Connect with us

ፍ/ቤቱ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞችን በራሱ ለማስተዳደር የሚያስችሉ መስረት ጣይ ስራዎችን ጀመረ

ፍ/ቤቱ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞችን በራሱ ለማስተዳደር የሚያስችሉ መስረት ጣይ ስራዎችን ጀመረ
ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ዜና

ፍ/ቤቱ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞችን በራሱ ለማስተዳደር የሚያስችሉ መስረት ጣይ ስራዎችን ጀመረ

ፍ/ቤቱ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞችን በራሱ ለማስተዳደር የሚያስችሉ መስረት ጣይ ስራዎችን ጀመረ

በቅርቡ የጸደቀው የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞችን የማስተዳደር ኃላፊነት በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት እንደተደነገገው ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በማውጣት ሙሉ በሙሉ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይሰጣል።

የዚህን አዋጅ ድንጋጌ የሰራተኞችን መብትና ጥቅም አስጠብቆ መፈጸም ያስችል ዘንድ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ የማርቀቅ ስራ በቴክኒክ ኮሚቴ ተጀምሯል። 

ቴክኒክ ኮሚቴው በሃገራችን የረጅም ጊዜ ልምድ ካካበተው ሲቪል ሰርቪስ አስተዳዳር አዋጆች አና ደንቦች እንዲሁም ከፍርድ ቤቶች ልዩ ባህሪ በመነሳት ያዘጋጀውን የመጀመሪያ ረቂቅ ደንብ ለሶስቱም ፌዴራል ፍ/ቤቶች አመራሮች አቅርቧል ።

የፍርደ ቤቶቹ አመራሮች የቴክኒክ ኮሚቴው በአጭር ጊዜ ዝርዝር ድንጋጌዎችን የያዝ ረቂቅ ደንብ ለውይይት መነሻ በማቅረቡ የኮሚቴው እባላትን አመስግነው በረቂቅ ደንቡ ላይ ታሳቢ በተደረጉ ዋና ዋና ሃሳቦች ላይ ስፊ ውይይት አድርግዋል። 

በውይይቱ መጨረሻም ፍ/ቤቱ የስው ሃይሉን በማስተዳደር ፖሊሲ በማውጣት፣ የሰራ ደረጃን በመወሰን፣ የምዘና ስርዓት በመዘርጋት ሌሎች ተያያዥ ጉዳዪችን የሚስራ እና የጠቅላይ ፍ/ቤትን አመራር የሚያማክር ቦርድ፤ ሲቪል ስርቪስ ኮሚሽን ሲስራ የቆየውን ስራ የሚሰራ አካል ስለሚደራጅበት፣ ስለሚኖርው ስልጣንና ኃላፊነት የሚያመለክት እና አመራሩን የሚያማክር መሆኑን የሚደነግግ፤ በአዲሱ መዋቅር  ሊደራጁ የሚችሉ ልዩ ክፍሎችን የሚጠቁሙ ድንጋጌዎች፤ ከዲሲፕሊን ጋር ተያይዞ የሚውስዱ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን በነጻነት እና በገለልተኝነት የሚመለከት የአስተዳደር ፍ/ቤት መስል አካል ስለሚቋቋምበት ሁኔታ ረቂቅ ደንቡ ዳብሮ እንዲቀርብ የስራ አቅጣጫ ተስጥቷል።

ረቂቅ ደንቡ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲጠናቀቅ በእስተዳደር ዘርፍ ልምድ ላላቸው ባለሙያዎች እና ለፌዴራል ፍ/ቤቶች ስራተኞች ተወካዮች ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት መሆኑም በውይይቱ ተገልጿል ።

(ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top