Connect with us

“መጪው ምርጫ ዕድል እና ችግሮችን ይዟል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

"መጪው ምርጫ ዕድል እና ችግሮችን ይዟል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

“መጪው ምርጫ ዕድል እና ችግሮችን ይዟል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

“መጪው ምርጫ ዕድል እና ችግሮችን ይዟል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

መጪው ምርጫ ለአገሪቱ ዕድል እና ችግሮችን አጣምሮ የያዘ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ‹አዲስ ወግ› የውይይት ፕሮግራም ላይ ገልፀዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱንም ተገንዝቦ ለመምረጥ የሚነሳና የሚመርጠውን አካል ሕጋዊነት ያረጋገጠ ማኅበረሰብ እንዲፈጠር ይህን መሰል ውይይቶች እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። 

አጋጣሚውን ሁከት መቆስቆሻ ለማድረግ የሚፈልጉም ቅጥረኞች እንዳሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። 

ችግሮችን በመፍራት ምርጫ አሁን አይኑር የሚሉም አካላት አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የእኛ ዓላማ ኢትዮጵያን አሸናፊ ማድረግ ነውና ሁላችን ኢትዮጵያውያን ለዚያ እንተባበር” ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። 

በመጪው ምርጫ የከተማዎች ሰላማዊነት እንደማያሳስብም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት። 

ሊተኮርበት የሚገባው ሰው ወጥቶ ለመምረጥ ሕዝብ ደህንነት እንዳይሰማው የሚያደርጉ ቅጥረኞች ጉዳይ ነው። 

ይህንንም በጊዜ ለጸጥታ አካላት መረጃ በመስጠት ለመከላከል እንችላለን። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ምርጫ ካለፉት የተሻለ ውጤት ይገኛል ብለው እንደሚያምኑም ገልፀዋል።(EBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top