Connect with us

ሰላም ሚኒስቴር በሃሰተኛ ወሬዎች ሕዝበ ሙስሊሙን እያደናገሩ ነው ያላቸው አካላትን አስጠነቀቀ

ሰላም ሚኒስቴር በሃሰተኛ ወሬዎች ሕዝበ ሙስሊሙን እያደናገሩ ነው ያላቸው አካላትን አስጠነቀቀ
ሰላም ሚኒስቴር

ዜና

ሰላም ሚኒስቴር በሃሰተኛ ወሬዎች ሕዝበ ሙስሊሙን እያደናገሩ ነው ያላቸው አካላትን አስጠነቀቀ

ሰላም ሚኒስቴር በሃሰተኛ ወሬዎች ሕዝበ ሙስሊሙን እያደናገሩ ነው ያላቸው አካላትን አስጠነቀቀ

(የሚኒስቴሩ መግለጫ እነሆ)

መንግስት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት ተጠብቆ በሰላምና በትብብር ህዝበ ሙስሊሙ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት ውስጥ ሚናውን እንዲወጣ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በዚህም መንግስት ህዝበ ሙስሊሙ ህዝቡ በመረጠው በራሱ አመራርና አደረጃጀት መስራት እንዲችል በተለያዩ ጊዚያቶች የነበሩ ልዩነቶችን በማጥበብ አንድነታቸውን ጠብቀው እንዲሄዱ ሰፊ ጥረት በማድረግ እንዲሁም ከተቋቋመው ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር በቅርበት በመስራት የሙስሊሙን ህብረተሰብ የአንድነት ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛውን የአጋዥነት ሚና የተጫወተ መሆኑ ዕሙን ነው። 

በተጨማሪ ለበርካታ ዘመናት የሙስሊሙ  ህብረተሰብ ጥያቄዎች የነበሩ በተለይም የእስልምና ምክር ቤቱ እንደ ማህበር ከሚታይበት አሰራር ተላቆ ህጋዊ መሰረት ያለው ተቋም እንዲሆን በአዋጅ እንዲቋቋም፣ እስላማዊ ባንክ እንዲፈቀድ፣ የመስገጃ ቦታ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ሰፊ ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በየወቅቱ ከእስልምና ጉዳዮች ወደ ተቋማችን የሚመጡ የድጋፍ ጥያቄዎች ህግና ስርዓትን ተከትለው ተገቢው አዎንታዊ ምላሽ እንዲያገኙ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በሂደቱም በመጅሊሱ ቦርድ እና የዑለማዎች ም/ቤት መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት በተለያዩ ጊዜያቶች ለመ/ቤቱ በቀረቡለት ተደጋጋሚ የድጋፍ ጥያቄዎች መሰረት የሚመለከታቸውን አካት ሁሉ በማካተት በተደጋጋሚ በተናጠልና በቡድን በማነጋገር፤ አንድነታቸው ላይ ትኩረት በማድረግ ልዩነታቸውን በማጥበብና አስቀድመው ችግራቸውን በምክክር ፈትተው በጋራ ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ በተለያየ ጊዜ እርቅና ስምምነት እንዲወርድ በመምከርና አቅጣጫ በማስቀመጥ ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ 

በዚህም ሚኒስቴር መ/ቤታችን አብዛኛውን ጊዜ በሁሉም ወገን የታዩ ጉድለቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ስምምነት  በመድረስ ረገድ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግና ሲያበረታታ የቆየ ቢሆንም የተቀመጡና በጋራ ስምምነት የተደረሰባቸው አቅጣጫዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች በሁለቱም ወገኖች በኩል ሊተገበሩ አልቻሉም።

