበት አብራርተው ህብረተሰቡን ማዕከል አድርጎ የሚሰራው ስራ በቂ ስላልሆነ ወደ ህብረተሰቡ መድረስ በምንችልባቸው መንገዶች በመጠቀም የማስተማር ስራ መሰራት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ታመነ አያይዘውም እርምጃ ለመውሰድ ጠንካራ ህግ ስላለ የወረዳና የክ/ከተማ አመራሮች ህጉን ለማስፈፀም ጠንክሮ መስራትና ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ (የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top