Connect with us

ራስ ዱሜራ ደሴቶችን  ለኢትዮጵያ መመለስ….

ራስ ዱሜራ ደሴቶችን ለኢትዮጵያ መመለስ….
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ራስ ዱሜራ ደሴቶችን  ለኢትዮጵያ መመለስ….

ራስ ዱሜራ ደሴቶችን  ለኢትዮጵያ መመለስ….

(እስክንድር ከበደ ~ ድሬቲዩብ)

የጂቡቲ እና ኤርትራ የድንበር ውዝግብ የተጀመረው እ.ኤአ በሚያዚያ 16/2008 ነበር:: በወቅቱ የኤርትራ ጦር በጂቡቲ ግዛት ዘልቆ ምሽግ መቆፈሩን በመጥቀስ አቤት ማለቱን ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት እ.ኤእ ሰኔ 10 እስከ ሰኔ13 /2008 የዘለቀ ግጭት ውስጥ ገቡ።

ኤርትራ የጂቡቲ የድንበር ስፍራ የሆነችውን ራስ ዱሜራን ለሁለት አመታት በቁጥጥር ስር አድርጋ ቆየች።እኤእ በ2010 የሁለትዮሽ ድር ድር ለማድረግ አካባቢውን ለቃ ወጣች።የኳታር ወታደሮች የሰላም አስከባሪ በመሆን ራስ ዱሜራን በተቆጣጠሪነት እዛው ስፈሩ።

ራስ ዱሜራ (Cape Doumeira) በቀይ ባህር 1.5 ኪሎሜትር የሚሽፍንና ባህረ ስላጤውን የሚከፍል አወዛጋቢ ስፍራ ነው፡፡በእኤአ1900 የተፈረመው ፕሮቶኮል የአለም አቀፍ ድንበር ሆኖ ከወታደራዊ ቀጠናነት ነጻ እንዲሆን ጣሊያንና ፈረንሳይ መስማማታቸው ይነገራል፡፡

በ1935 አመተ ምህረት  ግጭት ተከትሎ ሁለቱ ሃያላን ባካሄዱት ስምምነት ራስ ዱሜራን ኮረብታዎች ባይካለልም ስሜናዊ ቁልቁለቱን ለጣሊያን ሆኖ ደቡባዊ ቁልቁልቱን ደግሞ ፈረንሳይ እንድትይዝ ነበር።

እ.ኤ.አበ2008 ኤርትራ ለመንገድ ሰራ አሽዋ ለመውስድ ነው በሚል ሰበብ ድንበር ተሻግራ ስፍራውን ያዘችው።ሚያዚያ 16 ጂቡቲ ለተባበሩት መንግስታት  ድርጅት የጽጥታው ምክር ቤት ኤርትራ በራስ ዱሜራ አቅራቢያ በሁለቱም የድንበር አካባቢዎች ምሽግ እየገነባች ነው የሚል ክስ አቀረበች፡፡

ጂቡቲ ለፀጥታው ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤም ፤ኤርትራ በአዲሱ ካርታዋ ራስ ዱሜራን እካታለች የሚል ነበር፡፡

የኳታር አደራዳሪነት ብዙም ሳይሰማ ቆይቶ ሀገሪቱ ከባህረ ስላጤው ጋር በገባችበት ውዝግብ “በማሳበብ” ራስ ዱሜራን ከሰባት አመታት ቆይታ በኋ ጦሩ ሹልክ ብሎ መውጣቱን ተከትሎ የኤርትራ ጦር አካባቢውን ተቆጣጠረ። ይህ ድርጊት ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም አለው። ´´

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በወቅቱ የኤርትራ ድርጊት ለመላው የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ጽጥታ አደጋ ነው…´´ ብለው ነበር። ኢትዮጵያ በጂቡቲ የሚገኘውን የንግድ ኮሪደሯን  ደህንነት ለማረጋገጥ  ወታደራዊ እርምጃ  እስከመውሰድ እንደምትጌድ ጠቁማለች።

