Connect with us

አሁንም ከስሜት ፈረስ ወጥተን ቀልብን ሰብሰብ በማድረግ ማሰብ ይኖርብናል!

አሁንም ከስሜት ፈረስ ወጥተን ቀልብን ሰብሰብ በማድረግ ማሰብ ይኖርብናል!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

አሁንም ከስሜት ፈረስ ወጥተን ቀልብን ሰብሰብ በማድረግ ማሰብ ይኖርብናል!

አሁንም ከስሜት ፈረስ ወጥተን ቀልብን ሰብሰብ በማድረግ ማሰብ ይኖርብናል!

ባለፉት 30 አመታት ከክልሉ ውጭ በሚገኝ የአማራ ህዝብ ላይ ሲደርስ የነበረውን ግፍና በደል፣ ማፈናቀልና በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፍ ሁላችንም የምናውቀው እውነት ነው፡፡ 

ይኸ ሁኔታ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉም በግልጽ እየታየ እንደሆነም በየቀኑ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡ ይህም ሆኖ ይህን ችግር በዘላቂነት ለማስወገድ የሚያስችል የመፍትሄ ሀሳብ ስናቀርብ በስሜት ሳይሆን በስሌት፣ በጀብደኝነት ሳይሆን በብልሀት እንዲሁም በአየር ላይ ሳይሆን መሬት ላይ ያለውን ሀቅ መሰረት በማድረግ መሆን ይኖርበታል፡፡

በዚህ ረገድ መነሳት ያለባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች አማራ ክልል በሚባለው ውስጥ ያለውን አማራ መብትና ጥቅም በአግባቡ ማስከበር ችለናል ወይ የሚለው ነው (ባለፉት ሶስትና አራት አመታት በጎንደር አማራና – ቅማንት መካከል፣ በሰሜን ሸዋ የኢፍራታና ግድም እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥና መካከል ያለው አማራና ኦሮሞ ተስማምቶ እንዲኖር ማድረግ አለመቻሉ እየታወቀ) በአስር ሚሊዮኖች ህዝብ አምጥቶ የት ነው የሚሰፍረው የሚለው ጥያቄ በሚገባ መመለስ ያለበት ይመስለኛል፡፡

ሌላው ከአስር ሚሊዮን ህዝብ በላይ ቀርቶ በአስርና በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ህዝብን እንኳ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ወስዶ ለማስፈር ክልሉ ውስጥ በቂ የሆነ መሬት የለም፣ ቢኖር እንኳ ምን ያህል ገንዘብ፣ ቁሳቁስ፣ የሰው ሀይልና የመሰረተ ልማት ዝግጅት እንደሚጠይቅ ማሰቡ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማወቅ የሚቻለው ከዚህ በፊት የተካሄዱትን የሰፈራ ፕሮግራሞች ቀረብ ብሎ መመርመር ሲቻል ነው፡፡ 

አለበለዚያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንዲያ ስላሉ በቀላሉ የሚፈጸም እንደሆነ አድርጎ መረዳት ካለ የችግሩን ስፋት በሚገባ አለመገንዘብ ነው የሚሆነው፡፡

ይህንን እውነታ በአህዝ አስደግፈን እንመልከተው፣ ለምሳሌ አንድ ሚሊዮን ህዝብ አምጥተን እናስፍር ቢባል ለአንድ ሰው የመጓጓዣ፣ የቤት መስሪያ፣ የቀለብ፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት (ቢያንስ ትምህርት፣ ጤና፣ ውሀ በአቅራቢያው መገኘት አለባቸው) በድምሩ በትንሹ አንድ መቶ ሽ ብር ያስፈልጋል ብለን ብናስብ አንድ ሚሊዮን ሲባዛ በአንድ መቶ ሽ ብር እኩል ይሆናል አንድ መቶ ቢሊዮን ብር፡፡ 

እውነታ ይኸው ነው፣ ይህን በአስር ሚሊየን ስታባዛው የሚመጣውን ገምት፡፡ ይህም ማለት ግን የፋይናስ ሰዎች እንዳትስቁብኝ አንድ መቶ ሽብር በቂ ነው እያልሁ እንዳልሆነ ግንዛቤ ይያዝልኝ፡፡

ከሁሉም በላይ ግን አሁን ላይ ችግር እየተፈጠረባቸው በሚገኙ የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ የሚገኘውን አማራ በስሜት ተነሳስተን ማስወጣት ስንጀምር ሌሎቹ የኦሮሚያ አካባቢዎችም ይኸ ህዝብ እንዲወጣላቸው ጭፍጨፋውን አጠናክረው መቀጠላቸው አይቀርም፣ ከዛም አልፎ ሌሎች ክልሎችም ይህን በማድረግ ከክልላቸው እንዲወጣ ለማድረግ እንዲዘጋጁ መንገዱን ማሳየት ነው የሚሆነው፡፡ 

እናም ይኸኛው መፍትሄ የትም የሚያደርስ ሆኖ ስላላገኘሁት ነው ትክክል አይደለም በማለት የምሞግተው፡፡

ስለሆነም በእኔ እምነት መፍትሄው አንደኛ አሁንም እደግመዋለሁ በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ የሚገኝ አማራ እንዲደራጅ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ እንዲፈቅድና አብሮን እንዲሰራ ለማድረግ የሚያስችል የተቀናጀ ስራ እንሰራ፡፡ ሁለተኛ ሀገራዊ ስሜት ካላቸው የኦሮሚያና የሌሎች ክልሎች አመራሮች ጋር ተቀራርቦ በመነጋገር ችግሩ የሚቆምበትን ስልት መቀየስና ጠንከር ብሎ መገኘት ያስፈልጋል፡፡ ሶስተኛ በአማራ ክልል ውስጥ ያለው ልሂቅ አንድ ላይ በመቆም ህዝቡን በማደራጀት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና ይጫወት፣ ይህን ድርሻውን ለመወጣትም ከፌዴራሉ መንግስት ጋር በመነጋገር ህዝቡ እንዲታጠቅ መታገል፣ በቃ የተሻለው መፍትሄ ይኸው ነው፡፡

በነገራችን ላይ በዋነኛነት እየጠቃ ያለው ህዝባችን በአብዛኛው በተበተነ መልኩ የሚኖረውና በአግባቡ ያልተደራጀው እንደሆነ መታወቅ አለበት፣ ወለጋን ጨምሮ በአንጻራዊ መልኩ በተደራጀ አኳኋን የሚኖሩ አማሮች ራሳቸውን እየተከላከሉና ጥቃቱን እየቀነሱ መሆኑን ከስፍራው በደረሱኝ መረጃዎች አረጋግጫለሁ፡፡ 

ቀደም ሲል አርሲ አካባቢም ተደራጅተው ራሳቸውን ለመከላከል ጥረት ያደረጉ ወረዳዎች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ቀርቷል፣ ያልተደራጁት ግን የከፋ ጥቃት ደርሶባቸዋል፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top