Connect with us

በውስጥም በውጭም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሀይሎች ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨትና አንድነትን ለመናድ ጥረት እያደረጉ ነው

የሰላም ሚኒስቴር በውስጥም በውጭም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሀይሎች ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨትና አንድነትን ለመናድ ጥረት እያደረጉ ነው አለ
Photo: Social media

ማህበራዊ

በውስጥም በውጭም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሀይሎች ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨትና አንድነትን ለመናድ ጥረት እያደረጉ ነው

የሰላም ሚኒስቴር  በውስጥም በውጭም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሀይሎች ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨትና አንድነትን ለመናድ ጥረት እያደረጉ ነው አለ

ህግ ለማስከበርና ፍትህ ለማስፈን ብሎም የጥፋት ሀይሎችን ህግ ፊት ለማቅረብ መንግስት ሌት ከቀን እንደሚሰራ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሰላም ወዳዱን ህዝብ ኢላማ ያደረገ ሀብትና ንብረትን ከማውደም አልፎ በንጹሀን የዜጎች ህይወት ዋጋ እያስከፈለ ያለ የጥፋት ቡድኖች ሴራ እዚህም እዚያም እያጋጠመን ይገኛል ብሏል ባወጣው መግለጫ።

በዚህም ልብ ሰባሪ አጋጣሚዎች አጋጥመዋል እያጋጠሙም ይገኛል ነው ያለው።

እነዚህ በውስጥም በውጭም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሀይሎች ሰላምን ለማደፍረስ፣ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨትና አንድነትን ለመናድ ጥረት እያደረጉ መሆኑን መላው ህዝብ ተገንዝቦ፣ አንድ ሆኖ ከጸጥታ ሀይሉ ጋር በመተባበር ችግሩን ለመፍታት መረባረብ  ያስፈልገናል ሲል ገልጿል።

መንግስት የጸጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ጸጥታ በማደፍረስ ስራ ላይ በተሰማሩ የጥፋት ቡድኖች ላይ ተከታታይ እርምጃ በመውሰድ የህግ የበላይነት ለማረጋገጥና አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ቤተሰብንና ወዳጅን እንኳን በአመጸኞች እጅ ይቅርና በተፈጥሮ ግዴታ ማጣት እጅግ ቅስም የሚሰብር ነው ያለው ሚኒስቴሩ ባጋጠመው የጸጥታ መታወክ ሳቢያ ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ እና ለተጎዱ ወገኖቻችን መጽናናትን ተመኝቷል።

በእስከአሁኑ ሂደት በተለያዩ ክልሎች ያጋጠሙ ችግሮችና በዜጎች ላይ የተፈጸሙ አሰቃቂና አሳዛኝ ጥቃቶችን በተመለከተ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የምርመራ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብሏል።

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top