Connect with us

ከተፋሰሱ ስምምነት ዝንፍ ያላለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት !!

ከተፋሰሱ ስምምነት ዝንፍ ያላለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት !!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ከተፋሰሱ ስምምነት ዝንፍ ያላለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት !!

ከተፋሰሱ ስምምነት ዝንፍ ያላለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት !!

( ንጉሥ ወዳጅነው- ድሬቲብ )

 ሰሞኑን የኢትዮጵያ የዚህ ዘመን ትውልድ የሚኮራበት ታላቁ የህዳሴ ግድባችን (GERD) ሁለተኛ ሙሊት በተሳካ ሁነታ ተጠናቋል ፡፡ በዚህም በመጭዎቹ ወራት ቢያንስ ከሁለት ተርሚናሎች ሃይል የማመንጨቱ ስራ እንደሚጀመር ተነግሯል ፡፡

ኢትዮጵያዊን ከባንዲራ ፕሮጀክታችን የመጀመሪያዎቹን እሸቶች ስንቀምስ ግን  ፣ ጎረቤቶቻችን በተለይ የታችኛው ተፋሰስ አገሮችም ተቋዳሽ እንጂ ተጎጂ እንደማይሆኑ አሁን በሙሊቱ ወቅት የታዬው አልቦ ተፅኖ የውሃ ፍሰት አንድ ማሳያ  መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰሞኑን በድረገፃቸው አረጋግጠዋል ፡፡ይህ ደግሞ በናይል ተፋሰስ አገሮች ቀደሞ የተያዘ አቋም ነበር፡፡

 በመሰረቱ በናይል (አባይ) ላይ የሚካሄዱ ማናቸውም ፕሮጀክረቶች የዚህ ዘምን ትውልድ አሻራ ውጤቶች ናቸው ፡፡ ምስራቅ አፍሪካዊያኑ ህዝቦች “ናይል” በሚሉት ፣ በአብዛኛው የእኛ የተፈጥሮ ሀብት በሆነው አባይ ላይ በተፋሰሱ አገራት መካከል ጠንካራ  የትብብር ማዕቀፍ ለመፍጠር የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ የነበረውስ ካለፉት ሁለት አስርት አመታት ወዲህ አይደል እንዴ !?

በተለይ ለ10 ዓመታት( እ.ኢ.አ ከ1999- 2010 ገደማ) የዘለቀዉ የናይል ተፋሰስ አገራት ስምምነት ብዙ የተደከመበት  ነበር ። በአንፃራዊነት የላይኛው ተፋሰስ አገሮች መግባባትና ተፅኖ ማሳደር የጀመሩበት በእውቀትና በሙያዊ ብስለት ለመምከር ጥረት የተገደረገበት ወቅት መሆኑም ይታመናል ፡፡

በቀደሙት  ሥርዓቶች  በታችኛው ተፋሰስ አገራት በተለይም በግብጽና አጋሮቿ በነበረው ጫና፤በተለያየ ጊዜ በቀጠናው በተለይም በኢትዮጵያ በነበሩ መንግሥታት የአቅም ማነስ፣የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ተፅኖ መዳከም ምክንያት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ  የላይኛው ተፋሰስ  አገራት ህዝቦች  ከውሃው ተጠቃሚ ሳይሆኑ ዘመናት ማለፋቸው የሚታወቅ ነበር ።

ያ መድረክ ግን ቢያንስ ውሃው ሌሎች ባለቤቶችም አሉት ፣ የበይ ተመልካች ሆነው መቅረታቸውም ማብቃት አለበት የሚል መነሳሳትን ፈጥሯል ፡፡ 

በእርግጥ በርካታ ግብጻዊያን አባይ ከየት እንደሚነሳ መገንዘብ የጀመሩት ከተፋሰሱ አገሮች መክክር መጠናከርና ከኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጀመር ወዲህ ነው፡፡

