Connect with us

ሀገርን የማዳን ዘመቻው ስውር እንቅፋቶች የተገዙ የወሬ ቅጥረኞች ቢሆኑም እንደ ትህነግ ሴራቸው ዱቄት ሆኗል

Social media

ነፃ ሃሳብ

ሀገርን የማዳን ዘመቻው ስውር እንቅፋቶች የተገዙ የወሬ ቅጥረኞች ቢሆኑም እንደ ትህነግ ሴራቸው ዱቄት ሆኗል

ሀገርን የማዳን ዘመቻው ስውር እንቅፋቶች የተገዙ የወሬ ቅጥረኞች ቢሆኑም እንደ ትህነግ ሴራቸው ዱቄት ሆኗል

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

የትህነግ መሪዎች ስለናፈቃቸው ውስኪ፣ ስላልጠገቡት ሀገር ማውደም፣ ስላልቋጩት ጭቆናና ስቃይ ቁጭት ይዟቸው በሀሰተኛ ትርክት የትግራይን ወጣትና ገበሬ በውድም በግድም አሰልፈው ጦርነት ገጥመዋል፡፡

የፌዴራል መንግስት ዋሻ ካስገባቸውና ትምክህታቸውን ካፈረሰ በኋላ እየሆነ ያለው ነገር ለዚያ ምስኪን ገበሬ ረብ የሌለው በመሆኑ የጥሞናም የእርሻ ሥራ ወቅት ሰላም ጊዜም ለመስጠት በማሰብ ትግራይን ለቆ ወጥቷል፡፡

ከዋሻው የወጣው ሃይል ዳግም ወረራ ፈጽሟል፡፡ በአማራ ህዝብ፣ በፌዴራሉ መንግስትና በኢትዮጵያ ህልውና ላይ ክፉ እጁን ሰድዶ ሀገር አጠፋለሁ በሚል መንፈስ ጦርነት ላይ ነው፡፡ በዚህ ጦርነት የትህነግ ትልቁ ጉልበት እንደ ትናንቱ በኢትዮጵያ ካዝና ማዘዝ ሳይሆን ህዝብ መካከል የተሰገሰጉ ቅጥረኞቻቸውን መጠቀም ነው፡፡

አሁን ብርቱ ክንድ ሲያርፍባቸው ተቆርቋሪ መስለው የነጌታቸው ረዳን ጉልበትና ሃያልነት በየመንደሩ ለመስበክ የተቀጠሩ ሆድ አደሮችን አሰማርተዋል፡፡ ጦርነት ኪሳራ ቢሆንም ሀገር የማዳኑን ዘመቻ ከመምረጥ ይልቅ ሀገር እንዲፈርስ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ ተላላኪዎች በየሰፈሩ ታይተዋል፡፡

አንዱን ህዝብ ብዙ ቦታ ለማድረግ፣ በመከላከያና በክልል ህዝባዊ ሠራዊት መካከል መተማመን እንዳይኖር ወሬ በመንዛት፣ መሪዎች ስልጣን ይልቀቁ የሚል የጎጥ ዜማ በማቀንቀን ትህነግ ድል የምታገኘበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ይሰራሉ፡፡

አንዳንዶች ጥቁር አማራ የሚሏቸው እና በዚህ ሰዓት ነገሮች ሁሉ ባለመተማመን እንዲበላሹ ለማድረግ የሚደክሙ አልፈውም ጦርነቱ የብልጽግና ነው ብለው የአካባቢያቸውን ዘማች ለመጥራት የሚሞክሩ ከንቱዎችም ታይተዋል፡፡

እስከአሁን ባለው ሁኔታ ይሄ ሴራ እንደ ግንባሩ ውጊያ ሁሉ ድል ተነስቷል፡፡ በኦሮሚያ ያንን ሁሉ ጠባሳ የሚረሳ ወጣት ያለ ይመስል ከትህነግ ጎን የኦሮሞ ወጣት እንዲቆም ተቀጥረው የሚቀባጥሩት ሆድ አደሮች በተቃራኒም ብዙ ወጣቶች ሚሊዮኖች ለእናት ሀገራቸው በቁጭት እንዲነሱ ምክንያት ሆነዋል፡፡

ኦሮሚያ በሀገርን የማዳን ዘመቻው በትጥቅም በስንቅም በወታደርም አቅርቦት ቅዠታሞቹ ከተመኙት በተቃራኒው ሆኗል፡፡ በአማራም በየጊዜ ምሁሩም ባለሃብቱም ግንባር ወረደ እንጂ በወረደ ሞራል ስውር ሴራ የሚጎነጉኑት ቅጥረኞች አልተሳካላቸውም፡፡

የቅጥረኞች ዜማ፣ ከቅሶና እና ተክደናል ባይነት ቀሪዋ የትህነግ ጥይት ነበረች ተደምስሳለች፡፡ ትህነግ በአፋር እንደ ማይካድራው ሁሉ ዘር ማጥፋት ፈጽማለች፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ የከፋ አሸባሪነቷ ተረጋግጧል፡፡ ወጣቶችን በግድ አሰልፋ ለብዙዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆናለች፡፡

ለመቶ ሺህዎች መፈናቀል ሰበብ ከመሆን ባለፈ በለየለት መልኩ የትግራይ ህዝብ ለሁለት የምርት ዘመን ያለ እርሻ እንዲያሳልፋና ለረሃብ እንዲጋለጥ አድርጋለች፡፡

ከሰሜን እዝ ትግራይን ጠባቂ ሠራዊት ጭፍጨፋ እስከ ዛሬ ብዙ እድሎችን ሞክራለች፡፡ ሀገር ብታከስርም ወደ መቃብር እየወረደች ነው፡፡

የመጨረሻ የቀብር ሥነ-ሥርዓቷ ላይ ደግሞ ተላላኪ፣ ወሬ አናፋሽና አለመተማመን ፈጣሪ ቅጥረኞችን ለማሰማራት ብትሞክርም ነውራቸው ታውቆ ከስረው ህዝቡ ዛሬም አንድ መሆኑን አሳይቷል፡፡

የተለያዩ አካባቢዎች ሽፍታው ቡድን እያሸነፈ ነው ከሚለው ድል ነጋሪ መሳይ ስውር ደባ እስከ ህዝቡ በመሪዎቹ እንዳይተማመን እና መሪዎቹን ሊያጠፋቸው ካሰበው የትህነግ መሪ እኩል እንዲቆጥር በማሴር የተሞከሩ ደባዎች በአንድነትና በሀገር ፍቅር ዱቄት ሆነዋል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top