Connect with us

ያ ትውልድ ለምኞቱ የሚጠልፈኝ፤እኔ የሮፍናን ትውልድ ነኝ፡፡

ያ ትውልድ ለምኞቱ የሚጠልፈኝ፤እኔ የሮፍናን ትውልድ ነኝ፡፡
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ያ ትውልድ ለምኞቱ የሚጠልፈኝ፤እኔ የሮፍናን ትውልድ ነኝ፡፡

ያ ትውልድ ለምኞቱ የሚጠልፈኝ፤እኔ የሮፍናን ትውልድ ነኝ፡፡

(ሄኖክ ስዩም -ድሬቲዩብ)

የሮፍናንን ሙዚቃ ሰማሁት፡፡ ልጁ በስታይሉ ብቻ አይደለም የሚዘንጠው፡፡ ሀሳቡም ዘናጭ ነው፡፡ መንፈሱም እንዲሁ፡፡ ዘናጭ ሀሳብ ሰውን ሰው ነው ብሎ ማመን ነው፡፡ ደግሞ ሙዚቃ ባህልህን ትሸጥበታለህ እንጂ ባህልን አታስጠምድበትም፡፡ ኪነት ስምም ክብርም የሚኖራት እንዲህ እውነት ታሪክና ውበት ስትሆን ነው፡፡

የሙዚቃ ምትና ዜማ ብቻ ሳይሆን ቅንጡ የግጥሞቹም ይዘቶች ናቸው፡፡ ያጓጓሉ፡፡ ሮፍ ስለ ትውልዱ ጫንቃ ስምን በመቀበል የመጉበጥ ስቆቃ “እህ” ብሏል፡፡ “የሀገሬ ልጅ ስም አገኘህ ወይ?” ብሎ ይጠይቃል፡፡ የሀገሩን ልጅ ማነኝ አልሽ ይሆንም ይላል፡፡ ልቡ እውነት ማየቱን የራሱን አጋራ፤ ማን እንደተባለ ነግሮን፤ ነው የተባለውን ዞር ብሎ ወደ ኋላ ሲቃኝ ስሙ በክብር ቃል ተጽፎ አነበበ፤ ሰው የሚል፡፡

ይህ ትውልድ ሰው መሆን ይሻ ነበር፡፡ የሚገፋው ትውልድ አለ፡፡ ሂሳቡን ያላወራረደ፡፡ በቁጭት የሚወራረድ፡፡ ሰው ስቀል እያለ፤ ሰው ግደል እያለ፤ ሰው አባር እያለ፡፡ መልሶ ይሄ ትውልድ ሲል የሚኮንነው፡፡

ሮፍናን ግን የኔ ትውልድ ነው፡፡ የኔ ሰው መሆን ከፍ አድርጎ ያሰማ፡፡ በአዲስ ሙዚቃ ስልት ሊደመጥ የሚወደድን ሀሳብ ይዞ ከተፍ ያለ፡፡

እኛ ከቋንቋችን በፊት ሰዎች ነን፡፡ ከዘራችን በፊት ሰዎች ነን፡፡ ሃይማኖተኞች ከሆንን ፈጣሪ የሆነውን ሁሉ የሆነልን ሰው ስልሆንን ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ተከታይ ቋንቋ ወደ ሰማይ እወጣለሁ ብሎ ከሃጢአቱና ከልቡ ማበጥ የተነሳ የሰው ልጅ እንዲጠፋበት የተሰጠው መሳሪያ ነው ብሎ ያምናል፡፡

እንደ ባቢሎን የቋንቋችን መብዛት ግንብ እንዳንሰራ ሳይሆን ያደረገን ግንብ እንድናፈርስ ነው፡፡ ከቋንቋ በፊት ሰው ነኝ ብሎ ማዜም፤ ተው በቋንቋህ ምክያት ሌላ አትሁን ማለት ነው፡፡

ከዘርህ በፊት ሰው ነኝ ካላልክ ለዘርህም የማትሆን መካን ነህ፡፡ ይሄ ትውልድ እንዲህ ያስባል፡፡ ልክ አይደለህም በሚል ችግሩን መከራውን ረሃቡን ምክንያት ብለው አንተ ከሰውነትህ በፊት ዘር ነህ ይሉታል፡፡ እኔ የሮፍናን ትውልድ ነኝ፡፡ ከሁሉ የሚቀድም ሰው መሆኔ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ሰው ነኝና፡፡

ሮፍናን ስለ ሀገር መዝፈን ይችልበታል፡፡ ሀገር መውደድ እንጂ ሀገር መንጠቅ መንፈሱ ያልሆነ ድንቅ ሙዚቃ አደምጫለሁ፡፡ ከኢትዮጵያ መፈጠር ብዙ መሆንና ነጠላነት አልባ እንደሆነ በየቀኑ ከሚወጡት መጻሕፍት በተሻለ የሚናገር ሙዚቃ ሆኖ አገኘሁት፡፡

ማን ነህ ሲባል ኢትዮጵያዊ ማን ነኝ ለማለት ብዙ መሆኑን መርሳት እንደሌለበት የዘር፣ የቋንቋና የእምነት ልዩነቱ ከሌለበት ጭምር እንዳኖረው አሳየን፡፡ እሱ የዚህ ትውልድ አባል ሮፍናን ነው፡፡

የኔ ትውልድ የሚለው ሮፍናን የእኛ ትውልድ እንደሆነ ስለመሻታችን ዘፍኖ ነገረን፡፡ ዘፈን የሚለው ቃል ለሁሉ መሆኑ ቆጨኝ፡፡ ሙዚቃ ይሉት ስም የወል መጠሪያ ስለሆነ የሮፍናን እንዲህ ነው ማለት ከባድ መሰለኝ፡፡ ጥበብ ነው፡፡ ሀሳብ ተሸክሞ ትውልድን በምድረ በዳ ኑ ተመለሱ የሚል ጥበብ፡፡

ሃይማኖተኞቹ ሰው ነን ማለት ትተዋል፡፡ እኛና እነሱ ሲሉ ሁለትና ብዙ አድርገውናል፡፡ ፖለቲከኞቹ በየምክንያቱ አብዝተውናል፡፡ እነሆ ሮፍናን በጥበበኛ ስራው ሰበሰበን፤ ሰው ነን ሲል፡፡ የትውልዴን ከያኒ እጋራዋለሁ፡፡ አዎ ሰው ነኝ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top