የአፍሪካን ሶሳይቲ በመባል የሚታወቀው የግብጽ ተቋም ዳይሬክተር በየካቲት ወር 2019 ዓ.ም ግብፅን ለጎበኘው የአፍሪካ ጋዜጠኞች ቡድን ይህንኑ ሀሳብ መናገራቸውን ተፅፎ አንብቢያለሁ ፡፡ ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት 60 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ዐረብ ነን ብሎ ያምን ነበር፤ 40 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም ዓይነት አቋም አልነበረውም ።

በወቅቱ “ አባይ ሥሩ ኢትዮጵያ ፍሬው ግብጽ ነው” ያም ሆኖ ፣ ግብጽ አጠቃላይ ህይወቷ የተመሠረተው አፍሪካ ላይ መሆኑን እስከ መርሳት ደርሳ ነበር ፡፡ ከዚህ ሰመመን ነቅታ ፣ በዚያው በተለመደው የቅኝ ግዛት አስተሳሳብ እያቅማማችም  ቢሆን ለመደራደር የሞከረችው ከዚያ በሆላ መሆኑም የሚታወቅ ነው ፡፡

 የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ  አል ሲሲከዚህ ቀደም  ደጋግመው  “ ግብጽ ከአፍሪካ ተነጥላ  የኖረችባቸዉ  ዓመታት አግባብነት አልነበራቸውም ፤ ሥር መሠረቷን አስቷታል ፤ ለዚህም ቀላል የማይባል ዋጋ ከፍላለች “ የማለታቸዉ መነሻም ይሄዉ ጉዳይ ነበር የሚሉ ተንታኞች ትንሽ አልነበሩም ።

ይሁንና ግን የግብፅ መሪዎችም ሆኑ ፖለቲከኞች በወሬ እንጂ በገቢር ለዚህ እሳቤ ሲገዙ አለመታየታቸዉ ለናይል ተፋሰስ አገሮች ስምምነት ባአለመገዛት አሳይተዋል ፡፡ በእሱ ብቻ ሳይሆን በሶስትዮሽ ( ኢትዮጵያ ፣ሱዳንና ግብፅ) የድርድር መድረኮች ላይ ሁሉ  በሚያነሱት መንቻካና አደናቃፊ አቋምም ደጋግመው ማሳዬታቸው አልቀረም ፡፡ ቢያንስ ግን አሁን ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሁለተኛው ሙሊት እንኳን ምንም አይነት ጫና ባለመፈጠሩ ወደቀልባቸው ሊመለሱ ይገባቸዋል ፡፡ 

በዚህ ላይ የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ብቻ ሳይሆኑ  የመላዉ ዓለም የዉሃ ሃብት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ሞጋጆች የተሰማሙበት እዉነት መተግበሩን በስከነት መረዳት አለባቸው ፡፡ የአባይንም ሆነ የሌሎች አገራት አቋራጭ ( ድንበር ተሻጋሪ)  ወንዞችን  የዉሃ  አጠቃቀም ከግለኝነት ይልቅ በጋራና በሰጥቶ መቀበል መርህ ከመጠቀም ውጭ አማራጭ እንደሌለም መታመን አለበት ፡፡

ከዚህ አንፃር  በኢትዮጵያ ውስጥ ረጅም ግዛትን አቋርጦ  ለም አፈሯን እየጠራረገ የሚከንፈው የአባይ ወንዝ በግብጽ ተረጋግቶና የተለያዩ ጠቀሜታዎችን እየሰጠ መፍሰሱ ባይቀርም ፣ በኢትዮጵም ትልቅ ጥቅም (ለጎረቤቶችም የሚተርፍ የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲያመንጭ) መደረጉ ቅቡልንት ያለው ፣ ጥበበኛ ዉሳኔ መሆኑን መቀበል ግድ ይላል ፡፡

ኢትዮጵያዊያን  ዛሬም ሆነ ነገ ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድባችን ብቻ ሳይሆን በሁሉም የውሃ ፕሮጀክቶቻችን ከመላው የናይልል ተፋሰስ አገሮች ስምምነት ዝንፍ እንደማንል በተግባር መታየቱም የሚያኮራን ነው ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top