Connect with us

ልጅ ሚካኤል-የአራዳ ልጅ፤ እራስን መጠበቅ ዘንጦ መሰልጠን እንደሆነ በጉማ አዋርድ ያሳየ ሰው

ልጅ ሚካኤል-የአራዳ ልጅ፤ እራስን መጠበቅ ዘንጦ መሰልጠን እንደሆነ በጉማ አዋርድ ያሳየ ሰው
ሄኖክ ስዩም

ዜና

ልጅ ሚካኤል-የአራዳ ልጅ፤ እራስን መጠበቅ ዘንጦ መሰልጠን እንደሆነ በጉማ አዋርድ ያሳየ ሰው

ልጅ ሚካኤል-የአራዳ ልጅ፤ እራስን መጠበቅ ዘንጦ መሰልጠን እንደሆነ በጉማ አዋርድ ያሳየ ሰው

(ሄኖክ ስዩም – ድሬ ቲዩብ)

ከጉማ አዋርድ ምስሎች የገዙኝ ሁለት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ አለባበስ ለብሰው ልቤን ወከክ ያደረጉት የሀገሬ ከያኒያንና ተጠንቅቆም መዘነጥ እንደሚቻል ያሳየው ልጅ ሚካኤል፡፡

ሰሞነኛ የኮሮናን መከላከል ዘዴያችን አስቂኝ ነው፡፡ ብቻችንን መኪና ውስጥ ያደረግነው የአፍና የአፍንጫ ጭምብል ሰው ወደ ተሰበሰበበት ስንቀርብ እናወልቀዋለን፡፡ ጥንቃቄ ስሙም አይነሳም፡፡ አንድ ጃፓናዊ ተያዘ ተብሎ ባልና ሚስት ሳይቀር መጨባበጥ የፈሩበትን የመከላከል ሰሞን ስናስብ የአሁኑ እብደት ነው፡፡

ከሚመረመሩት ሦስት ሰዎች አንዱ ኮሮና አለብህ እየተባለ ዛሬም ከኮሮና በፊት ከነበረን ጠባይ የተለየ ነገር አይታይብንም፡፡ ኮሮናው ገባ ብለው ሀገሩን እናስተምር ሲሉ የነበሩ የኪነት ሰዎች አሁን የኮሮና መስፋፋት ምክንያትና የሀገር ስጋት ሆነው እያየናቸው ነው፡፡

ሰሞኑን የተካሄደው ጉማ ዓመታዊው የፊልም ሽልማት በርካታ ኢትዮጵያውያን ታዋቂ ሰዎችና የፊልም ባለሙያዎች የታደሙበት ነበር፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ የነበረው የጥንቃቄ ድባብ የመተንፈሻ መሳሪያ የታጣባትና በርካታ ሰው በጽኑ ህሙማን ማቆያ ክፍል የተኛባት ሀገር እየተካሄደ ያለ አይመስልም፡፡

በእርግጥ የጥበብ መድረኮች ብቻ ሳይሆኑ የአደባባይ በዓላት የፖለቲካ ጉባኤዎች የፓርቲ ድጋፍ ሰልፎችም እንዲህ ያለ ዝንጉነት የሚታይባቸው ናቸው፡፡

ምስሉን በቲዪቦች ስንከታተል አንዳንድ ጥንቁቆች አልፎ አልፎ ብቅ ቢሉም ፎቶ ለመነሳት ጭምር ጭምብሉን አውልቀው ተጠጋግተው ተሳስቀው በዚያው ረስተውን ሽር ብትን ሲሉ ተመልክተናል፡፡

እነኚህን መሳይ እውቅና ተወዳጅ ሰዎች ጥንቁቅ ቢሆኑና እንዲህ ባለው ሚሊዮኖች ዐይናቸውን ተክለው በሚመለከቱት ኩነት እንደ አብዮት አደጋውን የሚያሳይ ጥንቃቄ ቢያደርጉ ህዝቡን ለመቀየር ምትክ የለሽ እድልና አጋጣሚ ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡

በዚህ ዝንጉነትና አስረሽ ምቺው መሃል ከሁለት ሰዎች ጋር ሆኖ ጅንን ብሎ የገባው ልጅ ሚካኤል ትኩረት ሳበ፡፡ ሳቁን አላሳየንም፡፡ አፍና አፍንጫውን በጭምብል ሸፍኗል፡፡ እንቅስቃሴዎቹ ሁሉ ያለንበትን ጊዜ የገመቱ ናቸው፡፡ ያራዳው ልጅ፤ ልጅ ሚካኤል ተጠንቅቆም ዘንጧል፡፡ አፉንና አፍንጫውንም አፍኖ ከገለጡት እኩል ሞገሱ ድንቅ ነበር፡፡ ጥንቃቄውና የተሰማው ኃላፊነት ደግሞ ጎልቶ እንዲታይ አድርጎታል፡፡

አዳራሹ ውስጥም ከገባ በኋላ ሞቀኝ ብሎ አላወለቀም፡፡ ከአለባበሱ ጋር በሚሄድ ዲዛይን ሽክ ያለው ልጅ ሚካኤል “እውነትም ያራዳ ልጅ” የሚለውን ሙገሳ ከአዳራሹ ሳይወጣ ከተሜው ተቀባበለው፡፡

ልጅ ሚካኤል በርካታ አድናቂዎች እንዳሉትና እንደሚከተሉት ሰው የወሰደው ሃላፊነትና ያደረገው ጥንቃቄ ራሱን ከመጠበቅ ያልፋል፡፡ አርአያነት ያለው ስራ ነው፡፡ አንደኛ “ፕሮግራም አለብኝ” ባይነት ህይወትን ከመጠበቅ እንደማይጋጭ አሳይቷል፡፡ ደግሞ ጥንቃቄ የመዘነጥ ጠላት እንደሆነ ለሚያስበው ወገን “እንዲህም ይዘነጣል” በሚል አሳይቷል፡፡ እርሱ ዘንጦ ነበር ግን አልተዘናጋም፡፡ ኮሮና መኖሩን አረሳውም፡፡ ምን ነካው ሳይባል እንዴት ጥንቁቅ ሰው ነው ተብሎ የተመሰገነበት አለባበስ ከጥንቃቄ ጋር አሳይቶናል፡፡

አሁን ጥንቃቄው ህግ ሆኗል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ችላ ባይነት ተጠያቂነት እንዳለበትም መንግስት አሳስቧል፡፡ ከመንግስት ይልቅ የሚከበሩ ስም ያላቸው ሰዎች አርአያ ቢሆኑ ሳይገደድ ራሱን ለመጠበቅ ቁርጠኛ የሆነ ዜጋን ብዙ ማድረግ ይቻላል፡፡ አራዳነት ከአደጋ ማምለጥ ነው፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top