Connect with us

” በሰላም ቤቴ ተመልሻለሁ ! “

" በሰላም ቤቴ ተመልሻለሁ ! "
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

” በሰላም ቤቴ ተመልሻለሁ ! “

” በሰላም ቤቴ ተመልሻለሁ ! “

(ፍሬወይኒ ገ/ፃዲቅ)

ሐሙስ ሰኔ 24 ማለዳ 2 ሰዓት ላይ ከቤቴ ከተወሰድኩበት ሰዓት ጀምሮ እስከ ትላንትናዋ ቀን ድረስ ያለሁበትን ቦታ የሚመለከተው አካል እንዲያሳውቅ ድምፅ ለሆናችሁኝ ወዳጆቼ በሙሉ ላመሰግናችሁ ቃላት ያጥረኛል!!!

ስለ እውነት ድምፃችሁ ያበረከተልኝን ውለታ የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ።

ፌደራል ፖሊስ በተሰጠው ጥቆማ መሰረት ስራውን ነው የሰራው። ስህተቱ ያለሁበትን ቦታ ማሳወቅ ባያስፈልግም እንኳን ቢያንስ ለቤተሰቦቼ በመንግስት የፀጥታ አካላት እጅ ላይ ስለመሆኔ በማሳወቅ ከስጋት ነፃ እንዲሆኑ አለማድረጋቸው ብቻ ነው።

ለማንኛውም ለደህንነት እና ፌደራል ፖሊስ በግል ፀብ እና ጥላቻ ተነሳስቶ ባለው ቅርበት በቂም በቀል የሐሰት ጥቆማ ሰጥቶ እንዲህ ከባድ ስህተት ውስጥ የከተታቸው እና እኔን ከነቤተሰቦቼ እንዲሁም ጓደኞቼ ለስጋት እና መንከራተት የዳረገን ግለሰብ ማንነት ታውቆ የሚመለከተው አካል ተገቢውን ስራ በመስራት ላይ ይገኛል።

“ትግሬ በመሆኗ ነው የታሰረችው” የሚል የፖለቲካ ሸቀጥ ለመሸቀጥ የተጋጋጣችሁ አካላትም እንደነበራችሁ በተወሰነ መልኩ ተመልክቻለሁ።

ሆኖም ጠቋሚዬ ከዚህ ቀደም የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አመራሮች በክልሉ የተረጋጋ ስራን እንዳይሰሩ ሲረብሽ ሲሳደብ እና ሲያንጓጥጥ የነበረ እንዲሁም በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ወጣቶችን በቆየ የግል ቂሙ ተነሳስቶ የፀጥታ አካላትን በተመሳሳይ እያሳሳተ በማሳሰር ወጣቱ በስጋት በመሸሽ ወደ በረሃ እንዲሄድ የማማረር ተግባር ላይ የተሰማራ የኛው የትግራይ ተወለጅ ወጣት ነው።

ድምፅ ሆናችሁ የት እንዳለሁ ላልሰሙ ከፍተኛ የመንግስት አካላት እንዲሰሙ እንዲሁም በፍጥነት ጉዳዬ ተጣርቶ ካለሁበት እንድለቀቅ ለታገላችሁልኝ ለደነገጣችሁልኝ ላዘናችሁልኝ ውድ ኢትዮጵያዊያን ወዳጆቼ ግን ክፉውን ፈጣሪ ይጋርድላችሁ!!!

 ተጠርጥሬ የተከሰስኩበት ወንጀል ደግሞ

1 በሶሻል ሚዲያ እና በሁሉም የማህበራዊ ድህረ ገፅ ትስስርን በመጠቀም ብሔርን ከብሔር ማጋጨት ተግባርላይ በመሰማራት ህገመንግስትን በሀይ ለመናድ በድረ ገፅ ላይ ሽብር በመንዛት የሚሉ ናቸው። እኔ በጣም በመሳቅ ተገቢውን ምላሽ ሰጥቻለሁ በመጨረሻ የፌደራል ፖሊስ ባደረገው ማጣራት እና ሌሎች መረጃዎችን በማግኘቱ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቀውኝ ትላንት ማምሻውን ከነበርኩበት ቦታ ቤቴ አድርሰውኛል። ይህው ነው!!!

      ፈጣሪ አገራችንን ይባርክ!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top