Connect with us

ገቢዎች – በገቢ ተንበሸበሸ

ገቢዎች - በገቢ ተንበሸበሸ
የገቢዎች ሚ/ር

ዜና

ገቢዎች – በገቢ ተንበሸበሸ

ገቢዎች – በገቢ ተንበሸበሸ

      ባለፉት 8 ወራት ብር 191 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ገቢ ሰብስቧል፣

 በ2013 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ ብር 191 ነጥብ 28 ቢሊዮን ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 191 ነጥብ 45 ቢሊዮን በመሰብሰብ 100 ነጥብ 09 በመቶ ተመዝግቧል፡፡

ይህ አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ24 ነጥብ 63 ቢሊዮን ብር ወይንም የ14 ነጥብ 76 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

ይህም ከሀገር ውስጥ ታክስ ብር 116.70 ቢሊዮን፣ ከውጭ ቀረጥና ታክስ ብር 74 ነጥብ 59 ቢሊዮን እና ከሎተሪ ሽያጭ የተጣራ ገቢ ብር 154 ነጥብ 46 ሚሊዮን የተሰበሰበ ነው፡፡

ይህ የገቢ አሰባሰብ ከነበረውና ካለው ዓለም አቀፋዊና ሀገር አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ ከፈጠረው  ኢኮኖሚዊ ተግዳሮት አንጻር ሲታይ የተሻለ የአፈጻፀም የተመዘገበበት ነው፡፡ ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም እንዲመዘገብ አስተዋፅኦ ያደረጉ ምክንያቶች፡-

1ኛ). ዓለም አቀፍ የሆነው የኮሮና ወረርሽኝ በሀገራችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ የፈጠረውተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ፤

2ኛ). በሀገር አቀፉ የሕግ ማስከብር ዘመቻ ለ3 ወራት ያህል በትግራይ ክልል ሁለቱም ገቢ ሰብሳቢ ተቋሞቻችን ገቢ ያልሰበሰቡ በመሆናቸው፤

3ኛ). ላለፉት 8 ወራት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የፀጥታ ችግርና መፈናቀል ስለተከሰተ የንግዱ ማህበረሰብም ሆነ ተቋማችን ተረጋግቶ መሥራት ያልቻሉባቸው ሁኔታዎች እያሉ እንዲህ ያለ አፈጻፀም ማስመዝገብ መቻል ውጤቱን ይበል የሚያሰኝ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

ከላይ የተገለፀው አፈጻፀም ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የተሻለ ሆኖ የተገኘው በገቢዎች፣ በጉምሩክ ኮሚሽንና በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች ጠንካራ ሥራ ብቻ ሳይሆን ከላይ እስከታች ያሉ የመንግሥት አካላት፣ ሀገርና ህዝብ ወዳድ ግብር ከፋዮቻችን፣ የአጋር አካላትና የመላው ህዝባችን ድጋፍና ትብብር ከፍተኛ በመሆኑ  የገቢዎች ሚኒስቴር ምስጋናውን  ያቀርባል፡፡(የገቢዎች ሚ/ር)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top