Connect with us

ከ1ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች መንጃ ፍቃዳቸው ታገደ፡፡

ከ1ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች መንጃ ፍቃዳቸው ታገደ፡፡
ethio fm 107.8

ህግና ስርዓት

ከ1ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች መንጃ ፍቃዳቸው ታገደ፡፡

ከ1ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች መንጃ ፍቃዳቸው ታገደ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ህግ ተላልፈው ከባድ ጥፋት አጥፍተዋል ያላቸውን 1ሺህ 117 አሽከርካሪዎች መንጃ ፍቃዳቸው ማገዱን አስታዉቋል፡፡

መንጃ ፍቃዳቸው የታገደባቸው አሽከርካሪዎች 290 ሞት፣ 827 ከባድ ጉዳት ያደረሱ በመሆናቸው ነው መንጃ ፍቃዳቸው የታገደባቸው ተብሏል፡፡

የቢሮው የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ከዚህ በተጨማሪም የደህንነት ቀብቶን እና የህጻናት የደህንነት መደገፊያ በአሽከርካሪዎች መተግበሩን ለማጠናከር በተደረገው ቁጥጥር 4 ሺህ 443 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ስልክ እየተነጋገሩ ሲያሽከረከሩ የነበሩ 10 ሺህ 330 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዷልም ብለዋል፡፡

ቢሮው ከፍጥነት በላይ በአሽከረከሩ 1 ሺህ 20 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደም ቢሮው አስታውቋል፡፡

ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተብሎ ለብቻው በቀለም በተለዩት ከሜክሲኮ -ጀርመን፣ ከሜክሲኮ- ስታዲየም፣ ከለገሀር ፒያሳ፣ ከአንበሳ ጋራዥ ጎሮ እና ከላምበራት -ወሰን -ካራ ያሉ መስመሮችን ደንብ የማስከበር ተግባር ህጉን ተላልፈው በተገኙ 9 ሺህ አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱንም አቶ አረጋዊ ነግረውናል፡፡

በሶስት ምልክትና ማመላከቻዎች (መቆም የሚከለክል፣ ዩ ተረን የሚከለክል፣ አስገዳጅ ምልክት) ለማስከበር በተደረገው ጥረት ህግ ተላልፈው በተገኙ 30 ሺህ 011 አሽከርካሪዎች ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዷል ነዉ የተባለዉ፡፡

እንዲሁም 755 አሽከርካሪዎች የተሀድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ወደ ተቋም የተላኩ ሲሆን ከዚህ ውስጥ እግዳቸውን ያጠናቀቁና ስልጠና ወስደው የተመለሱ 437 አሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃዳቸው ተመላሽ እንደተደረገላቸውም ታዉቋል፡፡ ethio fm 107.8

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top