Connect with us

የብልፅግና ዕጩ ተወዳዳሪው ማስጠንቀቂያ!!

የብልፅግና ዕጩ ተወዳዳሪው ማስጠንቀቂያ!!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የብልፅግና ዕጩ ተወዳዳሪው ማስጠንቀቂያ!!

የብልፅግና ዕጩ ተወዳዳሪው ማስጠንቀቂያ!!

“የብልጽግና አካሄድ ራሴን ከምርጫ እንዳገል ሊያደርገኝ ነው!” ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ

ማንም ሰው በቀላሉ  እንደሚገነዘበው እስከቅርብ ጊዜ ድረስ እኔ የብልጽግና አባል ያልነበርሁ ሲሆን አሁንም ጭምር የብልጽግና አመራርና አባላት የሚፈጽሟቸውን ያልተገቡ ተግባራትና አካሄዶች አምርሬ እየተቸሁ አካሄዱን እንዲያስተካክልና ሕዝብንና አገርን የሚጠቅም ስራ እንዲሰራ በጽናት ስታገልና ስወተውት እንደነበር ይታወቃል።

ይህም ሆኖ የልዩነት ሀሳቤን በመያዝ በመጭው ምርጫ ብልጽግናን ወክየ ለአዲስ አበባ ም/ቤት አባልነት ለመወዳደር በዕጩነት ለመቅረብ ተስማምቼ ተመዝግቤያለሁ። ይህን ያደረግሁበት ምክንያት አንድም ብልጽግና የመሻሻል ዕድል ካለው በውስጣቸው ሆኜ የሚፈጽሙትን ችግር በድፍረት ለመታገል፣ ሁለትም ለህዝባችን ድምጽ ለመሆን ነበር። 

ይሁን እንጂ ብልጽግና ከጊዜ ወደ ጊዜ  ከመሻሻልና ለሕዝብና ለሀገር ህልውና መረጋገጥ ተግቶ ከመስራት ይልቅ ችግሩ እየተባባሰ እንዲሄድ አስተዋጽዖ እያደረገ ይገኛል። ይባስ ብሎ የአማራ ሕዝብ በየቦታው እየታረደ፣ ከቀየው በግፈኞች እየተፈናቀለ እና ንብረቱ እየተዘረፈ ባይተዋር እየሆነ ሲመጣ የተመለከተው የአማራ ክልል ሕዝብ ቁጣውን በሰላማዊ ሰልፍ ሲገልጽ መሪየ ተሰደበ፣ ፎቶው ተዘቀዘቀ፣ የፓርቲ ፖስተር ተቀደደ ወዘተ የሚል የማይረባ መግለጫ አወጣ።  

ከዛም አልፎ ያለ ሀጢያቱ እየሞተ ያለው፣ በግፍ እየተፈናቀለ የሚገኘው እና ለዘመናት ያፈራው ሀብቱና ያለማው መሬቱ በተረኞች አየወደመና እየተዘረፈ ያለው የአማራ ሕዝብ ሆኖ ሳለ ይህን ህገወጥ ድርጊት ከማስቆም ይልቅ በስሜትና በብስጭት ሰልፍ የወጣ ህዝብ ያውም ጥቂት ግለሰቦች የያዙትን መፈክር ነቅሶ በማውጣት ለምን ብሎ ለማጣጣል መሞከር እጅግ የሚያስተዛዝብ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

ስለሆነም በየትኛም የአገሪቱ አካባቢ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ጭፍጨፋና ማፈናቀል በአስቸኳይ እንዲቆም ካልተደረገ፣ በጨዋነትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በየከተሞቹ ሰልፍ የወጣው የአማራ ሕዝብ ድምጽ የማይሰማ ከሆነ እና ጥያቄውም ተገቢ ትኩረት ተሰጥቶት በአፋጣኝ ካልተመለሰ ራሴን ከዕጩ ተወዳዳሪነት እንዳገል የምገደድ መሆኔን ከወዲሁ  ለማሳወቅ እወዳለሁ።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top