Connect with us

የድንገተኛ አደጋዎች እና የጽኑ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ማሻሻያ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በይፋ ተጀመረ 

የድንገተኛ አደጋዎች እና የጽኑ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ማሻሻያ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በይፋ ተጀመረ
ጤና ሚኒስቴር

ዜና

የድንገተኛ አደጋዎች እና የጽኑ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ማሻሻያ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በይፋ ተጀመረ 

የድንገተኛ አደጋዎች እና የጽኑ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ማሻሻያ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በይፋ ተጀመረ 

 የጤና ሚኒስቴር ለዜጎች የሚገባቸውን ወቅታዊና ያልተቆራረጠ እንዲሁም ጥራቱን የጠበቀ የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ህሙማን እንክብካቤ ተደራሽ ለማድረግ ከተያዘው ስልት እንዱ ዛሬ ለሁለተኛ ዙር ይፋ እየተደረገ የሚገኘው ማሻሻያ ፕሮግራም የማስጀመር መርሀ ግብር  ነው፡፡

በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባደረጉት ንግግር ሁለተኛው የጤናውን ሴክተር ትራንስፎርሜሽን እቅድ /HSTP / በማዘጋጀት ወደ ስራ የተገባ መሆኑን በመጥቀስ የጤና ስርዓቱን ምላሽ ሰጪነት ለማሻሻል እንዲሁም ድንገተኛ አደጋ መቋቋም የሚችል  የጤና ስርአት በመፍጠር ዜጎችን ከድንገተኛ የጤና አደጋ መጠበቅና ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን ተደራሽ ማድረግ ዋና አላማ ያደረገ በመሆኑ የድንገተኛ አደጋዎች እና የጽኑ ህክምና የአምስት ዓመት እቅድ በማዘጋጀትና የሚመለከታቸውን ባለድርሻ በማሳተፍ ወደ ስራ የተገባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

ዶ/ር ሊያ ታደሰ አያይዘውም ይህም ከክልሎች ጤና ቢሮ፤ የከተማ አስተዳደሮችና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት በከተሞች ውስጥ በሚገኙ ጤና ተቋማት ላይ ማሻሻያ እየተሰራ እንደሚገኝ በመጥቀስ ባለፉት ሁለት ዓመታትም በተመረጡ አምስት ከተሞች ላይ ፕሮግራሙ እየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ 

በሀገራችን በከተሞችና በኢንዲስትሪዎች መስፋፋት፤በመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችና በከፍተኛ የህዝብ ቁጥር መጨመር፤ የኑሮ ዘይቤ መለወጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መበራከት በዋና ዋና ከተሞች ውስጥ የድንገተኛ አደጋዎችና ድንገተኛ ክስተቶች መጨመር ይህን የማሻሻያ ፕሮግራም በከተሞች ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራበት ዋና ምክንያቶችም መሆናቸውን ተጠቅሷል፡፡

የድንገተኛ አደጋ እና የጽኑ ህክምና አገልግሎቶችን አስመልክቶ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና በቅንጅት መስራት አነስተኛ መሆን ፤የቅድመ ዝግጅት ስራ በጤና ተቋማት አነስተኛ መሆን ፤ በድንገተኛ እና ጽኑ ህክምና የሰለጠኑ ባለሙያዎች እጥረት፤ ለአስቸኳይ የጤና ክብካቤ አገልግሎቶች የሚውል ዘላቂነት ያለው የፋይናንስ ስርዓት አለመጠናከር የነበሩ ዋና ዋና ችግሮች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በመሆኑም በነዚህም ከተሞች የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማካተት የማሻሻያ ፕሮግራሙን ወደ ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ለማስፋት የሁለተኛው ዙር የዋና ዋና ከተሞች የድንገተኛ አደጋ እና የጽኑ ህክምና  ማሻሻያ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በስምንት ከተሞች  በይፋ ለማስጀመር ቁልፍ ባለድርሻ አካላት በተለይም የከተማ አስተዳደር ፤ የክልሉ ጤና ቢሮዎች፤ ዩኒቨርሲቲዎች  ፤በተገኙበት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ 

በፕሮግራሙም የክልል ጤና ቢሮ ሀላፊዎች፤ የከተማ መስተዳድር ከንቲባዎች የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች እና የሆስፒታል ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡(ጤና ሚኒስቴር)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top