Connect with us

ደስ የሚል ምሽት ነበር!!! የኢንጂነሩ ሙግት ምርጥ ነበር!

ደስ የሚል ምሽት ነበር!!! የኢንጂነሩ ሙግት ምርጥ ነበር!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ደስ የሚል ምሽት ነበር!!! የኢንጂነሩ ሙግት ምርጥ ነበር!

ደስ የሚል ምሽት ነበር!!! የኢንጂነሩ ሙግት ምርጥ ነበር!

(ጌታሁን ሄራሞ)

  ኢንጂነር ስለሺ ሱዳን ረዘም ላለ ጊዜ ከጎናችን ሆና አሁን በቅርቡ አመሻሽ ላይ ከጎናችን ተለይታ ወደ ግብፅ እጥፍ ማለቷን የገለፁት “…and most recently Sudan…” በማለት ነበር፣ ካልተሳሳትኩ  ይህን ሐረግ ሁለቴ ተጠቅመዋል! በንግግር ወቅት አጠር ያለ ሲመነዘር ግን ብዙ ዕምቅ አቅም ያላቸውን ቃላት መጠቀም አንድ ነገር ሆኖ ያንኑ መደጋገም ደግሞ ኢላማውን በቀጥታ እንዲያገኝ ያግዛል። 

And  such repetition of a word or phrase for the sake of emphasis is called epizeuxis!  The phrase he used was highly critical of Sudan!

  ሌላው ያስተዋልኩት የኢንጂነሩን ቁርጠኝነት ነው፣ The delivery of the argument was full.of passion!!! ኢንጂነር ስለሺ እውነትን ስለያዙ ምንም ዓይነት የልምምጥና የመሽርኮመም ድባብና ድምፀት (Tone) ፊታቸውም ላይ አይታይም ነበር። ግብፅንና ሱዳንን ከንግግራቸው የበለጠ ይህ የሚያበግናቸው ይህ ይመስለኛል። 

“Delivery” ከንግግር ጥበብ (Rhethoric) አምስት አለባዎች አንዱ ነው። አንዳንድ ተናገሪ ጥሩ ይዘት ያለው ፅሁፍ ይዞ አቀራረብ ላይ ግን ይሾቃል!

የትናንተ ማታው የነግብፅ ሽንፈት ሥነ ልቦናቸው ላይ የሚያስከትለው ተፅዕኖ ስለሚኖር በቀጣይነት ለሚወስዱት እርምጃዎች ኢትዮጵያ ሳትዘናጋ በተጠንቀቅ መቆም አለባት።

የገጠሙን ፈተናዎችና ተግዳሮቶች የበለጠ አንድ እያረጉን ነው፤ አሁንም ለሀገራችን ሉዓላዊነትና ጥቅም በአንድነት እንቁም!

መልካም ቀን።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top