Connect with us

የጦር መኮንኖቹ ተመልሰዋል፤ አማራ ብልጽግናን “አሁን ደመቅህ የኛ አበባ” ማለት አሁን ነው!

የጦር መኮንኖቹ ተመልሰዋል፤ አማራ ብልጽግናን "አሁን ደመቅህ የኛ አበባ" ማለት አሁን ነው!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የጦር መኮንኖቹ ተመልሰዋል፤ አማራ ብልጽግናን “አሁን ደመቅህ የኛ አበባ” ማለት አሁን ነው!

የጦር መኮንኖቹ ተመልሰዋል፤ አማራ ብልጽግናን “አሁን ደመቅህ የኛ አበባ” ማለት አሁን ነው!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

እነሱ ካልዘረፍን ብለው ባኮረፉት ኩርፊያ ሌባ ነው ብለው በአደባባይ የነገሩን ጄነራል ዛሬ ጀግና ተብሎ የጦር መሪያቸው ሲሆን ሀገር ማፍረስ አይባልም፡፡ ሌላው ሀገር ለማዳን የሚያደርገው ሙከራ ሁሉ አንዴ ዘር ማጥፋት አንዴ ሌላ ስም ይሰጠዋል፡፡

ጄነራል ጻድቃን ሰፈሩን እንደሚወድ ሁሉ ጀኔራል ተፈራ ማሞ ሀገሩን ቢወድ ምን ሐጢአት አለው? እነሱ የህዳሴ መሃንዲስና የወርቅ አእምሮ ባለቤት የሚሉት መለስ ዜናዊ እኮ ነው ጻድቃን ገብረ ተንሳይ ጠባብ ብሔርተኛና ቦናፓርቲስት ነው ብሎ የነገረን፡፡ ዛሬ ጀግና ያሉት ስዬን ከእኛ ቀድማ ሌባ ነው ብላ ያሳመነቺን እኮ ህወሃት ናት፡፡

ግን ምንም ቢሆን ሀገር ለማፍረስና ኢትዮጵያን ለመጉዳት ሲሆን የተባባሉትን ጭምር ወደ ጎን አድርገው ጀግና ጀግና በመባባል አብረው ይሰለፋሉ፡፡ በሰውር እጆቻቸው ሌላ አንድ ሆኖ እንዳይታገላቸው ያደርጋል፡፡ የአማራን ስመ ጥር የጦር መኮንኖች በየምክንያቱ ከሙያቸው እንዲገለሉ ሲያደርጉ ኖረዋል፡፡

የአማራ ብልጽግና አሁን ትልቅ ስራ ሰርቷል፡፡ ሀገር የማዳኑን ዘመቻ ኑ እና ተቀላቀሉ ሲል የቀድሞ መኮንኖችን ጋብዟል፡፡ እሺ ብለው ጥሪውን ተቀብለዋል፡፡ የትናንቱ ዜና ደግሞ ብዙዎቹ ወሳኝ ሹመቶችን እንዳገኙ ይነግረናል፡፡ እውነት ነው፤ የእኛ ሰው በእነሱ እየተመራ አሸንፈዋል፡፡ የእኛ ሰው በእኛ ሲመራና ሀገሩን በሚወድ የጦር መሪ ሲመራ ውጤቱን ያዩታል፡፡

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሳያፍሩ በአደባባይ እየጨፈሩ፣ ሰንደቋን እረግጠው፣ ወታደሯን አርደው አይተናቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን ለማዳን ስንፈልግ ግን ሁሌን ስም ሊያወጡለትና ሊያሸማቅቁን ይሞክራሉ፡፡

ያ ምዕራፍ ከዚህ በኋላ ያበቃል፡፡ ኢትዮጵያ ምን ዓይነት ሀገር እንደሆነች የጥቂት ወንበዴ ምኞት አክሽፋ ህያው ስትሆን ያዩዋታል፡፡ ብዙሃኑ መስሎት የገባበት ማጥ ውጤቱን እያየ የሚወጣበት ስለሆነ አያሳስብም፡፡

አማራ ብልጽግና ግን በሰራው ስራ አሁን ደመቅህ የእኛ አበባ ተብሎ ሊዘፈንለት ይገባል፡፡ በጋራ ቆመው ሊያጠፉን ካሰቡ በጋራ ቆመን እንመክታለን፡፡ ለዚህ ነው ሲዳማው ሰሜን የገባው፣ ለዚህ ነው ኦሮሞው ግንባሩን ሊሰጥ ግንባር የደረሰው፣ ለዚህ ነው ደቡቡ ሱማሌው ጋምቤላው ቤኒሻንጉል ጉምዙ ሆ ብሎ የዘመተው፡፡

ሲጥሉን ኖረው፣ ሲያባሉን ከርመው አሁን ደግሞ ሲዖልም ቢሆን እንወርዳለን ብለው ዝተዋል፡፡ ምላሳቸው ከቤተ መንግሥት አብርሮ ዋሻ ያጎራቸው መሆኑን እንኳን ማሰብ አይፈልጉም፡፡ ጥጋብ አስጨፍሯቸው ስለ ረሃብ የሚያወሩ እንደሆኑ ግራ ይገባቸዋል፡፡ ንጹህ ህዝብ ይዘው ገደል እየገቡ እንደሆነ ማሰብ ስለማይፈልጉ በአደንዛዥ እጽ ሰክረዋል፡፡

ዓለም እውነቱን ነገ ያውቀዋል፡፡ ጥቂት ሌቦች ከያሉበት ተጠራርተው የተሰራቂውን አንገት ካልቀላን ያሉበት ዛቻ መልሶ ራሳቸውን በልቷቸዋል፡፡ ብቻችንን ለምን ብለው ህዝብ ይዘው እየጠፉ ነው፡፡ ብዙ ወጣት እያስጨፈጨፉ ነው፡፡ የሉዓላዊ ሀገር ህልውና አደጋ ውስጥ መክተትን ራስን ማዳንና ሉዓላዊነት ነው ይሉናል፡፡ 

ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በጋራ ቆመው የመጨረሻ እድላቸውን እየሞከሩ ነው፡፡ እንደ እነሱ ያልሞከርነው የነበረው ተባብሮ አብሮ መቆም ነበር አሁን ግን ጀመርን የአማራ ብልጽግና የሚያስመሰግን ስራ ሰራ፡፡ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top