Connect with us

በአውስትራሊያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።

በአውስትራሊያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።
አብመድ

ማህበራዊ

በአውስትራሊያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።

በአውስትራሊያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።

በአውስትራሊያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የድጋፍ  ሰልፍ አካሂደዋል።

ሰልፈኞቹ  የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ እንደገሚደግፉ ገልጸዋል።

በካንቤራ ከተማ  በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ በማደናገር በኢትዮጵያ ላይ ህጋዊ ያልሆነ ጫና ለማድረግ የሚሞክሩ ኀይሎችን አውግዘዋል።

ሰልፈኞቹ የሃሰት መረጃ በማሰራጨት ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ለማሳሳት የሚሰሩ አካላትን እንደሚቃወሙ ነው በድጋፍ ሰልፉ የገለጹት።

ምዕራባውያን መንግስታት ሃገራችን ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅና አንድነቷን ለማስቀጠል የምትወስደውን እርምጃ ከመደገፍ ባሻገር በውስጥ ጉዳይዋ ጣልቃ መግባት የሌለባቸው መሆኑን የሚያሳዩ መፈክሮችን ያቀረቡ ሲሆን፣ በኢትዮጵያውያን መካከል ትብብርና ወንድማማችነትን የሚያጠናክሩ መልዕክቶችንም አስተላልፈዋል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች በሁነቱ ላይ ለመታደም ከካንቤራ፣ ሲድኒ፣ ሜልቦርን እንዲሁም ረጅም ኪሎሜትሮችን በማቋረጥ ከታስማኒያና ከኩዊንስላንድ ግዛቶች እንዲሁም ከሌሎች አካባቢዎች መምጣታቸው ታውቋል። (አብመድ)

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top