Connect with us

ዶናልድ ትራምፕ አፈና አድጋችሁብኛል ሲሉ ፌስቡክ፣ ጉግል እና ትዊተርን ከሰሱ

ዶናልድ ትራምፕ አፈና አድጋችሁብኛል ሲሉ ፌስቡክ፣ ጉግል እና ትዊተርን ከሰሱ
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንሰቲትዩት

ዜና

ዶናልድ ትራምፕ አፈና አድጋችሁብኛል ሲሉ ፌስቡክ፣ ጉግል እና ትዊተርን ከሰሱ

ዶናልድ ትራምፕ አፈና አድጋችሁብኛል ሲሉ ፌስቡክ፣ ጉግል እና ትዊተርን ከሰሱ

የቀድሞው የአሜሪካን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያለ አግባብ ድምፄን አፍናችኋል በማለት በፌስቡክ፣ ትዊተር፣ እና ጉግል ላይ ክስ መመስረታቸውን አስታወቁ፡፡ በካፒቶሉ ነውጥ የተነሳ የማህበራዊ ገፆቻቸውን ማገዳቸውን ተከትሎ ለወራት ከነዚህ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር እሰጣገባ ውስጥ የቆዩት የ75 ዓመቱ ሪፐብሊካን ተቋማቱ ሕገ-ወጥ እና ሕገ-መንግስታዊ ያልሆነ አፈናን ወደማድረግ ተሸጋግረዋል ሲሉ ወቅሰዋቸዋል፡፡

ፌስቡክ የካፒቶሉ ነውጥ በተነሳ በማግስቱ ነበር ነውጡን አነሳስተዋል ሲል የቀድሞ ፕሬዘዳንቱን የፌስቡክ ገፅ ያገደው፡፡ ብዙም ሳይቆይ ትዊተርም ይህን የፌስቡክ ውሳኔ በመከተል ተጨማሪ አመፅ እንዳይነሳ ያሰጋል በሚል ምክንያት እንዲሁ አግዷቸዋል፡፡ በገለልተኛ ቦርድ አማካኝነት ውሳኔውን መለስ ብሎ የተመለከተው ፌስቡክ ታድያ የዛሬ ወር ገደማ እገዳውን በ2 ዓመት ማፅናቱ ይታወሳል፡፡ ከነዚህ በተጨማሪም ዩትዩብ እና ባለቤት ድርጅቱ ጉግል ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዙ ተንቀሳቃሽ ምስሎቼን አጥፍተዋል ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ይከሳሉ፡፡

ጉግል፣ ፈፌስቡክ እና ትዊተር አባል የሆኑበት የኮምፒውተር እና ኮምዩኒኬሽን ሕብረት የዲጂታል አገልግሎት ሰጪዎች የራሳቸውን ደንቦች ተፈፃሚ የማድረግ መብት እንዳላቸው ይናገራል፡፡ በአንፃሩ ደቡባዊ ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት ክሳቸውን ያቀረቡት ዶናልድ ትራምፕ “ማሸነፍ የምንችልበት ሙግት ውስጥ ነው የገባነው” ብለዋል፡፡ አክለውም ይህ ገና ጅማሮው ነው ባሉት ክስ “ስለ እያንዳንዱ አሜሪካዊ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመቆም ለአሜሪካን ዲሞክራሲ እየቆምን ነው” ብለዋል፡፡

ሆኖም በሕገ አዋቂዎች ዘንድ ክሱ ያን ያህል ፍሬ አያፈራም የሚል አስተያየትን አስተናግዷል፡፡ በሳንታ ክላራ ዩኒቨርሲቲ የሀይ ቴክ ሎው ኢንስቲትዩት ዳይሬክተሩ ኤሪክ ጎልድማን እንደሚሉት በህገ መንግስቱ ላይ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ጭምር የሚደነግጉት የመጀመሪያ ማሻሻያ ተብለው የሚታወቁት የሕግ ማዕቀፎች የመንግስት አካላትን እንጂ የግል ተቋማትን አይመለከቱም በማለት ከዚህ ቀደም ሌሎች ተመሳሳይ ክሶችም ውድቅ መደረጋቸውን በምሳሌነት ያነሳሉ፡፡ 

ዶናልድ ትራምፕ ያነሱት ክስ ታድያ እገዳውን ያስተላለፉት የቴክኖሎጂ ተቋማት ከፌደራል መንግስቱ ጋር በትብብር እንደመስራታቸው ስፍራቸውን ከግል ኩባንያነት ወደ ሀገራዊ ሚና ተጫዋችነት ተሸጋግረዋል ሲል ይሞግታል፡፡(የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንሰቲትዩት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top