Connect with us

አባዬ ከቻልክ ለሀገር ድምጽ ሁን፤ ካልቻልክ ዝም በል!

አባዬ ከቻልክ ለሀገር ድምጽ ሁን፤ ካልቻልክ ዝም በል!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

አባዬ ከቻልክ ለሀገር ድምጽ ሁን፤ ካልቻልክ ዝም በል!

አባዬ ከቻልክ ለሀገር ድምጽ ሁን፤ ካልቻልክ ዝም በል!

(ጫሊ በላይነህ)

መሐመድ አልአሩሲ ለሀገሩ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ነው፡፡ የማንንም ፈቃድ ሳይጠይቅ ስለሀገሩ፣ ስለአነታራኪው የአባይ ግድብ ግብጾችንና ሌሎች የዓረብ ሰዎችን ፊት ለፊት የተጋፈጠና እየተጋፈጠ ያለ ጀግና ነው፡፡ ለዚህ ጀግና መንግስት ዕውቅና ሰጥቶታል፡፡ በአሁን ሰዓት ብልጽግናን ወክሎ ለፓርላማ ከተመረጡ ሰዎችም አንዱ ሆኗል፡፡ 

ይህን ያስተዋሉ አንዳንድ ግለሰቦች “ለልጁ የተሰጠው ዕውቅና የተጋነነ ነው” በሚል ከንፈራቸውን ለትችት ሲያላቅቁ አያለሁ፡፡ ግን እኔ እጠይቃለሁ፡፡ እናንተ የመሐመድን ጠብታ ያህል ብትሰሩ የሀገሪቱ ገጽታ በምን ያህል ከፍ ሊል እንደሚችል አስባችሁታል ወይ እላለሁ፡፡

አሁን ማን ይሙት!.. አልጀዚራን፣ ቢቢሲን፣ ሲኤንኤን እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ስታዩ ኢትዮጵያ የወላድ መካን ናት ወይ የሚል ጥያቄ የሚያስነሱ ብዙ ነገሮችን ትታዘባላችሁ፡፡ መሐመድ ለምን ደጋግሞ አልጀዚራ አረብኛ ላይ በአስረጂነት የሚቀርብ ይመስላችሃል? መሐመድ ሚዲያ ወዳድ ስለሆነ ነው?…ስለፈለገና ወደሚዲያ መሮጥ ስለቻለ ነው? አይደለም፡፡ ሌላ ተጋፋጭ ሰው በብዛት ስለሌለን ነው፡፡ 

እውነታው ይኼ ነው፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝና ብዙ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ነኝ፣ ፕሮፌሰር ነኝ፣ ረዳት…ተባባሪ ፕሮፌሰር ነኝ፣ ዶክተር ነኝ፣ ዕጩ ዶክተር ነኝ…ከሚለውና በየተቋማቱ የጥናት ወረቀት ስራ እያሳደደ ኪሱን ከመሙላት ያለፈ ቁምነገር ከማይታየው ምሁር ተብዬ መሐመድ ሺ ጊዜ የበለጠ ለሀገሩ ጠቃሚ ሥራ ሰርቷል፡፡

እስቲ ጠይቁ፡፡ ለምን ጥቂት ኢትዮጵያውያን ብቻ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ደጋግመው ፊታቸው ይታያል? እንደግብጻውያን የተለያዩ ፊቶችን ለምን ማየት አልቻልንም? መልሱ ተመሳሳይ ነው፡፡ የሚጋፈጥ ምሁር፣ የሚጋፈጥ ካድሬና አባል፣ የሚጋፈጥ ሀገር ወዳድ ነኝ ባይ፣ የሚጋፈጥ አክቲቪስትና ተቆርቋሪ ነኝ ባይ በመጥፋቱ ነው፡፡

አሁንም ጠይቁ፡፡ በሚሊየን አባል ያለው ብልጽግናን ውሰዱ፡፡ በሰሞኑ ምርጫ ቅስቀሳው በትንሹ ሁለተኛ ዲግሪ የያዙ ሰዎችን በብዛት ማሰለፉን በኩራት ነግሮናል፡፡ 

ከእነዚህ ሰዎች መካከል ግን ብልጽግናን ደግፈው፣ ለሀገር ተቆርቁረው በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ ሲሟገቱ የምናያቸው ምን ያህሉን ነው? ሁለት በመቶ ይሞላልን? ምሁራኑ ስለአባይ፣ ስለኢትዮጵያ ሲናገሩ የማይሰማው ለምን ይመስልሃል? የቋንቋ እጥረት ስለገደባቸው? ሚዲያውን ስለማያውቁ? አለቆቻቸው ስላልፈቀዱላቸው? አይምሰልህ፤ እውነታው እሱ አይደለም፡፡ ብዙዎቹ ፓርቲውን ተጠግተው የሚፈልጉትን ሥልጣንና ጥቅማጥቅም ካሳኩ በኋላ እግራቸውን ዘርግተው መኖርን ስለሚመርጡ ነው፡፡ የምን አገባኝ ስሜት በውስጣቸው አድጎ ስለፋፋ ነው፡፡ አንዳንዶች ወጣ ወጣ ያለች ማሽላ አንድም ለወፍ፣ አንድም ለወንጭፍ ትዳረጋለችን እያቀነቀኑ በፍርሃት ተሸብበው መቀመጥን ስለመረጡ ነው፡፡

እናም በቅድሚያ መሐመድ አልሩሲ እና የእሱን መንገድ የተከተሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ያለአንዳች ቤሳቤስቲን በበጎ ፈቃደኝነት፣ የሸፈኑት ይህንን ግዙፍ ቀዳዳ መሆኑን ተረዳ፡፡ ጥቂት የማይባል ምሁር ነኝ ባይ ያልሞከረውን፤ ደፍረው በአደባባይ የቆሙት ሀገራቸውን ስለሚወዱ ብቻ መሆኑን አትርሳ፡፡

እናም ጀግኖቻችን በተግባር ስለግድባችን ተሟግተው ለግብጻውያንና ለዓለም ማህበረሰብ የኢትዮጵያን ሀሳብ ከፍ አድርገው ማሳየትና ማስረዳት ችለዋል፡፡ የግብጽ የውሀ መሐንዲስ፣ ተመራማሪ ምሁር ነኝ ባዩን ሁላ ፊት ለፊት ተጋፍጠው ለሀገራቸው ድምጽ መሆን ችለዋል፡፡

አባዬ ከቻልክ ለሀገርህ ድምጽ ሁን፡፡ 

አደባባይ ውጣና ተሟገት፣ በዓለም አቀፍ ቋንቋ ጻፍ፣ አስረዳ፡፡ ካልቻልክ ዝም በል!..የሚሰራ፣ የሚለፋ አታደናቅፍ!…ይኸው ነው፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top