መለስ ዜናዊ የአልጀርሱን የድርድር ስምምነት በመርህ ደረጃ መቀበላቸውን ባለአምስት ነጥቦች ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ ”ሰጥቶ መቀበል ” የሚል ማብራሪያ ለህዝብ ተወካዮች አቅርበው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይህም ማለት የውዝግቡ ማዕከል የሆነችውን ”ባድመን” መስጠት ቢኖር እንኳን ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ሊፈጥር የሚችል ክፍተቱ በዚሁ የዱሜራ በኩል መፈጠሩ አይቀርም ነበር፡፡  ይሄን ”ሰጥቶ መቀበል” አሁንም እልባት ያገኘ አይደለም፡፡ ኤርትራ እግሯን አንፈራጣ፤ጂቡቲ ድግሞ ከኤርትራ ጋር እግሯን ዘርጋት በማጋጠም ከባህሩ እንደከለሏት ማጤን ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦርነት ጉዳይ  የግጭቱ መነሻ የ”ባድመ” የተባለችው ቦታ የገነነ ትኩረት ቢሰጣትም፤ ”የድንበር ማካለሉ መሬት ላይ ሲሰመር አሰብን በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ኢትዮጵያ የማያካልልበት ምክንያት የለም፡፡   

በኤርትራና በጂቡቲ መካከል  በመሀል ሰንጥቆ የሚወጣ ጠባብ ኮሪደር ላይ አዲስ ወደብ የሚያስገነባ ሰርጥ ወይም ደሴት የሚያስገኝ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ አካባቢውን የሚያውቁ እንደሚናገሩት በኤርትራና በጂቡቲ መካከል የሁለቱም ያልሆነ 15 ኪሎሜትር ጨምሮ ፤ኤርትራ ነጻ ከወጣች ከ17 አመታት በኋላ  የራስ ዱሜራና የዱሜራ ደሴቶች  የገባችው  ጥያቄ ያስነሳል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ኮሪደር ለመያዝ እያደባ  የነበረ ቢሆንም፤የድንበር መካለሉ እልባት አለማግኘቱ እክል ፈጥሮበት እንደሚሆን መጠርጠር ይቻላል፡፡

ኤርትራ  አዲስ ካርታ መስራቷና ራስ ዱሜራንና ደሴቶቹን ማካተቷን ለጂቡቲ መረጃ የሰጣት  የኢትዮጵያ መንግስት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በመርህ ደረጃ ተቀበልኩት ያለቸውን የአልጀርሱ ስምምነት መሬት ላይ በሚካሄደው መካለል ባድመን ብትስጥም፤የቀይ ባህር መውጫ በር ኮሪደር የሚፈጥር አከላለል መኖሩ አይቀርም ነበር፡፡

ይህ ደግሞ  ከ2017 አመተ ምህረት ጀምሮ  ግብጽ፣ሳኡዲአረቢያ፣ባህሬን፣የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ሌሎች  ከኳታር ጋር የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ግንኙነት በማቋረጣቸው ፤ ዶሃ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ ማስገባት የምትችልበት ሀማድ የተሰኘ ወደብ ገንብታ ማስመረቋ ትልቅ ትምህርት ይሰጣል፡፡ ማክሰኞ በዶሃ በተካሄደው የአረብ ሊግ ስብሰባ የግብጽና የኳታር ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ አርሚ ዋር ኮሌጅ The United States Army War College (USAWC) የአሜሪካ ወታደራዊ የጦር አዛዦች ኮሌጅ ነው።ይህ በ2ስኬየር ኪሎሚትር ያረፈ ግዙፍ ኮሌጅ ካርሊዝል ፔንሲልቪኒያ ይገኛል።ስመጥሩ ኮሌጁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪሎች ይሰጣል።በኮሌጁ ቦርድ ተቀባይነት የሚገኙት በኮሎኔልና ሌተና ኮሎኔል ደረጃ የደረሱ ከፍተኛ የጦር አዛዦችን ናቸው። 

በአንድ ጊዜ 800 ወታደራዊ መኮንኖችን በሁለት አመት ተኩል ጊዜ ግማሹን በርቀት ቀሪውን በግንባር ተገኝተው ምርምር ያደርጋሉ።በዚሁ ዝነኛ የጦር ኮሌጅ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ1991 “የባብኤል መንደብ ስትራቴጂክ ጠቀሜታ” “በሚል የየመን ኮሎኔል ያጠኑት ኘሮጀክት በቀይ ባህር ላይ ጂቡቲ 2 ደሴቶች፤ ኢትዮጵያ ደግሞ 4 ደሴቶች እንዳሏት ይገልጻል።

