Connect with us

በምዕራብ ወለጋ ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ በማስመልክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰጠው  መግለጫ እነሆ፡-

በምዕራብ ወለጋ ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ በማስመልክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰጠው መግለጫ እነሆ፡-
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

ዜና

በምዕራብ ወለጋ ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ በማስመልክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰጠው  መግለጫ እነሆ፡-

በምዕራብ ወለጋ ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ በማስመልክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰጠው  መግለጫ እነሆ፡-

ሀገራችን እና ክልላችን ባለፉት ሶስት የለውጥ ዓመታት  የተሳለጠ ሽግግር ለማሳካት ሲሰሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ከለውጥ ሂደቱ በተቃራኒው የቆሙ ሃይሎች ሙሉ ሓይላቸውንና አቅማቸውን አሟጠው ለጥፋትና  አፍራሽ ድርጊት ሲያውሉ ነበር፡፡

ከለውጥ ሂደቱ በተቃራኒ ከቆሙት የጥፋት ሓይሎች መካከል የጁንታው ተላላኪ ኦነግ ሸኔ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው፡፡

ይህ ሀይል የመንግስት መዋቅርን በማፍረስ የአፍራሽና የመተላለቅ ሰንሰለቱን ለማስፋት ሲታትር እንደነበር በግልጽ የሚታወቅ ነው፡፡

የጁንታው ተላላኪው ኦነግ ሸኔ የጥፋት ሰንሰለቱን በገጠርና በከተማ በማስፋት በመንግስት አመራሮችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ዘግናኝ የሽብር ጥቃቶችን ሲፈፅም ቆይቷል፡፡

በዚህም ሳቢያ የብዙ ንፁሃን ዜጎች ህይወት አልፉዋል፡፡ከቀበሌ እስከ ክልል አመራር ድረስ የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡አያሌ  የግልና የመንግስት ንብረቶች ወድመዋል፡፡

የዚህን የኦነግ ሸኔ እኩይ ተግባር ለማስወገድ መንግስት በወሰደው የህግ በላይነትን የማስከበር እርምጃ ሀይሉ እየተዳከመ የሄደ ቢሆንም በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ የጥፋት ሴራውንና እርምጃውን ቀጥሏል፡፡

በትናንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ በቦኔ ቀበሌ በወሰደው የሽብር ጥቃት ለግዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች በጥቃቱ ህይወታቸው አልፏል፡፡

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት  በዚህ አሰቃቂና ዘግናኝ ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለተጎጂ ቤተሰቦችና ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

የክልል መንግሰት ድርጊቱ  በተፈጸመበት አካባቢ በፍጥነት በመድረስ በወሰደው እርምጃ በጥቃቱ አድራሾች ላይ የአጸፋ እርምጃ የወሰደ ሲሆን በቀጣይነትም የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እንደምናደርግ ከወዲሁ እንገልጻለን፡፡

ከሃገር ግንባታ ሂደት በተቃራኒ የቆመው ይህ ሓይል አቅዶ የሚንቀሳቀሰው የጥፋት ሴራ በህዝቦች የተባበረ ክንድ ላለመመለስ እንደሚመክን እርግጠኞች ነን፡፡

ስለሆነም ህዝባችን አንድነቱንና መተባበሩን የዚህን ሓይል የጥፋት ሴራ እንዲያከሽፍ  የክልሉ መንግስት ጥሪ ያቀርባል፡፡

በልጆቿ ደምና አጥንት ላይ የተገነባች ኢትዮጵያ በሽብርተኞች ሴራ አትፈርስም!

 የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት

ፊንፊኔ

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top