Connect with us

“ኢትዮጵያ አሸንፋለች!!”

"ኢትዮጵያ አሸንፋለች!!"
Photo: Social media

ማህበራዊ

“ኢትዮጵያ አሸንፋለች!!”

“ኢትዮጵያ አሸንፋለች!!”

(ፋሲል የኔዓለም)

የጸጥታው ም/ቤት የመጨረሻው ፍርድ ሰጪ አለማቀፍ ተቋም እንደመሆኑ፣ ግብጽና ሱዳን ከዚህ በኋላ የሚሄዱት ወደ እግዚአብሄር ብቻ ይሆናል ማለት ነው። እዛም ቢሆን የፍትህ አምላክ አያሳፍረንም።

የምክር ቤቱ አባላት ግብጽና ሱዳን ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለሱ መክረዋል። እንግዲህ ጥያቄው ባለ ሁለት ኮፍያ አገሮች ከአፍሪካ ህብረት ወጥተው ወደ አረብ ሊግ ተጠቃለው ይገባሉ ወይስ አንገታቸውን ደፍተው ወደ ህብረቱ ይመለሳሉ ወይ የሚለው ነው?

ጦርነት መቀስቀስ ወይም አላስፈላጊ የሆነ ማስፈራሪያ ማድረግም አለማቀፍ ወንጀል መሆኑ ተነግሯቸዋል። የሚፈልገውም ይህ ነበር።

የኢትዮጵያውያን ትህትናና የግብጾች ትዕቢትና ድንፋታ በአለም መድረክ ላይ ታይቷል። ኢ/ር ስለሺ ስላቀረቡት እጥር ምጥን ያለ መከራከሪያ አድናቆታችን እንገልጻለን።

የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሽንፈታቸውን ለመደበቅ ቢሞክሩም፣ አለም በቀጥታ የተከታተለውን እውነት መደበቅ አይቻልም። ኢትዮጵያ አሸንፋለች።

የኢትዮጵያን ወኪሎችና የጸጥታውን ም/ቤት አባላትን እናመሰግናለን።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top