በዚህ ሰነድ ላይ የዱሜራ ደሴቶች የኢትዮጵያ መሆናቸውን የሚጠቅስ ሲሆን ጂቡቲ ባለቤትነት እንደሌላት ያሳያል።ኢትዮጰያ በዝምታ ያለፈቻቸውን ይህን ስትራቴጂክ ደሴቶች የኤርትራና ጂቡቲ ጉዳይ ብቻ አድርጎ መዉሰድ የሀገሪቱን ጥቅሞች አሳልፎ መስጠት እንዳይሆን ። 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኤርትራ  ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አስመራ በተገናኙበት የመጀመሪያ ቀን” የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነትን ደርቤ እሰራለሁ ” አሉ፡፡ ኢሳያስን ያስፈገገው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንገተኛ አባባል የገባን፤ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማአቀብ ሲያስነሱ ነበር፡፡

 በወቅቱ ጂቡቲ ኤርትራ መሬቴን ይዛለች በሚል ማአቀቡ እንዳይነሳ ያደረገችውን ተቃውሞ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራ ልኡክና የሱማሊያ ልኡካን ቡድን በመላክ የጂቡቲን አቋም በማለሳለስ ከኤርትራ ላይ ማአቀቡን አስነስተዋል፡፡  

ይህ የኢትዮጵያ መልካም ዲፕሎማሲ  በይዞታው ላይ ህጋዊ ጥያቄ ማንሳት የሚከለክላት ነገር ባይኖርም፤ አስመራና ጂቡቲ የራስ ዱሜራ ደሴቶችን  ከእኛ ይቅር ብለው መስጠት ይችላሉ፡፡

ከሩቅ ሀገራት ጦር እንዲሰፍር የምትፈቅደው ጂቡቲም ሆነች ኤርትራ የቀኝ ገዢዎችን ሀተታ ጠቅሰው “የኛ ብቻ ነው “የሚሉበት አካሄድ የለም ።ኤርትራም ብትሆን ይህን ስትራቴጂክ ቦታ ነጻነቷን ካገኘች 14 አመት በኋላ ምን ትዝ ብሏት ወረረችው? ጂቡቲም ቢሆን ይህንን “ባለቤት አልባ” ስፍራ አምርራ ለምን  ፈለገችው? ወዘተ ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ። ስለዚህ የራስ ዱሜራና  የዱሜራ ደሴቶች ጉዳይ  የሁለቱ ሀገራት ጉዳይ  ብቻ አድርጎ መውሰድ አይገባም።

የኤርትራና  የጂቡቲ  እግራቸውን ያንፈራጠጡበትና የኢትዮጵያ  ማለፊያ  አጥራቸውን ወደ ኋላ ሰብሰብ  በማድረግ የሚያጡት ነገር አይኖርም፡፡ በአለምአቀፍ ህግም ፤ይሁን የሦስቱ ህዝቦች ወንድማማችነት የትስስር ነጥብ ራስ ዱሜራ ብትሆንስʔ በኤርትራና በጂቡቲ ድንበሮች መካከል ኢትዮጵያ  ቢያንስ የአንድ አውራጎዳና ስፋት ክፍተት ቢኖራት፤ የራስ ዱሜራ ደሴቶች ላይ ባህር ኋይሏ በነጻነት መስፈር ይችላል፡፡ ኤርትራና ጂቡቲ በመሀል በሚፈጠር ቀጭን መስመር የሚለውጠው ነገር ቢኖር ኤርትራና ጂቡቲ ኩታ ገጠም  ጎረቤታም  ሀገር መሆን ብቻ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን ኮሪደር  ማግኘቷ የወደብ ገቢ ያሳጠናል  የሚል ስጋት መኖር የለበትም፡፡ አሁን ኢትዮጵያ የወደብ ጉዳይ ሳይሆን ከውጭ ጠላቶች የሚሰነዘርባትን ጥቃትም ሆነ የኢኮኖሚ ደባዎች የምትከላከልበት መተንፈሻ የሚያስፈልጋት ጊዜ ላይ ናት፡፡

ያም ሆነ ይህ የአርጀንቲናና እንግሊዝ በፎክላንድ ደሴቶች ውዝግብና ጦርነት የደሴት ትንሽ እንደሌለው ይነግረናል።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top