ህዝበ ሙስሊሙን የመምራት ሃላፊነት የተጣለባቸው አካላትም በቅድሚያ በመካከላቸው ያለውን የተከፋፈለ ሃሳብ መልክ አስይዘው በመግባባትና የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ የጋራ ጠቅላላ ጉባዔ በአስቸኳይ ጠርተው በጋራ በመምከር ከዚህ ቀደም በስምምነት የፀደቁ ሰነዶችን ወደ ተግባር እንዲያሸጋግሩ እንዲደረግ፤ መግባባት ያልተደረሰባቸውን ጉዳዮች ግን በጋራ መድረክ በምክክር እንዲፈቱ አቅጣጫ በማስቀመጥ፣ ተቋማዊ አሰራሮች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ሙስሊሙ ማህበረሰብ አንድነቱን ጠብቆ ችግሩን በራሱ እንዲፈታ መ/ቤታችን ሲያሳስብ እና ሲመክር ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ጉዳዩ በመሠረታዊነት የመጅሊሱ ዉስጣዊ ችግር እንደሆነ ህዝበ ሙስሊሙ የሚረዳው ሲሆን ሰላም ሚኒስቴር ላለፉት ጊዜያቶች ችግሩ እንዲፈታ በተጠየቀው ድጋፍ መሠረት በርካታ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም ለህዝበ ሙስሊሙ ሰላምና አንድነት ተገቢውን ሁሉ ዓይነት ድጋፍ አድርጓል እያደረገም ይገኛል። ሆኖም ግን አሁን በተለያዩ የግልና የቡድን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች እና በተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች የሃሰት መረጃ መሆናቸውን ህዝበ ሙስሊሙ እንዲያውቅ እንፈልጋለን፡፡

ስለሆነም አሁን እየተሰራጨ ያለው መረጃ እንደተቋም ስናደርግ ከነበረው ያላሰለሰ ጥረት እጅግ የራቀ የሃሰት መረጃ ሲሆን ሃገራዊው ምርጫ መንግስታዊ ሰርዓት መመሰረቻና ማጠናከሪያ እንጅ ከሀይማኖታዊ አሰራር ጋር ግንኙነት የሌለው መሆኑ እየታወቀ ለራስ የግል ጥቅም በሚመች መንገድ መልዕክት እያዘጋጁ ሙስሊሙን ህብረተሰብ ለማደናገር የሚደረግ ጥረት ተገቢነትም፣ እውነትነትም፣ ተቀባይነትም እንደሌለው ለመግለጽ እንወዳለን።

የሰላም ሚኒስቴር ደጋግሞ ያስገነዘበው ጉዳይ ቢኖር ልዩነቶችንና አለመግባባቶችን ማጥበብ ከማንኛውም ተግባር ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲሰራ ሲሆን ነገር ግን በሁለቱም በኩል ያለው መካረር ለችግሩ መፍትሄ ከማስቀመጥ ይልቅ በሁለቱም ወገኖች መካከል ያለው መካረር ችግሩን እያሰፋው ያለ መሆኑን አሁን ያለንበት ሁኔታ በግልጽ ያሳያል።

እስካሁን ባለው ሁኔታ መፍትሄ በማፈላለግ በሂደቱ ሲሳተፉ የነበሩ አካላት በጋራ ስምምነት የተደረሰባቸውን የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ ከማድረግ ይልቅ በየፊናቸው ሲያፋርሱ እና ልዩነቱን ሲያሰፉት የቆዩ መሆናቸውን ህዝበ ሙስሊሙ ሊያውቀው ይገባል።

በመሆኑም በተለያዩ ጊዜያት በተለይም በትናንትናዉ እለት በተለያዩ ግለሰቦች ማህበራዊ ድረ ገፆች እና በአንዳንድ ሚዲያዎች እየተላለፉ ያሉ የተሳሳቱ መረጃዎች የሰላም ሚኒስቴር የማያውቃቸው እና እያቀረቡት ባለው መልክ አስተያያትም ሆነ መልስ ያልሰጠንባቸው እንደሆኑ በአንፃሩ ሁለቱም ወገኖች ችግራቸውን በምክክር እንዲፈቱ ሲደረግ የቆየውን ከፍተኛ  ጥረት ህዝበ ሙሰሊሙ እንዲረዳ እናስታውቃለን። 

በዚህ መልኩ ህዝበ ሙስሊሙን ለመከፋፈልና አንድነቱን ለማናጋት ብሎም መንግስትና ህዝብን ለማራራቅ ሀሰተኛ መረጃ በግል የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችና በተለያዩ ሚዲያዎች የሚያሰራጩ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊቶቻቸው እንዲቆጠቡ ልናሳስብ እንወዳለን።

ህዝበ ሙስሊሙም በሃሰተኛ መረጃ እንዳይደናገርና  ትክክለኛ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ሰላሙን እና አንድነቱን ጠብቆ እንዲሄድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የሰላም ባለቤት እርስዎ ነዎት!

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top